እንደምን ነህ ዘርማ (በግርማ ቢረጋ )

0

ወሄ ነህ ወይ ዘርማ አንተ ትኩስ ወጣት፣

ታውቃለህ በጥሩ ዘረኞችን መቅጣት ።

ቢነኩህ አቃጣይ እሳት ፍም የምትሆን፣

አጋር ተባባሪ የቆምከው ለወገን።

የፋኖ እና ቄሮን ፈለግ ተከትለህ፣

አሳየው እንግዲህ ማንበርከክ ታውቃለህ።

ወሄ ነህ ወይ አንተ ሰላም ነህ ወይ ዘርማ ፣

ከአጥፊ ከዘረኞች ቆመህ ላትስማማ፣

ፍትህ ነፀነትን ደርበህ እንደ ሸማ ፣

እኔስ ቀናውብህ ወሄ ነህ ወይ ዘርማ ።

ታግሰህ ብትተወው የፈራህ መስሏቸው

ጉመርስ ምን አለ መደፈሩን ሲያውቀው ፣

ለባንዶች አጎብዳጅ ሆኖ የማያውቀው።

ይኸው አሳየኸው ቀና ብለህ ዘርማ፣

ከገዳዮች ጋራ ቆመህ ላትስማማ፣

ሞቅ ደመቅ አሉ አረቅጥም ቸሃ ፣

ዘርማ ነብስ ዘራበት ሊሰራ ነው ስራ።

መስቃን እና ምሁር ምን ብለው አወሩ፣

ወትሮም ልምዳቸው ነው ጠላት ማሸበሩ ።

እውነት ነው ወይ ዘርማ ነብር እንደ ፋኖ፣

እውነት ነው ዘርማ አንበሳ እንደ ቄሮ።

በፍቅር ከሆነ ሁሉንም አክባሪ

እምድብር ነው አሉ ጠላት አሸባሪ።

የጌታ ጀፎሮስ እንዴት ሆኖ ይሆን ፣

አውቃለው ምን ጊዜም አብሮህ እንደሚሆን፣

ዘርማ በሄደበት የሃገር አድባር ይሁን።

እንደጋኝ ሰምቷል ወይ ምንስ አለ እነሞር፣

ሁሌም ልምዱ ያለው ድልን የሚያበስር ።

እዣ መስቃን ሶዶ እንደው የሰሙ ለት ፣

የወያኔው ጓዳ በቃ አለቀለት ።

ቢሆንም ቢሆንም  ልጠይቅህ ብቻ፣

እንዴት ሆኖ ነበር ያላቻው ጋብቻ።

ከነካኩህማ ታውቃለህ ሰው መቅበር፣

ኢነር ሰው ጠፋ ወይ ከአትንኩኝ ባይ መንደር።

ወሄ ዘበር ዘርማ ይታያል ከፊቱ፣

ባንተ ክፉ ያሰበ አረ የት አባቱ።

ካንተ ጋር ቆመ ወይ እዣ ምንስ አለ፣

እሱም አወቀ ወይ እንደ ተታለለ ።

እንዴት ከርሟል ጉመር እንዴት ነው ወልቂጤ ፣

እንዴትስ አሰበ ምን አለህስ ስልጤ።

ቸሃስ ምን ተሰማ አብሮህ ቆሟል ወይ፣

ለሌላው የሚተርፍ ተዉ አትንኩኝ ባይ።

ይሁን መልካም ጊዜ ይንመንዳ ኬር ዘበር፣

የነፃነት ብርሃን ተስፋ ሆኖ የማይቀር ፣

ኬር ዘበር ያምንደ ወሄ ዘበር ይምጣ፣

ኢትዮጵያችን ትኑር ጠላታችን ይውጣ።

ፌብሩዋሪ 2018

ስቶክሆልም / ስዊድን