የመንግስት ወታደሮች በነቀምት ህዝብ ላይ ተኩስ ከፈቱ

አባይ ሚዲያ ዜና
አቤኔዘር አህመድ

በኦሮሚያ ነቀምት ከተማ ተቋውሞ ለማሰማት በወጡ ነዋሪዎች ላይ የመንግስት ወታደሮች ተኩስ መክፈታቸው ታወቀ።

የከተማው ነዋሪዎች ለተቋውሞ የወጡበት ምክንያት በቅርቡ ከእስር የተለቀቁትን የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ አመራር አባላት  ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና እና  አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ ሌሎችም የተካተቱበት ቡድን ወደ ከተማው እንዳይገቡ በመንግስት ወታደሮች በመከልከላቸው ነው።

የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ አመራር አባላት ከእስር ከተለቀቁ በኋላ ፕሮግራም ይዘው ከህዝባቸው ጋር በመገናኘት ውይይት እያደረጉ ይገኛል። በዚሁ ፕሮግራም መሰረት  ከነቀምት ነዋሪዎች ጋር ለመገናኘት እየተጓዙ ሳለ  አምቦ ላይ በአገዛዙ ወታደሮች ታግደው እንደነበረ ይታወቃል።

ነቀምት ከተማ ባኬ ጃማ በሚባል ቦታ ላይ የሰፈሩት የአገዛዙ ወታደሮች ህዝቡ ላይ እየተኮሱ ሲሆን ህብረተሰቡ ከተማውን በአስቸኳይ ለቀው እንዲወጡ በመጠየቅ ላይ ነው።