በመላው ኦሮሚያ የተጠራው የስራ ማቆም አድማ ዛሬ ከተሞች ምንም እንቅስቃሴ ባለማድረግ ተጀምሯል

አባይ ሚዲያ ዜና
በአሰግድ ታመነ

በመላው ኦሮሚያ ለሶስት ቀናት የተጠራው የስራ ማቆም ከቤት ያለመውጣት አድማ በዛሬው እለት በበርካታ ከተሞች በጠቅላላ ዝግ በመሆን ተጀምሯል።

ዛሬ ማለዳ የጀመረው ሕዝባዊ የተቃውሞ በሻሸመኔ ህዝቡ አደባባይ በመውጣት አገዛዙን እያወገዘ ነው ተብሏል። የንግድ ቤቶች፣ መንግስታዊ ቢሮዎች፣ ባንክና ትምህርት ቤቶች ዝግ ናቸው ።

በሱሉልታ ከባድ ተቃውሞ እየተካሄደ ነው። አምቦ፣ ጀልዱ፣ ወሊሶ፣ ሰበታኛ ጊንጪ ተቃውሞው ተጠናክሮ ቀጥሏል፤ አለም ገናም ወጥረት አለ፣ ከምዕራብ እስከ ምስራቅ በአራቱም መውጫ የንግድ መደብሮች የጎዳና መንገዶች ጭር ብለዋል። ወለቴ ላይ አንድ የቤት መኪና ተቃጥሏል። ሱቆች ገና በለሊት ተዘግተዋል ማንኛውም ትራንስፖርት ማለፍ ክልክል ሆኖ ሁሉም ቆሟል።

ከወለጋ እስከ ሀረርጌ፣ ከባሌ እስከ አምቦ አድማው በታቀደው መሰረት በቄሮ ወጣጦጭ እየተካሄደ ነው። አገዛዙ የበቀለ ገርባን ክስ ማቋረጡን እየዘገበ ነው። የህዝብ ትግል አስጨንቆታል። በቡራዩ ቄሮዎች የከተማዋን መንገድ የዘጉ ሲሆን ምንም አይነት ተሽከርካሪ ወደ አዲስ አበባ እንዳይገባ ተደርጓል።

በሌላ በኩል የአጋዚ ጦር ትናንትና ህዝብ በጨረሰበት የሀማሬሳ ካምፕ ሌላ ግድያ እያካሄደ መሆኑ እየተነገረ ነው።

27867542_533565683681007_5259499982939083319_n

ቢሸፍቱ በዚህ ሁኔታ ላይ ነች