የመከላከያ አባላት በገበያተኛ ላይ ተኩስ ከፍተው ህይወት አጠፉ

አባይ ሚዲያ ዜና
አክሊሉ ታደሰ

በወዳወላቦ ወረዳ ወዳ ቀበሌ ለሰኞ ገበያ በወጡ የአካባቢው ነዋሪዎች ላይ በተከፈተ ተኩስ ሶስት ሰዎች ሲገደሉ ሰባት ሰዎች መቁሰላቸው ከአካባቢው በተገኘው መረጃ ለማወቅ ተችሏል፡፡

በባሌ ዞን ወዳወላቦ ወረዳ ወዳ ቀበሌ ገበያ በወጡ ሰዎች ላይ ያለአንዳች ምክንያት  ሰራዊቱ በከፈተው የእሩምታ ተኩስ ምክንያት ከተገደሉት ንጹሀን ሰዎች ውስጥ አንዷ የስምንት ልጆች እናት ሲሆኑ ሌላኛው የአስራ አራት አመት እድሜ ወጣት መሆኑን በስፍራው ከነበሩ የአይን እማኞች ለማወቅ ተችሏል፡፡

የአካባቢው ነዋሪዎች እንደተናገሩት፣ የመከላከያ ሰራዊቱ ካደረሰው ግድያ አንድ ቀን ቀደም ብሎ አስራ ሁለት የሚደርሱ የአካባቢው ነዋሪ የሆኑ ወጣቶችን አፍሶ ወደ ካምፕ በመውሰድ የደበደቧቸው ሲሆን ጸጉራቸውንም በጠርሙስ ላጭተዋቸዋል፤ በነጋታው ደግሞ በገበያተኛው ላይ ግድያ ሲፈጸም አንዳችም ምክንያት ያለመኖሩን ያስረዳል፡፡

የድብደባና ግድያ ወንጀሉ በመከላከያ ሰራዊቱ እንደተፈጸመ የሚወጡ መረጃዎች ሲያመለክቱ መንስኤው ምን እንደሆነ በግልጽ አልተቀመጠም።