ቁጭት ቂም ጥላቻ ( ግርማ ቢረጋ )

0

ወደሽ ነው ገጣቢት ትለቂያለሽ በቃ፣

በዘር መመካትሽ ላይሆንሽ ጠበቃ፣።

ወደሽም አይደለ በግድ  ትለቂያለሽ ።

ልብሽም አውቆታል  ቀኑ እንደመሸብሽ ።

የጥይት ጋጋታ ላያስጥል ጋብቻ ፣

ማስተዋል አቅቶሽ ተኮፍሰሽ ብቻ ።

ላያዋጣሽ ነገር የመን ላይ ተሻግረሸ፣

ዶላርሽን ሰጥተሽ የገዛሽው ሃበሽ፣።

መስሎሽ ነበር አንቺ ሁሉም ያለቀለት፣

እሱ ሆኖ ሳለ  የሃገር ሃብት ኩራት ፣

መሞኘትሽ በዛ ተጫወትሽው በእሳት፣

ከልክ በላይ በልተሽ ያገሳሻል ብስናት።

በይ ቀጥይ ጨርሽ ገና ይቀርሻል ፣

የጀግኖቹን ጀግና አንድዬን ይዘሻል፣

ጉያሽ ስር ተቀምጦ ይቆጠቁጥሻል ፣

ገና ደም አለብሽ ገና ብዙ ቁስል፣

ነዶ ነዶ ሁሌም ጨርሶ የማይከስል ፣

ቁጭት ቂም ጥላቻ ብዙ ቅር የሚያስብል።

ፌብሩዋሪ 2018

ስቶክሆልም