ኢት-ኢኮኖሚ     ET-ECONOMY

ክፍል ሁለት

አቶ አሰፋ አብርሃ፣ አቶ በየነ ገብረመስቀል፣አቶ ብርሃኔ ገብረመድህን፣ ሜ/ጀኔራል ክንፈ ዳኘውየገቢዎችና ጉሙሩክ ባለሥልጣን 199 ቢሊዮን ብር ገቢ አቅዶ ከ90 ቢሊዮን ብር ሠበሰበ፡፡ አፈፃፀሙ የዕቅዱን 45 በመቶ ሆኖ ሾቋል፡፡

{1} ወርቅ የማዕድን ዘርፍ ፣ ኢትዮጵያ ስፊና የተለየ ባህላዊ የማዕድን ዘርፍ ወርቅ የማንጠር ብልኃትና ጥበብ የተካኑ ከ1 ሚሊዮን አስከ  1.5 ሚሊዩን (2009 ዓ/ም) የወርቅ አንጥረኛ ጠበብት ያላት ሃገር ናት፡፡ የወርቅ አንጥረኞቹ ለዜጎች ጠቃሚ የሆነ የሥራ ዕድል በመፍጠር፣ ለሃገሪቱ የውጪ ንግድ ትልቅ አስተዋፅኦ በማድረግና የውጪ ምንዛሪ በማስገኘት ከወያኔ መንግሥት ኃላፊነት በላይ የሰሩ የኢትዮጵያኖች ባህላዊ ወርቅ አንጣሪዎች ታሪክ አይረሳቸውም፡፡ በ2012 እኤአ የማዕድን ዘርፍ 19 በመቶ የአጠቃላይ የውጪ ንግድ ሸፍኖል፣10 በመቶ የውጭ ምንዛሪ አስገኝቶል፡፡ ከማዕድን የውጪ ንግድ በወርቅ ምርት የተገኘው ከ100 መቶ የሚጠጋ ሲሆን ከዚሁም ውስጥ በአመዛኙ ሁለት ሦስተኛው ገቢ የተገኘው ከባህላዊ የወርቅ አምራቾች መሆኑን የዓለም ባንክ ግሩፕ በጥናት በድረ-ገፁ አረጋግጦል፡፡ ‘‘Ethiopia also has an extensive and unique artisanal mining sector; the government estimates there are around 1 million miners, making it an important source of job creation, and an important source of foreign currency. Although the industry is in its infancy stage, the contribution to the country’s exports is already significant. In 2012, mining was responsible more than 19% of the total value of exports, and up to 10% of foreign exchange earnings. Gold makes close to 100% of mining exports and most of it, about 2/3, comes from artisanal mining, according to a recent World Bank Group (WBG) partner study, Strategic Assessment of the Ethiopian Mineral Sector

የሃገሪቱ ካላት የማዕድን ኃብቶች ዘርፍ መሪውን ስፍራ የያዘው ወርቅና ላይም ስቶን ምርቶች ሲሆን በአነስተኛ ምርቶች ደረጃ የሚመረቱት ውስጥ ታንታለም፣ ጨውና፣ፑሚስ ይገኛሉ፡፡  የዓለም ዓቀፍ ማዕድን ኢንዱስትሪ ግልፅነት ኢኒሼቲቭ፣ ዋና ዓላማ በማዕድን ኃብት ዘርፉ ሃገሪቱ ጥሩ ገቢ እንድታገኝ ለማድረግ የኢትዮጵያ ህዝብ  ካለው እምቅ የማእድን ኃብቶቹ  ተጠቃሚ እንዲሆንና በተግባር ድህነትን እንዲቀንስ  ለማበረታታትና መንግሥት በዘርፉ ለውጥ ጉልህ ሚና እንዲጫወት ማማከር ነው፡፡ በኢትዮጵያ  የማዕድን ኃብት ዘርፍ 14 በመቶ ለውጪ ንግድ፣ 1 በመቶ ለአጠቃላይ የሃገር ውስጥ ምርት (ጂዲፒ)፣ 2 በመቶ ለመንግሥት ገቢ ሲያስገኝ እንዲሁም ሪፖርት ባደረጉት ካንፓኒዎች መረጃ መሠረት ለ11,000 ሰዎች የሥራ እድል  ፈጥሮል፡፡ “The country is a leading producer of gold and limestone, but also produces smaller quantities of tantalum, salt and pumice. Ethiopia EITI aims at helping the government reform the mining sector to ensure a good return on Ethiopia’s significant untapped mineral resources. Extractive Industries contribution 14 % to exports 1 % to GDP 2 % to government revenue 11 thousand jobs (reporting companies only)” Website EITI Ethiopia 

በአጠቃላይ በ2009 ዓ/ም መረጃ መሠረት በባህላዊ የወርቅ አምራቾች ለአንድ ሚሊዮን አምስት መቶ ሽህ በላይ ሰዎች የሥራ ዕድል የፈጠረና ሁለት ሦስተኛ የሚሆነው የውጪ ንግድ ገቢ የሚያስገኘውና የውጪ ምንዛሪ ገቢ የሚገኘው ከባህላዊ የወርቅ አምራቾች ዘንድ ነው፡፡ በአንፃሩ በዘመናዊ የወርቅ አምራቾች በአል-አሙዲን ሚድሮክ ጎልድና በህወኃት/ኢፈርት ኢዛና ወርቅ ካንፓኒዎች ከዚሁ የማዕድን ዘርፍ አንድ ሦስተኛ የሚሆነው የውጪ ንግድ ገቢና የውጪ ምንዛሪ የሚያስገኙ ሲሆን ለአስራ አንድ ሽህ ሰዎች የሥራ ዕድል መፍጠር ችለዋል፡፡ ህወሓት የጦር አበጋዞች መንግስት በሁሉም የሀገሪቱ ሥፍራዎች የተገኙ የወርቅ ማዕድን ቦታዎችን በአግአዚ ጠራዊት እያስጠበቁ በመዝረፍ ላይ ይገኛሉ፡፡

ድንበር ዘለል የወርቅ ማዕድን ኮንትሮባንድ ንግድ ከወርቅ ማዕድን ኃብት ዘርፍ በውጪ ንግድ ገቢ ከ2003 እስከ 2009 ዓ/ም ማሽቆልቆል፤ የኢትዮጵያ የንግድ ሚኒስቴር ከወርቅ ማዕድን ኃብት ዘርፍ በውጪ ንግድ ገቢ ያገኘችው ውጪ ምንዛሪ ገቢ ሪፖርት መረጃ እንደሚያሳየው፡-

  • በ2003 ዓ/ም የወርቅ የውጪ ንግድ 430 ሚሊዮን ዶላር ገቢ፣ከጠቅላላ የውጪ ምንዛሪ1%፣ድርሻ ነበረው፡፡
  • በ2004 ዓ/ም የወርቅ የውጪ ንግድ 620 ሚሊዮን ዶላር ገቢ፣ከጠቅላላ የውጪ ምንዛሪ1%፣ድርሻ ነበረው፡፡
  • በ2006ዓ/ም የወርቅ ውጪ ንግድ2 ሚሊዮን ዶላር ገቢ፣ከጠቅላላ የውጪ ምንዛሪ 13.8% ድርሻ ነበረው፡፡
  • በ2007 ዓ/ም የወርቅ የውጪ ንግድ7 ሚሊዮን ዶላር ገቢ፣ከጠቅላላ የውጪ ምንዛሪ –% ድርሻ ነበረው፡፡
  • በ2008 ዓ/ም የወርቅ የውጪ ንግድ 219 ሚሊዮን ዶላር ገቢ፣ከጠቅላላ የውጪ ምንዛሪ1% ድርሻ ነበረው፡፡
  • በ2009ዓ/ም የወርቅ ውጪ ንግድ1 ሚሊዮን ዶላር ገቢ፣ከጠቅላላ የውጪ ምንዛሪ 10.1% ድርሻ ነበረው፡፡
  • የ2010 ዓ/ም የመንፈቅ ዓመት የኢትዮጵያ በውጭ ንግድ ገቢ2 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት ዕቅድ ተይዞ አፈፃፀሙ 1.35 ቢሊዮን ዶላር እንደሆነ ተገልፆል፡፡አፈፃፀሙ 61 መቶ የእቅድን እንደሆነ ያሳያል፡፡ ከዚህም ውስጥ የማዕድን ዘርፍ ወርቅ 59 ሚሊዮን ዶላር በውጭ ንግድ ገቢ እንዳስገኘ መረጃ ተገኝቶል፡፡ በሃገሪቱ ድንበር ዘለል ከፍተኛ የኮንትሮባንድ ንግድ በቁም እንሰሳት፣ ወርቅ፣ ቡና፣ ሰሊጥ፣ ጫት ወዘተ ምርቶች ወደ ጎረቤት አገራት እንደሚወጡ ታውቆል፡፡

ከወርቅ ማዕድን ኃብት ከውጪ ንግድ የተገኘው 620 ሚሊዮን ዶላር ወደ 209 ሚሊዮን ዶላር መውረድ ዋነኛ ምክንያት የወርቅ ማዕድኑ በኮንትሮባንድ በተለያዩ አጎራባቾች ሃገራት በኩል  መውጣት፣ ሚድሮክ፣ ኢዛናና የቻይና ኩባንያዎች የሚላከውን የወርቅ ምርት በመቀነስ የውጭ ምንዛሪውን ገቢ ውጪ በማስቀረት፣ራሳቸውን ተጠቃሚ በማድረግ የሃገርና የህዝብ ጥቅምን አስቀርተዋል፡፡ በብሄራዊ ባንክ ለዓለም ገበያ የሚቀርበው የወርቅ ምርት  በ2006ዓ/ም 12350 ኪሎ ግራም የነበረ ሲሆን፣ ቀስ በቀስ እያሽቆለቆለ በመሄድ በ2007ዓ/ም 9000ኪ/ግ፣ በ2009ዓ/ም 8580ኪ/ግ ወርቅ ለውጭ ገበያ ቀርቦ ተሸጦል፡፡ የወርቅ ማዕድን ኃብታችን የመቀነስ ሚስጢሩ የኮንትሮባንድ ንግድ ነው!!! መፍትሄው፣ኢትዮጵያ የማዕድን ኢንዱስትሪ ግልፅነት ኢኒሼቲቭ አባል እንድትሆን  የክልል መንግሥታትና ህዝብ መታገልና መጠየቅ አለበት፡፡ “በህይወቴ በዓለም ላይ ለሕዝብ ተጨንቆ ሲሰራ ያየሁት ሁለት መንግስት ብቻ ናቸው ፡እነሱም የኢትዮጵያና የሳኡዲ ዓረቢያ መንግስት ናቸው” ሸህ አላሙዲን ከሚሉ “በህይወቴ በዓለም ላይ በሙስና ተጨማልቆ  ሲሰራ ያየሁት ሁለት መንግስት ብቻ ናቸው፣እነሱም የኢትዮጵያና የሳኡዲ ዓረቢያ መንግስት ናቸው”ቢሉ ይሻላቸው ነበር።

‹‹ የወርቅ ባህላዊ አምራቾች፣ ለሃገሪቱ የወርቅ ወጪ ንግድ ከፍተኛ አስተዋፆኦ ካላቸው መካከል ባህላዊ አምራቾች ሰፊውን ድርሻ በመያዝ በዘርፉ እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ፡፡በየዓመቱ ለውጪ ገበያ ከሚቀርበው የወርቅ ምርት ውስጥ ከ60 በመቶ በላይ ድርሻ የሚይዘው በባህላዊ መንገድ የሚመረተው ወርቅ ሲሆን፣ ከ1.5 ሚሊዮን ያላነሱ ዜጎች በባህላዊ ወርቅ የማውጣት ሥራ ውስጥ በመሰማራት የህልውናቸው መሠረት ለመሆን ችሎል፡፡›› በባህላዊ መንገድ የሚመረተው የወርቅ ምርት በ2004ዓ/ም 8327.7 ኪሎ ግራም ወርቅ በባህላዊ መንገድ ተመርቶ ለብሄራዊ ባንክ ቀርቦ ነበር፡፡በመሆኑም 439.3 ሚሊን ዶላር የውጭ ምንዛሪ ተገኝቶበታል፡፡ ይህም በ2004ዓ/ም ከወርቅ ከተገኘው 620 ሚሊዮን ዶላር የውጪ ምንዛሪ ገቢ አኮያ ሲመዘን፣ በባህላዊ መንገድ ከሚመረተው የተገኘው ምርት የአብላጫውን ድርሻ ለመያዙ አመላካች ነው፡፡ ለወርቅ የውጪ ንግድ መቀነስ የኮንትሮባንድ ንግድ ነው፡፡ የብሄራዊ ባንክ በባህላዊ መንገድ ወርቅ በማምረት ለማዕከላዊ ገበያ የሚያቀርቡ ማህበራት ምርቱን ባቀረቡበት ዕለት ካለው የዓለም የወርቅ ዋጋ አምስት በመቶ ጭማሪ በማድረግ ግዥ ይፈፅማል፡፡ ይሁንና የኮንትሮባንድ ንግድ ሊገታ ባለመቻሉ፣ ወደ ማዕከላዊ ገበያ የሚመጣው የወርቅ መጠን በየጊዜው እንዲቀንስ አድርጎል፡፡  ከ2004 ዓ/ም ወዲህ የወርቅ ምርት እየቀነሰ ለመምጣቱ ከዓለም የወርቅ ዋጋ መውደቅ አንዱ ቢሆንም የወርቅ ምርቱን በመጨመር የውጭ ምንዛሪ ገቢን ከፍ ማድረግ ሲቻል፣ በአሁኑ ወቅት በባህላዊ መንገድ የሚመረተውም ሆነ በኩባንዎች በኩል ለዓለም ገበያ የሚቀርበው የወርቅ ምርት በአቅርቦት ደረጃ በእጅጉ ቅናሽ ማስመዝገቡን ቀጥሎል፡፡ የህወኃት የጦር አበጋዞች መንግሥት ጀነራል መኮንኖች በህገወጥ የድንበር ንግድ ዋነኛዎቹ አይነኬ ተዋናዮች በመሆናቸው እነሱን ከሥልጣን መንበራቸው መንቀል ግድ ይላል፣ ብሎም ኢትዮጵያ የማዕድን ኢንዱስትሪ ግልፅነት ኢኒሼቲቭ አባል እንድትሆን ማድረግ ነው፡፡

የኮንትሮባንድ የደም ገንዘብ!!!

‹‹የንግድ ሚኒስቴር የ2009 ዓ/ም የውጪ ንግድ አፈጻፀም የሚያሳየው ሪፖርት፣ወርቅ ብቻ ሳይሆን ከአጠቃላይ የማዕድን ዘርፍ የተገኘው ወጪ ንግድ ገቢ እጅግ ዝቅተኛ ነው፡፡ በ2009 በጀት ዓመት ከማዕድን ዘርፎች አንደሚገኝ ታቅዶ የነበረው የውጪ ምንዛሪ ገቢ መጠን 718.6 ሚሊዮን ዶላር ቢሆነም፣ በተጨባጭ የተገኘው ግን 231 ሚሊዩን ዶላር ብቻ እንደሆነ የንግድ ሚኒስቴር ሪፖርት አስፍሮል፡፡›› የቀድሞው የማእድን ሚኒስቴር የአሁኑ የማእድን፣የነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ሚስቴር አቶ ሞቱማ መቃሳ  በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ለቀረባላው ጥያቄ ‹‹ የወርቅ ኮንትሮንድ ንግድ እና በድንበር አካባቢ የሚወጣ ሕገወጥ የማዕድናት ዝውውር መስፋፋት አገሪቱ ከዘርፉ ማግኘት የሚገባትን ከፍተና ጥቅም እያሳጣት መሆኑን በቅርቡ ተገልፆል፤ ይሄን ለመከላከል ምን አይነት መፍትሄዎች እተወሰዱ ነው›› ሲመልሱ ‹‹አገሪቱ ከምታመርተው አጠቃላይ የወርቅ ሀብት 60 በመቶ የሚመረተው በባህላዊ አምራቾች በኩል ነው፡፡ ሕሁንና በባህላዊ መንገድ የተመረተወ ወርቅ በአግባቡ ወደ ብሄራዊ ባንክ እየቀረበ አይደለም፡፡ ምርቱ ቢኖርም በኮንትሮባንድ ንግድ እየወጣ ነው፡፡የባህላዊ ምርቱ የሚከናወንባቸው አምስት ክልሎች ኦሮሚ፣ ትግራይ፣ ቤኒሻንጉል፣ ደቡብ እና ጋምቤላ ናቸው፡፡ ወርቅ በብዛት የሚገኘውና የሚመረተው ጠረፍ በሆኑ አካባቢዎች ነው፡፡ ከእዚህ ጋር ተያይዞ የተመረተውን ምርት ወደ ባንክ ከማቅረብ ይልቅ ወደ ውጪ በኮንትሮባንድ የመሸጥ ሁኔታ ይታያል፡፡ ይሄንን ችግር ለመግታት አገራዊ ንቅናቄ ተጀምሮል፡፡ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመራ ኮሚቴ ተቆቁሞ እየሰራ ነው፡፡ የሁሉንም ትኩረትና ርብርብ ይጠይቃል፡፡ በተለይ ደግሞ የአካቢዎቹ አስተዳዳሪዎች መሰጠት የሚገባቸው ትኩረት ከፍተኛ መሆን ይገባዋል፡፡ አገሪቱ ማግኘት የሚገባትን የውጪ ምንዛሪ ሳታገኝ በህገወት መንገድ ወደ ውጭ የሚሄድበት ሁኔታ እየታየ ነው፡፡ ችግሩ በሚፈለገው ደረጃ እየተገታ አይደለም፡፡›› የብሄራዊ ባንክ ወርቅ የሚገዛው ከዓለም አቀፍ ዋጋ አምስት በመቶ ጭማሪ በማድረግ ሆኖ እያለ እንኮን ወርቁ በህገወጥ መንገድ ድንበር አቆርጦ መሸጡ ነጋዴዎቹ በጎረቤት ሃገራት ዶላር ለማሸሽና ማስቀመጥ ሲረዳቸው የሃገሪቱን የውጪ ምንዛሪ ገቢን በመቀነስ የሃገሪቱን የኢኮኖሚ እድገት በማደናቀፍና የህዝቡን ጉሮሮ በመዝጋት ላይ ይገኛሉ፡፡ ኢትዮጵያ በሰሜን ከኤርትር፣ በደቡብ ኬንያ፣ በምስራቅ ጅቡቲና ሶማሊያ፣ በሰሜን ምዕራብ ሱዳንና በስተ ደቡብ ምዕራብ ደግሞ ደቡብ ሱዳን ያዋሰኖታል፡፡ የህወሃት ጦር አበጋዞች መንግሥት፣ መከላከያ ሠራዊት ጀነራል መኮንኖች በዚህ ህገወጥ የድንበር የወርቅ ማዕድን ንግድ ግንባር ቀደሙን ሥራ በመስራት ወርቁን በዶላር በመሸጥ ዘረፋ ያከናውናሉ፡፡ የማእድን፣ የነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ሚስቴር ድኤታ አቶ ቴውድሮስ ገብረመድህን ከስር ሆነው በመዘወር ህወኃትን ድንበር ዘለል የወርቅ ንግድ  ያመቻቻሉ አሊያም ያስቆማሉ ተብሎ አይጠበቅም፡፡ መፍትሄው አንድና አንድ ብቻ ነው፣ኢትዮጵያ የማዕድን ኢንዱስትሪ ግልፅነት ኢኒሼቲቭ አባል እንድትሆን ማድረግ ብቻ ነው፡፡ 

ኢዛና ማዕድን ልማት ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማሕበር፣  በህወሃት/ ኢፈርት ባለቤትነት የተቆቆመ ካንፓኒ ሲሆን የህወሓት የጦር አበጋዞች መንግሥት  በትግራይ ክልል ውስጥ የተገኘውን 13 ቶን ወይም ፣13,000 ሸህ ኪሎ ግራም የወርቅ ማዕድን ለዓለም ዓቀፍ ጨረታ በማውጣት የካናዳዊያን የወርቅ ማዕድን ካንፖኒ ጋር ህወሃት/ኢፈርት በትግራይ ህዝብ ስም የሚዘረፈው የወርቅ ሃብት ነው፡፡ኢዛና ካንፓኒ 393.7 ሚሊዩን ብር የፕሮጀክት ወጪ 2017 ኪሎግራም ወርቅ በሁለት ዓመታት ውስጥ ለመማምረት አቅዶል፡፡በዚህ መሠረት 2017 ኪሎ ግራም ወርቅ 2,017,000 ግራም ወርቅ ይሆናል ይሄን ለ29 ግራም (1 ወቄት ማለት ነው) ስናካክለው 69,552 ወቄት ወርቅ ይሆናል ይሄን በ1 ወቄት ዋጋ 1218.80 ዶላር ስናባዛ 84,769,977.6 ሚሊዩን ዶላር ይሆናል በብር ስንቀይረው ደሞ በ20.34 ሲባዛ 1,724,221,344.384 ቢሊዩን ብር የህወሃት ጦር አበጋዞች በውጪ ሃገር ባንኮች ያከማቻሉ ማለት ነው፡፡

የማዕድን ኃብት(Mineral resource)

የህወሓት የጦር አበጋዞች መንግሥት፣ በትግራይ ክልላዊ መንግስት የገንዘብና ፕላን ቢሮ በነደፈው የእድገትና ትራንስፎርሜድን ፕላን (2010/11-2014/15) በገፅ 17 መሠረት፤ ከ1999 እኤአ ጀምሮ፤በትግራይ ክልል አጠቃላይ፤የስነ-ምድር ካርታ ጥናት መሠረት፤በዓይነት፣ በሚሸፍነውና በመጠኑ የክልሉን የማዕድን ኃብቶች መለየት ተችሎል፡፡ እስካሁን የስነ-ምድር ካርታ ጥናት እንቅስቃሴ  መረጃ መሠረት 24,780 ሜትር ስኮይር የስነ-ምድር ጥናት ተጠንቶና ተጠናቅሮ ሪፖረቱ ለማቅረብ በዝግጅት ላይ ነው፡፡ በትግራይ ክልል የስነ-ምድር ካርታ ጥናት ስብስብ መረጃ 46.2%  ደርሶል፤እናም ክልሉ 850 ኪሎ ግራም ወርቅ በኢትዩጵያ ብሄራዊ ባንክ ተቀማጭ አድርጎል፡፡ በዚህም ረገድ፤ የተወሰኑ ድክመቶች ስላሉ አስፈላጊው ትኩረት ሊደረግላቸው ከሚገቡት መኃል፤ የሰለጠነ የሰው ኃይል ልማት፣ የመመርመሪያ መሣሪያዎችና የላብራቶሪ አገልግሎቶች ማሞላትና ሌሎቹም ነጥቦች ይጠቀሳሉ፡፡ በዚህ መሠረት 850 ኪሎ ግራም ወርቅ 850,000 ግራም ወርቅ ይሆናል ይሄን ለ29 ግራም (1 ወቄት ማለት ነው) ስናካክለው 29,310 ወቄት ወርቅ ይሆናል ይሄን በ1 ወቄት ዋጋ 1,218.80 ዶላር ስናባዛ 35,773,448 ሚሊዩን ዶላር ይሆናል በብር ስንቀይረው ደሞ በ20.34 ሲባዛ 726,768,548.7 የህወሃት ጦር አበጋዞች በብሄራዊ ባንክ አከማችተዋል ማለት ነው፡፡ ዝርዝሩን ከድረ-ገፁ ያንብቡ፡፡ የትግራይ ክልላዊ መንግስት እድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ (2010/11- 2014/15) ‹‹Since 1999, geological map survey has been conducted so as to identify the type, coverage and amount of mineral resources in our region. Up to now, the activities of collecting geological information from 24,780 meter square and consolidating reports have been finalized. The geological map coverage of our region has reached 46.2% and around 850 kg gold is already deposited in the national bank of Ethiopia. In this regard, there were some limitations which need due attention such as fulfilling enough skilled manpower and inspecting equipments and laboratory services among others.›› (Tigray Regional State, Five Years 2010/11-2014/15, Growth & Transformation Plan, Bureau of Plan and Finance, September 2003 E.C, Mekelle, page 17)

ኢዛና ወርቅ ከሜድሮክ ወርቅ ካንፖኒ የጠበቀ ሸርክና እንዳላቸው ይታወቃል፡፡ የህወሃት መንግስት  በትግራይ ህዝብ ጭምር አንቅሮ ተፍቶታል፡፡ ኢዛና የማዕድን ኃብት በ1993እኤአ ሲመሠረት በ1.4 ቢሊዩን ብር መነሻ ካፒታል ነበር፡፡ ካንፓኒው በ 17.8 ሚሊዩን ዩኤስ ዶላር የወርቅ መዕድን ማውጫ ፋብሪካ በቱርክ ማንሃተን ኮርፖሬሽን ተገነባ፡፡ ኢዛና የወርቅ መዕድን ማውጫ ፋብሪካ ሲገነባ ለአራት ዓለም ዓቀፍ ኮንትራክተሮች ጨረታ ወጥቶ የተሠጠ ሲሆን የአዶላና የለገደንቢ በዓለም ዓቀፍ ጨረታ ሳይወጣ ያለጨረታ ለሼክ አላሙዲ መሸጡ ምን ያባላል!!! ህወሃት  በኢትዩጵያ  ህዝብ ላይ የሚሠራው ግፍና ደባ ለምን ይሆን!!! ህዝቡን ከድህነት አረንቆ አወጣለሁ እያለ ሲምል ሲገዘት 26 አመታት ተቆጠረ፡፡የህወሃት የፖለቲካ ካድሬዎች፣ የመለስና የስዬ የጦር አበጋዞች ለሼክ አላሙዲን የተሸጠውን የወርቅ መዕድንን በተመለከተ፤ ይሄን ሞልቶ የፈሠስ የግፍ ፅዋ ሞልቶ ፈሰሰና ሸኩ ሳውዲ አረቢያ በሙስና ወንጀል ዘብጥያ ወረዱ፡፡ የኢትዮጵያ አምላክ!!! የኢትዬጵያ  ፌዴራል ዲሞክራቲክ ሪፕብሊክ የማዕድንና ኢነርጂ ሚኒስትር የለገደንቢ የወርቅ ማዕድን የሃያ ዓመት ውል አልቆል፡፡ ለህዝብ ይመለስ የወጣቶች ዋነኛ ጥያቄ ነው፡፡ የአሜሪካን ድምፅ ሬዲዩ (ቪኦኤ)፣ የጀርመን ድምፅ ሬዲዩ (ዶቼቬሌ)፣ የኢትዬፕያ ሳተላይትና ቴሌቪዝን (ኢሳት)ና ሌሎችም በሬዲዩና ቴሌቪዝን ስርጭታችሁ ይህን ድብቅ ሚስጥር የለገደንቢ የወርቅ ማዕድን የሃያ ዓመት ውል ማለቁንና ምን ደረጃ ላይ እንዳለ  እንድትመረምሩ አደራ እንላለን!!!  የብዙ ኢትዩጵያዊያን ጥያቄ መሆኑን ስንገልፅላችሁ የህሊና ፍርድ ለእናንተው በመተው ነው፡፡ ሼክ አላሙዲን ሢሦ መንግስት አክትሞል!!! የወያኔ ኢፈርትና ሜድሮክ የንግድ ሽርክና ሙስና ግብዓተ መሬታቸው አንድ ቀን ነው፡፡ ይሄን የሚጠራጠር ካለ የኢትዩጵያ ኢኮኖሚ፣ የፌዴራልና ክልሎች መንግስታዊ ኢንተርፕራይዞች፣ ማለትም የትግራዩ ኢፈርት፣ የአማራው ጥረት፣ የኦሮሞው ዲንሾ፣ የደቡቡ ወንዶ እንዲሁም የህወኃት ሜቴክ፣ የህወኃትና የሼክ መሃመድ የሽርካ ሜድሮክ የቢዝነስ ሞኖፖሊ 90 በመቶ በላይ ኃብት መያዛቸውን ልብ ሊሉ ይገባል!!! እነዚህ ድርጅቶች የመንግስት ግብር ባለመክፈል የኢትዩጵያን ኢኮኖሚና ህዝብ መቀመቅ የከተቱ የማፍያ ቡድኖች ናቸውና፡፡ ያለ ኢኮኖሚ ነፃነት የፖለቲካ ነፃነት የለም!!!

{2} ከኢትዩጵያ ድንበር ዘለል የቁም እንስሳት ንግድ፣

ከኢትዩጵያ ከመካከላኛው ምስራቅ አገራቶች አንፃር በቁም እንስሳትና የሥጋ ውጤቶች  ንግድ ትልቅ ጥቅምና ብልጭ ያላት ሃገር ስትሆን የቆላማው ዝርያ በተለይም የቦረና በሬና የሱማሌ ጥቁር ጭንቅላት ያላቸው በጎች ዝርያ በብዙ ደንበኞች ተወዳጅ ናቸው፡፡ ወደ ውጪ የሚላኩ 1.6 ሚሊዩን የቁም እንስሳት በአመት ወደ ባህር ማዶ አገራት በተለይም የገልፍ አገራትና ግብፅ ይላካል፡፡ የሚገርመው ታዲያ ከዚህ ውስጥ 1.4 ሚሊዩን የቁም እንሰሳት ህገወጥ በሆነ መንገድ ከሃገራችን እንደሚወጣ ጥናቱ ያረጋግጣል፡፡የህወሃት የጦር አበጋዞች መንግስት  በትግራይ፣በአማራ፣ በኦሮሚያ፣ በሱማሊያ በደቡብ ክልሎች በኩል ከኢትዩጵያ ድንበር ዘለል የቁም እንስሳት ንግድ ወደ ሱዳን፣ ሱማሊያ፣ ጅቡቲ፣ ኬንያና ኤርትራ በመላክና በመሸጥ ዳጎስ ያለ የውጭ ምንዛሪ ዶላር፣ የትግራዩ ኢፈርትና ሜቴክ፣ የአማራው ጥረት፣ የኦሮሞው ዲንሾ፣ የደቡቡ ወንዶ እንዲሁም፣የሼክ መሃመድ  ሜድሮክ የቢዝነስ ሞኖፖሊ በውጭ ሃገራት ባንኮች የዘረፈውን ያስቀምጣል፡፡ የቁም እንሰሳት፣ሃገሪቱ አንጡራ ኃብት በህገወጥ መንገድ የቁም እንሰሳት፣በተለያዩ ክልሎች በድንበር በኩል ወደ፣ሱዳን፣ሱማሊያ፣ ኬንያና፣ጅቡቲ በኩል ከአገር እንደሚወጡና በከፍተኛ ዋጋ በውጪ ምንዛሪ ይሸጣሉ፡፡ በቁም እንሰሳት ድንበር ዘለል ህገወጥ ንግድ ውስጥ የክልሎች ሹማምንትና ጀነራል መኮንኖች፣የፖለቲካ ካድሬዎች እንዲሁም የቢዝነስ ድርጅቶች፣የትግራዩ ኢፈርትና ሜቴክ፣ የአማራው ጥረት፣ የኦሮሞው ዲንሾ፣ የደቡቡ ወንዶ፣   የሼክ መሃመድ ሜድሮክ እጅ እንዳለበት ይታወቃል፡፡ ‹‹የውጪ ንግድ- ከርሞም ጥጃ›› (አዲስ ዘመን የካቲት 7 ቀን 2009 ዓ/ም) ኢትዩጵያ በዓለም የእንሰሳት ሃብት 10ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡ በአፍሪካም የቁም እንሰሳትን ለውጭ ገበያ በማቅረብ ትልቁን ድርሻ ትይዛለች፡፡ ሶማሊያ፣ ጂቡቲ፣ ኬንያ፣ ሱዳንና ሳውዲ ዓረቢያ የቁም እንሰሳት የምትልክባቸው ሃገሮች ናቸው፡፡

ኢትዩጵያ ከቁም እንሰሳ ንግድ በ2003 ዓ/ም 147.88 ሚሊዮን ዶላር፣ በ2003 ዓ/ም 147.88 ሚሊዮን ዶላር፣   በ2004 ዓ/ም 207.12 ሚሊዮን ዶላር፣   በ2005 ዓ/ም 166.40 ሚሊዮን ዶላር፣   በ2006 ዓ/ም 186.68 ሚሊዮን ዶላር፣   በ2007 ዓ/ም 148.51 ሚሊዮን ዶላር፣ በ2008 ዓ/ም 147.80 ሚሊዩን ዶላር አግኝታለች 535 ሽህ በላይ የቁም እንሰሳት ለውጪ ገበያ በመላክ ፡፡ በ2009 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት የተገኘው ገቢ 36 ሚሊዩን 360 ሽህ ዶላር መሆኑ ታውቆል፡፡ ከቁም እንስሳት የውጪ ንግድ የሚጠበቀው የውጪ ምንዛሪ ተግዳሮቶች መኃል በዋናነት የሚጠቀሱት ውስጥ፣ መንግሥት ህገወት የቁም እንሰሳት ንግድን መቆጣጠር ባለቻሉ፣ ከብቶቹ በተለያዩ ክልሎች ድንበር በኩል፣ በሱዳን፣ ሱማሊያ፣ ኬንያና፣ ጅቡቲ በኩል በህገ-ወጥ መንገድ በእግር እየተነዱ ከአገር እንደሚወጡና በከፍተኛ ዋጋ በውጪ ምንዛሪ ይሸጣሉ፡፡

በ2008 ዓ/ም ብቻ የቁም እንሰሳት፣በኮንትሮባንድ ንግድ ከአገር ሊወጡ ሲሉ የተያዙ የቁም እንሰሳት ውስጥ  1,800,330 ሚሊዮን ግመሎች፣ 6,250 ፍየሎች፣ 536,226 በጎች፣ 3,450,925 የቀንድ ከብቶች ናቸው፡፡ በ2008 ዓ/ም ብቻ  በኮንትሮባንድ ንግድ ከአገር ሊወጡ ሲሉ የተያዙ ጠቅላላ የቁም እንሰሳት ብዛት 5,793,731 ናቸው፡፡( ምንጭ፣የካቲት 7 ቀን 2009ዓ/ም አዲስ ዘመን ጋዜጣ)

ህወሓት የጦር አበጋዞች መንግሥት በ2008 ዓ/ም ብቻ የቁም እንሰሳት፣ በኮንትሮባንድ ንግድ ከአገር ሊወጡ ሲሉ 5,793,731 (አምስት ሚሊዩን 793 ሽህ 731) እንደተያዙ ሲገለፅ፣ በአገራችን መንግሥት አለ ለማለት አያስደፍርም፡፡ በኮንትሮባንድ የተያዙት ቁጥር ይሄን ከአከለ ሳይያዙ ድንበር የተሻግረው የተሸጡት ቁጥር ከዚህ በትንሹ ሁለት ዕጥፍ እንደሚሆን መገመት ይቻላል፡፡ ሌላው በመረጃው ያልተገለፀው ከየት ክልል ምን ያህል የቁም እንሰሳት ወደ የትኛው ጎረቤት አገር የሚለው አሃዝ ቢታወቅ ጥሩ ነበር፡፡ የኮንትሮባንዱ ንግዱ ዋናው ምክንያት የውጪ ምንዛሪ ዶላር ለማግኘት እንደሆነ ምንም ጥርጥር የለውም፡፡ ህወሓት የጦር አበጋዞች መንግሥት ‹‹ጀነራል መኮንኖች›› እና የትግራይ ክልል መንግሥት በሱማሊያ፣ በደቡብ ሱዳን፣ ሱዳን፣ ጅቡቲ፣ ኬንያ በኩል የቁም እንስሳት ንግድ ላይ ዋነኛዎቹ ተሳታፊዎች በመሆናቸው ኮንትሮባንድ ንግዱን ማስቆም አይቻልም፡፡ ‹‹በኢትዩጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን የግብር ከፋዩች ንግድና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ፋሲካ በላይ እንደሚሉትም፤የኮንትሮባንድ ገቢና ወጪ ንግድ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቶል፡፡ ሁኔታው በቅባት እህሎች፣በጫት ንግድ እንዲሁም በቁም እንሰሳትና በሌሎችም ዘርፎች ላይ ጎልቶ ይንጸባረቃል፡፡››      

ሱዳን ከኢትዩጵያ ድንበር ዘለል የቁም እንስሳት ንግድ ድርሻ

ከኢትዩጵያ ከመካከላኛው ምስራቅ አገራቶች አንፃር በቁም እንስሳትና የሥጋ ውጤቶች  ንግድ ትልቅ ጥቅምና ብልጫ ያላት ሃገር ስትሆን የቆላማው ዝርያ በተለይም የቦረና በሬና የሱማሌ ጥቁር ጭንቅላት ያላቸው በጎች ዝርያ በብዙ ደንበኞች ተወዳጅ ናቸው፡፡ ወደ ውጪ የሚላኩ 1.6 ሚሊዩን የቁም እንስሳት በአመት ወደ ባህር ማዶ ገገራት በተለይም የገልፍ አገራትና ግብፅ ይላካል፡፡ የሚገርመው ታዲያ ከዚህ ውስጥ 1.4 ሚሊዩን የቁም እንሰሳት ህገወጥ በሆነ መንገድ ከሃገራችን እንደሚወጣ ጥናቱ ያረጋግጣል፡፡የህወሃት የጦር አበጋዞች መንግስት  በትግራይ፣በአማራ፣ በኦሮሚያ፣ በሱማሊያ በደቡብ ክልሎች በኩል ከኢትዩጵያ ድንበር ዘለል የቁም እንስሳት ንግድ ወደ ሱዳን፣ ሱማሊያ፣ ጅቡቲ፣ ኬንያና ኤርትራ በመላክና በመሸጥ ዳጎስ ያለ የውጭ ምንዛሪ ዶላር በውጭ ሃገራት ባንኮች የዘረፈውን ያስቀምጣል፡፡

በተለይ በአማራ ክልል በኩል ወደ ሱዳን የቁም እንሰሳቶች በድንበር በኩል ይሸጣሉ፡፡በ2007 እኤአ 100000 (መቶ ሽህ) ቁም ከብቶች በህጋዊና ህገ ወጥ መንገዶች ድንበር ተሸግረው ተሸጠዋል፡፡ ከዚህ ውስጥ 40 በመቶ ሚሆነው በህጋዊ መንገድ በውጪ ንግድ በኩል የተሸጡ ሲሆኑ 60 በመቶው በህገወጥ መንገድ የተከናወነ ንግድ ነበር፡፡ በ2005እኤአ 50 በመቶ  ህጋዊውና የህገወጡ የውጪ ንግድ ድርሻ ነበራቸው፡፡ 90 በመቶ የሚሆነውን የቁም እንሰሳት የውጪ ንግድ የሚያከናውኑት አርቢዎቹ ሲሆኑ ከኢትዩጵያ ድንበር ወደ ሱዳን ሀገር ወስደው በኢትዩጵያ ብር ይሸጣሉ፡፡ የሱዳን የገቢ ንግድ ነጋዴዎች ወደ ኢትዩጵያ መጥተው በዶለር የቁም ከብቶች ገዝተዉ ይመለሳሉ፡፡ በአማራ ክልል የውጪ ንግድ ቀረጥ ለሱዳን ነጋዴዎች የለም፡፡ በሌላ በኩል በሱዳን በኩል ከፍተኛ የቁም ከብቶች ቀረጥ ማለትም 400 ብር በአንድ ከብት የሱዳን መንግስት የኢትዩጵያን ነጋዴዎች ግብር ያስከፍላል፡፡ ህወሃት የጦር አበጋዞች በዚህ ሕገወጥ ድንበር ዘለል የቁም እንሰሳቶች የውጪ ንግድ ተጠቃሚዎች በመሆን ዳጎስ ያለ በመቶ ሚሊዩን የአሜሪካ ዶላር ሃገሪቱ ኪሳራ ደርሶባታል፡፡ የጦር አበጋዞች  በውጭ ሃገራቶች ዶለር በማስቀመጥና የሃገሪቱን የውጭ ንግድና የውጪ ምንዛሪ በመዝረፍ ስራ ላይ በመሳተፍ ሃገራችንና ህዝብን ለርሃብ ለበሽታና ለስደት መዳረጋቸውን ጥናቱ ይጠቁማል፡፡ በተረፈ ከድህረ-ገፁ ቀሪውን ያንብቡ፡፡  Challenges to Ethiopia’s cattle and beef chain By Carina PerkinsCarina Perkins, 04-Jul-2013

የቁም እንሰሳት፣ኢትዩጵያ ከቁም እንሰሳ ንግድ በ2008 ዓ/ም ከ535 ሽህ በላይ የቁም እንሰሳት ለውጪ ገበያ በመላክ 148 ሚሊን ዶላር አግኝታለች፡፡ በ2009 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት የተገኘው ገቢ 36 ሚሊዩን 360 ሽህ ዶላር መሆኑ ታውቆል፡፡ የወያኔ የጦር አበጋዞች መንግሥት ህገወት የቁም እንሰሳት ንግድን ውስጥ በመሳተፍ ከፍተኛ ገቢ ያገኛል፡፡ ከብቶቹ በተለያዩ ክልሎች ድንበር በኩል፣በሱዳን፣ሱማሊያ፣ ኬንያና፣ጅቡቲ በኩል በእግር እየተነዱ ከአገር እንደሚወጡና በዚህ ድንበር ዘለል በህገ-ወጥ ንግድ ህወኃት ከፍተኛ ዶላር ያገኛል፡፡

ህወሓት የጦር አበጋዞች መንግሥት በ2008 ዓ/ም ብቻ የቁም እንሰሳት፣ በኮንትሮባንድ ንግድ ከአገር ሊወጡ ሲሉ 5,793,731 (አምስት ሚሊዩን 793 ሽህ 731) እንደተያዙ ሲገለፅ፣ በአገራችን መንግሥት አለ ለማለት አያስደፍርም፡፡ የኮንትሮባንዱ ንግዱ ዋናው ምክንያት የውጪ ምንዛሪ ዶላር ለማግኘት እንደሆነ ምንም ጥርጥር የለውም፡፡ ህወሓት የጦር አበጋዞች መንግሥት ‹‹ጀነራል መኮንኖች›› እና የትግራይ ክልል መንግሥት በሱማሊያ፣ በደቡብ ሱዳን፣ ሱዳን፣ ጅቡቲ፣ ኬንያ በኩል የቁም እንስሳት ንግድ፣ ወርቅ መዕድን ንግድ፣ የግብርና ምርቶች ንግድ፣ የጫት ንግድ፣የቅባት እህሎች ንግድ ላይ ዋነኛዎቹ ተሳታፊዎች በመሆናቸው በኮንትሮባንድ ንግድ ፎቅ ይገነባሉ፡፡ በኢትዩጵያ የኮንትሮባንድ ገቢና ወጪ ንግድ ከጊዜ ወደ ጊዜ ዘረፋው እየጨመረ መጥቶል፡፡

{3} የፋይናንስ ዘርፍ፣ በሃገሪቱ ህግና ደንብ መሠረት ባንኮች የሚቋቋሙት በባለ አክሲዩኖች ሲሆን ከዘር፣ ከሃይማኖትና ከፖለቲካ ነፃ ሆነው የህዝብ አገልጋይ እንዲሆኑ ነው፡፡ የፖለቲካ ፓርቲዎች በንግድ ዘርፍ ውስጥ መሳተፍ እንደሌለባቸው የኢትዩጵያ ህገ-መንግሥት ደንግጎል፡፡ ከህወሓት/ኢህአዴግ የፖለቲካ ፓርቲዎች በኢትዩጵያ ኢኮኖሚን የፋይናንስ ዘርፍ በመቆጣጠር  ፓርቲዎች የሃገሪቱን ባንኮችና ኢንሹራንሶች 75 በመቶ ኃብት ድርሻ ይዘዋል፡፡ በግሉ ዘርፍ ኢኮኖሚ የፋይናንስ ባንክና ኢንሹራንስ ዘርፍ ውስጥ፤ ያላቸውን ድርሻ እንቃኛለን፡-ህዝባዊ ወያኔ ሃርነነት ትግራይ (ህወኃት) ንብረት የሆነው የትግራዩ ኢፈርት፣ ወጋገን ባንክ፣ ፀሃይ ኢንሹራንስ፣አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ፣ ንብ ኢንሹራንስ፣ እናት ባንክ፣ ናሽናል ኢንሹራንስ ይገኙበታል፡፡የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) ንብረት የሆነው የአማራው ጥረት አባይ ባንክ፣ አባይ ኢንሹራንስ፣የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦሕዴድ) ንብረት የሆነው የኦሮሚያው ቱምሳ የኦሮሚያ ህብረት ባንክ፣ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ፣የደቡብ ኢትዩጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ለደኢሕዴግ) ንብረት የሆነው የደቡቡ ወንዶ ደቡብ ግሎባል ባንክ፣ ሉሲ ኢንሹራንስ በሚል ስያሜ የሃገሪቱን የባንክና ኢንሹራንስ ድርጅቶችን ተቆጣጠረዋል፡፡ እነዚህ ከህወሓት/ኢህአዴግ ፓርቲዎች ንብረት የሆኑ የአውራው ፓርቲ የባንክና ኢንሹራንስ ድርጅቶች የኢትጵያን ብሄራዊ ባንክ በማዘዝ የኢትዩጵያ ንግድ ባንክ፣ የኢትዩጵያ ልማት ባንክ፣ የኮንስትራክሽን ቢዝነስ ባንክ ተቆጣጥረው ለከፍተኛ ኪሳራ ዳርገዋል፡፡ በኮንትሮባንድ፣የደም ገንዘብ የሰከሩ አይነኬ የህወሓት ጀነራሎች ይወገዱ!!!!!!

የፋይናንስ ዘርፍ፣ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በጋምቤላ ክልል በግል አልሚዎች ለተጀመሩ ሰፋፊ እርሻዎች በለቀቀው ከፍተኛ መጠን ያለው ብድር መመለስ ባለመቻሉ ምክንት፣ 8.6 ቢሊዮን ብር  መሰብሰብ አልቻለም፡፡ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ መመሪያ፣ አንድ ባንክ የተበላሸ ብድር መጠን ከአጠቃላይ ብድሩ 5 በመቶ ሊበልጥ እንደማይችል ቢደነግግም፣ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የተበላሸ ብድር ክምችት ከአጠቃላ ብድሩ 25.3 በመቶ መድረሱ ታውቆል፡፡ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በዚህ ምክንያት ከሥሮል፡፡ የኢትዩጵያ ልማት ባንክ፣ ከግብርና ኢንቨስትመንት ጋር በተያያዘ ከሁለቱ ባንኮች በድምሩ 4.27 ቢሊዩን ብር ለ200 ያህል ቦዘኔ ባለሃብቶች ተዘርፎል፡፡ 12 ከንግድ ባንክ የተበደሩ ሲሆን 188 ከልማት ባንክ መበደራቸው ታውቆል፡፡ ‹‹ሰባቱ ኮኮቦች›› ተብለው የሚታወቁት የቀን ጅቦች

{1}ጄኔራል ዩሐንስ ዓለም ሠገድ፣

{2}ሻለቃ አዕምሮ ገብረክርስቶስ፣

{3}ሻለቃ ኪዱ ጣዕመ

{4}ኮማንደር ሙሉ ሁሉፍ፣

{5}ካማንደር ትርሃስ ገብረ ዩሃንስና

{6}አቶ ሳለእግዚአብሄር በርሄ

አንድ መቶ አስራሦስት (113000000) ሚሊዩን ብር ከባንክ ተበድረው የጋምቤላን መሬት ተቀራምተው ምንም ሳያለሙ በጨበጣ ገንዘቡን ዘርፈው በአዲስ አበባ መሬት እየገዙ በመሸጥ ንግድ መሰማራታቸው ተረጋግጦል፡፡ አብዛኛዎቹ በሙስና ተዘፍቀው የሚገኙት የመከላከያ ሠራዊት ከፍተኛ ባለሥልጣኖች እንደሆኑና ከህግ በላይ በመሆናቸው፣ማንም ጠያቂ እንደሌለ በጥናት ተረጋግጦል፡፡  በአበባ እርሻ ልማት ስም ለ80 ቦዘኔ ባለሃብቶች 800 ሚሊዩን ብር ብድር ተሰጥቶ ተዘርፎል፡፡ በ2008 እና በ2009 ዓ/ም ላይ በሃገሪቱ በተከሰተው የህዝብ እንቢተኛነትና ተጋድሎ የወደሙ የውጪና የሃገር ውስጥ ባለሃብቶች ፋብሪካዎች፣ እርሻዎች፣ የጭነት መኪኖች፣ ወዘተ በብዙ መቶ ሚሊዩን ብር ሚቆጠር ገንዘብ በመንግሥት ግምት 20 ሚሊዩን ዶላር መንግሥት ካሳ እንዲከፍላቸው በህግ ጠይቀዋል፡፡ ይህም የካሣ ጥያቄ ካልተፈፀመ ሃገሪቱ ለኢንቨስትመንት ምቹ ካልሆኑ ሀገራት ተርታ መፈረጆ አይቀሬ ነው፡፡ የልማት ባንክ ፕሬዚዳንት የነበሩት አቶ ኢሳያስ ባህረ፣ ምክትል ፕሬዜዳንት ወ/ሮ መሠንት ሸንቁጤ እና የብድር አገልግሎት አቶ ገነነ ሩጋ፣የኮርፖሬት አገልግሎት ሃላፊ አቶ ግርማ ወርቄ ወዘተ ከአገር ወጥተው ኮብልለዋል፡፡ የኢትዮጵ ልማት ባንክ በጋምቤላ ለሰፋፊ እርሻዎች ለሰጠው ብድር 8.6 ቢሊዮን ብር  ተጠያቂ የሆነ ማንም ሰው የለ!!! የእንዚህ ባለኃብቶች የነፍስ አባት ወያኔ ስለሆነ ማንም አይነካቸው፣የህጋ የበላይነታ አይሰራም፡፡ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ገዥዎች በሃገሪቱ የባንክ ታሪክ ሙያቸውን ያረከሱ፣    ላሜራ ብረት ወርቅ ብለው የተቀበሉ ሙሰኛ የወያኔ ካድሬዎች የሽርክና ሥራ በመሆኑ ማንም አይጠየቅ፡፡  ከኢትዩጵያ ልማት ባንክ ብድር የወሰዱ የትዕምት ኩባንዎች ከህዳር 2002 ዓ/ም ጀምሮ ብድር በመውስድና ባለመክፈል የሚታወቁ ኩባንያዎች ናቸው፡፡ በኢትዩጵያ የፋያናንሻል ዘርፍ መረጃ ርሃብ አንዱ የሙስና ገጽታ ነው፡፡ በመንግሥት ደረጃ፣ የሚከወን ሙስና ለአንድ ዘውግ ያለ አድሎ፣ ያልተስተካከለ የክልሎች የፋይናንስ አቅርቦት ማመቻቸት ብሎም በህወሓት/ኢህአዴግ መንግሥት ለብሄራዊ ባንክ ትዕዛዝ ለኢፈርት ኩባንያዎች የተደረገ የእዳ ስረዛ ጊዜ ያወጣዋል፡፡ ለዚህ ነው በኢትጵያ ያሉ ባንኮች ተዘርፈው ለኪሣራ ከተዳረጉ ዓመታት ተቆጥሮል፡፡   

በኢትጵያ ምድር የህግ ሉዓላዊነት ይከበር!!! የህገውጥ ኮንትሮባንዲስቶችን በዘር ፖለቲካ አይጠለሉ!!! የኦሮሞና ክልል መሪዎች አቶ ለማ መገርሳና ዶክተር አብይ እንዲሁም የአማራ ክልል አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የወያኔን ህገወጥ ኮንትሮባንዲስቶችን ለህግ ማቅረብ ህዝባዊ ሃላፊነት አለባቸው!!!

የኦሮሞ ቄሮዎችና የአማራ ፋኖዎች ከጎናቸሁ አሉ እስከመሰዋትነት ድረስ!!!

ምንጭ

{1} ጥር 30 ቀን 2010ዓ/ም አዲስ ዘመን ጋዜጣ

{2} For more information on EITI, visit: www.eiti.org.  Download: EITI_factsheet-1.jpg (55kb) EITI_factsheet-2.jpg (92kb)

{3} ፖርተር ሚያዝያ 8 ቀን 2009 ዓ/ም

{4} ጳጉሜ 4 ቀን 2007 ዓ/ም

{5} መስከረም 23 ቀን 2008ዓ/ም

2017-10-09{6} http:www.globalmeatnews.com/Industry-Markets/Challenges-to-Ethiopia-s-cattle-and-beef-chain