‹‹ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት የህወሓት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ›› የድምፅ እቀባ በማድረግ ታሪክ ሥሩ (ከኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ ማህበር ዶክተር እሸቱ ጮሌ ክበብ)

0

ኢት-ኢኮኖሚ /ET- ECONOMY

‹‹ባትዋጋ እንኳ በል እንገፍ እንገፍ፣
የአባትህ ጋሻ ትኋኑ ይርገፍ!!!››

ለኢትዮጵያ ሃገራዊ ንቅናቄ፣ ለኢትዮጵያዊያን የጋራ ግበረ ኃይል፣ ለኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ፣ ለኢትዮጵያውያን ተጋሩ፣ ለሁሉም ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶችና የሲቪክ ማህበራቶች ሁሉ፡- ብሄራዊ ትግሉን አቀናጅታችሁ እንድትመሩ ህዝቡ ይጠይቃል፡፡

ለህዝብ ተወካዬች ምክር ቤት አባላት  ‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ›› ድምፅ እቀባ አድማ  

{1} የሚኒስትሮች ምክርቤት ‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ›› አውጆል በህገመንግስቱ በተደነገገው የጊዜ ወሰን ውስጥ ፣የታወጀውን  ‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ›› ለህዝብ ተወካዬች ምክር ቤት አቅርቦ ያስፀድቃል፡፡ በዚህ መሰረት ሁለት ዓመት የሥራ ጊዜ ዘመን የቀራችሁ ለህዝብ ተወካዬች ምክር ቤት የተደነገገውን ፋሽስታዊ ‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ›› ምክር ቤቱ የድምፅ እቀባ ውድቅ እንዲያደርግ ህዝብ ይጠየቀል፡፡  ‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ›› ውድቅ ላደረጉ የህዝብ ተወካዬች ምክር ቤት ህዝቡ በሚቀጥለው ምርጫ እንደሚመርጣቸው ቃል ይገባል፡፡ አዲሱ የፓርላማ ወጣት ትውልድ በኢትዮጵያዊያን ወገኞቹ ጋር በመቆም ታሪክ መሥሪያው ጊዜ አሁን ነው፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ በመቃወማችሁ ምክንያት ለሚደርስባችሁ ሁሉ በአገር ውስጥና በባህር ማዶ ወገኞቻችሁ አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ‹የፓርላማ የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ›በማዋቀር ለመርዳት ቃል ይገባል፡፡ በኢትዮጵያዊያ ህዝብ የታሰሩትን የህዝብ ልጆች እንዳስፈታ ልብ ይበሉ፡፡ የአሜሪካ መንግሥት ፣ የእንግዚዝ መንግስት፣ የካናዳ መንግስት፣ የጀርመን መንግሥት፣የኖርዌ መንግሥት እንዲሁም የአውሮፓ ህብረት አገራቶች ይህን ‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ›› መቃወማቸውን ይወቁ፡፡ የአሜሪካ መንግሥት ኤች አር 128 ኢትጵያ መንግሥት የዓለም ስብዓዊ መብት ኮሚሽን ሃገሪቱ ውስት ገብተው ግድያውን እንዲያጣሩ  የካቲት 28 ድረስ ቀነገደብ አስቀምጠዋል ካለበለዛ ልልዩ ማእቀቦች በህወኃት/ኢህአዴግ ሹማምንትና በሃገሪቱ ላይ የኢኮኖሚ እቀባ ይከተላል፡፡ የወያኔን ፋሽስታዊ  አዋጅ የህዝቡን ዴሞክራሲዊና ስብዓዊ መብቶች የሚያፍን  ‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ›› የደገፈ የህዝብ ወኪል በህብረተሰቡ ይገለላል እንዲሁም ዳግም የመመረጥ ዕድላቸው የጨለመ ይሆናል፡፡

{2} ህዝቡ የመንግሥት ግብር ለወያኔ መንግሥት የኢትዩጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ግብር ባለመክፈል አድማ ይምታ

{3} ህዝቡ የብሄራዊ ሎተሪ ትኬቶች ባለመግዛት የወያኔን ገቢ ምንጭ የማሽምመድ አድማ ተጀምሮል፣ ሎተሪ ትኬት ባለመግዛት የወያኔን ገቢ በመቀነስ የወያኔን ጥይት መግዣ ማድረቅ ይቻላል፡፡ የተሠው ሠማዕታት ወንድሞቻችንን ደም ለማስታወስና ‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ›› እስኪነሳ የብሄራዊ ሎተሪ ትኬቶች ባለመግዛት የአድማ ጥሪ ለህዝብ ቀርቦል፡፡

{4}ብሄራዊ የቤት ውስጥ የመቀመጥ አድማ ማዘጋጀት፣

{5}የህዝብ ተወካዬች ምክር ቤት ‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ››ካወጁ ልክ ከምስቱ ዎስት ሰዓት ላይ በመላ ሃገሪቱ የኡኡታ፣የፉጨት፣ የጡሩንባና የፌሽካ ድምፅ ማሰማት አድማ ይካሄዳል፡፡ ይህንንም ጥረ በሃገር ውስትና የባህር ማዳ በሚገኙ መገናኛ ብዙሃን መረጃውን ለህዝብ እንዲያዳርሱ  ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡

{1} የአገር ውስጥ ታክስ፣ የውጭ ንግድና ቀረጥ ገቢዎችና የብሄራዊ ሎተሪ ሽያጭ ገቢ አሽቆልቁሎል

በ2008ዓ/ም 133 ቢሊዩን ብር ከህዝብ በግብር ሰበሰቡ፤ወያኔ በ2009ዓ/ም የኢትዩጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን 173.19 ቢሊዩን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ 113.56 ቢሊዩን ብር ብቻ በመሰብሰቡ የጎደለውን 59.63 ቢሊዩን ብር በቀሪው ሁለት ወራቶች ውስጥ ለመሰብሰብ በመገደዱ ከህብረተሰቡ ተጨማሪ ግብር ለመሰብሰብ አስቸኮይ የስራ ዘመቻ ነበር የከፈተው፡፡ በዛም የተነሳ ህዝብ ላይ የተጫነው ግብር ዋናው ምክንያት ለ‹‹አስቸኮይ ጊዜ አዋጅ›› በኮማንድ ፖስቱ አወጣ፡፡ የመከላከያ ሠራዊት፣ የፖሊስ ሠራዊት፣ የአጋዚ ጦር፣ልዩ ኃይል፣ ወዘተ የደሞዝ፣ የቀን አበል ያልተጠበቀና በበጀት ያልተያዘ ወጪ ሥርአቱን አናግቶታል፡፡ በሃገሪቱ በ2008 ዓ/ም  የተጀመረው እስከ 2009 እሰከ 2010ዓ/ም በተቀሰቀሳ ሕዝባዊ እንቢተኝነትና ተጋድሎ ምክንያት የህወኃት የጦር አበጋዞች መንግስት ከህዝብ፣ ከግብርና እና ታክስ የሚሰበስበው ገቢ በጣም ቀንሶል፡፡

‹‹በ2010ዓ/ም መንፈቅ ዓመት ከአገር ውስጥ ታክስ፣ ከውጭ ንግድና ቀረጥ ገቢዎችና ከብሄራዊ ሎተሪ ሽያጭ 199.11 ቢሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ ነው የታቀደው፡፡ በስድስት ወራት ታዲያ መሰብሰብ የተቻለው ከ90 ቢሊዮን ብር ብዙም የዘለለ አይደለም፡፡ ይህ አኃዝ ከዓመታዊ ዕቅዱ አንፃር ሲመዘን ከ40 በመቶ በታች ነው፡፡ ለገቢው መቀነስ የግብር ከፋዮ የህግ ተገዥነት ዝቅተኛ መሆን በምክንያት ይጠቀሳል፡፡ የቁጥጥር መላላትና የአሰራር ክፍተቶች፣ የግንዛቤ ማነስና የግብር ሥወራም የግብር አሰባሰብ ተግዳሮቶች ናቸው፡፡ ከዚህ በላይ ደግሞ እየተስፋፋ የመጣው ኮንትሮባንድ የግብር ትልቅ ፈተና ሆኖል፡፡ በበጀት ዓመቱ ስድስት ወራት ብቻ 436.74 ሚሊዮን ብር ግምት ያላቸው ዕቃዎች በኮንትሮባንድ  ወደ አገር ውስጥ ሊገቡና ሊወጡ ሲሉ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተመልክቶል፡፡ ይህን ህገ ወጥ ድርጊት መግታት ካልተቻለ በአገር ኢኮኖሚ ላይ የሚያሳድረው ጫና ከባድ ነው፡፡››… ‹‹የገቢዎችና ጉሙሩክ ባለስልጣን መስሪያ ቤት፣ የኮንትሮባንድ ሰለባ እንደሆነ የሚጠቁሙት በበጀት ዓመቱ ስድስት ወራት 109ቢሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ  አቅዶ አለመሳካቱን በማሳያነት ያቀርባሉ፡፡… ለኮንትሮባንድ መሥፋፋት የገቢዎችና ጉሙሩክ ባለስልጣን ህጉን የማስፈፀም አቅም ደካማ መሆን ነው ይላሉ፡፡ በአሁኑ ወቅት በየክልሉ የድንበር ንግድ ተብሎ ከውጭ ወደ አገር ውስጥ ዕቃ በገፍ እገባ እንደሆነ ገልፀው በዚህ አጋጣሚ የኮንትሮባንድ ዕቃ ወደ አገር ውስጥ የሚያስገቡ አካላት መኖራቸውን ያመለክታሉ፡፡ ይህን ማሰወገድ እንደሚገባም ይጠቁማሉ፡፡›› አቶ ዮሃንስ ወልደገብርኤል፡፡

የህወኃት/ኢህአዴግ መንግስት ‹‹በ2010ዓ/ም መንፈቅ ዓመት ከአገር ውስጥ ታክስ፣ ከውጭ ንግድና ቀረጥ ገቢዎችና ከብሄራዊ ሎተሪ ሽያጭ 199 ቢሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዶል፡፡ በ2010 ዓ/ም በስድስት ወራት ውስጥ  መሰብሰብ የተቻለው ከ90 ቢሊዮን ብር ሲሆን አፈፃፀሙ የእቅዱን 45 በመቶ ሆኖል፡፡

{2} የመደበኛው ባጀት ወጪ መጨመር የኢኮኖሚ ውድቀቱን አፋጥኖል

በሌላ በኩል መደበኛው ባጀት(ለመንግስት ሠራተኛና ለመከላከያ ሠራዊት  ደሞዝና አበል እንዲሁም ስራ ማስኬጃ  ከሃገሪቱ ዓመታዊ ባጀት የመደበኛው ባጀት በየግዜው እየጨመረ በመሄድ ላይ ይገኛል፡፡ በ2002 እኢአ 14.5 ቢሊዩን ብር፤ከሃገሪቱ ዓመታዊ ባጀት(22.48) በመቶኛ የነበረ ሲሆን፣ በ2004 እኢአ  23.0 ቢሊዩን ብር፤ከሃገሪቱ ዓመታዊ ባጀት (19.52) በመቶኛ የነበረ ሲሆን፣ በ 2006 እኢአ  32.56 ቢሊዩን ብር፤ ከሃገሪቱ ዓመታዊ ባጀት (21.01) በመቶኛ የነበረ ሲሆን፣ በ 2007 እኢአ  45.05 ቢሊዩን ብር፤ ከሃገሪቱ ዓመታዊ ባጀት የመደበኛው ባጀት (25.22) በመቶኛ እድገት አሳይቶል፡፡ የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የ2008ዓ/ም በጀት 223 ቢሊዩን 397 ሚሊዩን 819 ሽህ 216 ብር እንዲሆን ለሚንስትሮች ምክር ቤት አስወስኖ ለፓርላማ እንዲፀድቅ አስደርጎል በጀቱ ከአለፈው አመት ጋር ሲነፃፀር 44.58 ቢሊዩን ብር ብልጫ እንዳለው ታውቆል፡፡የ2008ዓ/ም መደበኛው በጀት 50,288,442,902 ቢሊዩን ብር መሆኑ ተጠቅሶል፡፡ የ2010ዓ/ም መደበኛው በጀት 82 ቢሊዩን ብር መሆኑ ተጠቅሶል፡፡ በመንፈቅ ዓመቱ 14 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት ለህዝብ ተወካዬች ምክር ቤት ወያኔ አፀድቆ ሃገሪቱን ኢኮኖሚ ወደ ገደል እየከተተ ይገኛል ይህም አልበቃ ብሎት ህወሓት ‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ››በማወጅ የክልል መንግሥቶችን ሥልጣን በመንጠቅ ወታደራዊ አስተዳደር በመመሥረት የህዝብ ልጆችን ለመግደልና ለማሰር አቅዶል፡፡ ለዚህ ፋሽስታዊ ድርጊት ተባባሪ የሚሆኑ የህዝብ ተወካዬች ምክር ቤት አባላት በታሪክ ያስጠይቃል፡፡

የኢትዬጵያ ፌዴራል መንግስት ዓመታዊ ባጀት(ቢሊዩን ብር)

ከ2002/2009 እንደ ኢትጵያዊያን አቆጣጠር

የባጀት ዓይነት 2002

ቢሊዩን ብር

2004

ቢሊዩን ብር

2006

ቢሊዩን ብር

2007

ቢሊዩን ብር

2008

ቢሊዩን ብር

2009

ቢሊዩን ብር

ለመደበኛ ወጪ 14.5 23.0 32.56 45.05 50.288 82
ለካፒታል ፕሮጀክቶች ወጭ 29.1 48.0 64.29 66.99 84.300 115
ለክልል መንግስት ድጋፍ 20.9 31.4 43.09 51.50 76.808 117
ለምዕተ አመቱ የልማት ግቦች ማጠናከሪያ 15.0 15.00 15.00 12.000    7.0
ጠቅላላ ዓመታዊ የፌዴራል መንግስት ባጀት 64.5 117.8 154.94 178.6 223.3 321.8

የ2009 ዓ/ም መደበኛው በጀት

የ2009 ዓ/ም መደበኛው በጀት 82 ቢሊዩን ብር መሆኑ ተጠቅሶል፡፡ የኢትዬጵያ ፌዴራል መንግስት የ2010 ዓ/ም የተያዘው ዓመታዊ በጀት 321.8 ቢሊዩን ብር ውስጥ የመደበኛ በጀት ወጪ ከ2008 ዓ/ም ጋር ሲወዳደር በ31 ቢሊዩን 712 ሚሊዩን ብር ሲጨምር፣ጭማሪው የ61 በመቶ ከፍ ያለ መሆኑን ማስተዋል ይቻላል፡፡ ይህ አምራች ላልሆነው ለመንግስት ሠራተኛና ለመከላከያ ሠራዊት፣ለፖሊስ ሠራዊት፣ ለአጋዚ ጦር፣ ለልዩ ኃይል በአጠቃላይ ህዝቡን ለማፈን ለተሰማራው ፀረ ህዝብ ሠራዊት ደሞዝና አበል እንዲሁም ስራ ማስኬጃ፣ የመኪና ነዳጅ መግዣ ወጪ የሚሆን በጀት መሆኑን ህዝብ ሊያውቀው ይገባል፡፡ በህዝቡ ላይ የተጫነው ግብር የቀጣዩን ዓመታዊ በጀት ለመሸፈን ‹‹ገበሬ የሚበላው ቢያጣ የሚከፍለው አያጣም!›› እንደሚባለው ነው፡፡  

የህወኃት የጦር አበጋዞች መንግሥት፣በተጨማሪ አዲስ የመከላከያና ፖሊስ ሠራዊት መመልመያ፣ አዲስ ሚሊሽያ ሠራዊት መመልመያ፣ አዲስ እስር ቤቶች መገንቢያ፣ አዲስ ፖሊስ ጣቢያዎች ለመገንባትና የተነሳውን ህዝባዊ እንቢተኝነትና ህዝባዊ ተጋድሎ ለማፈን ‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ›› የካቲት 9 ቀን 2010 ዓ/ም ባወጣው አዋጅ የተበጀተልን መደበኛ ወጪ ለሃገሪቱ ልማት ቢውል፣ ለረሃብተኛው ህዝብ እህል መግዣ ቢውል፣ ከዩኒቨርሲቲ ለተመረቁ ወጣቶች የሥራ መስክ ፈጠራ ላይ ቢውል፣ ለህብረተሰቡ የውሃ፣ ጤና፣ ትምህርትና መብራት አገልግሎት ላይ ቢውል መልካም ነበር፡፡     

የኢትዩጵያ ሕዝቦች አብዩታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) መደበኛው ባጀት ለብሄራዊ ክልላዊ መንግስታት ለመንግስት ሠራተኛ ደሞዝና አበል እንዲሁም ስራ ማስኬጃ ያውለዋል፡፡ የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ለኦሕዴድ) ሹማምንትና ካድሬዎች ለኦሮሚያ ክልል፣ ብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ለብአዴን) ሹማምንትና ካድሬዎች ለአማራ ክልል፣ የደቡብ ኢትዩጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ለደኢሕዴግ) ሹማምንትና ካድሬዎች ለደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል፣ ለሶማሌ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ለሶዴድ) ሹማምንትና ካድሬዎች ለሶማሌ ክልል፣ ለህወሃት ሹማምንትና ካድሬዎች  ትግራይ ክልል ፣ለአዴድ ሹማምንትና ካድሬዎች  የአፋር ክልል፣ ቤኒሻንጉል ሕዝቦች ነፃ አውጭ ንቅናቄ (ለቤህነን)  ሹማምንትና ካድሬዎች የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ ጋምቤላ ሕዝቦች ነፃነት ንቅናቄ (ለጋሕነን) ሹማምንትና ካድሬዎች ለጋምቤላ ክልል፣ ለሃዴድ ሹማምንትና ካድሬዎች ለድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ለሃራሪ ክልል ሹማምንትና ካድሬዎች፣ ለአዲስአበባ አስተዳደር ሹማምንትና ካድሬዎች በ2002 እኢአ 14.5 ቢሊዩን ብር የነበረ ሲሆን በ2007 እኢአ 45.05 ቢሊዩን ብር፣ በ2008ዓ/ም መደበኛው በጀት 50,288,442,902 ቢሊዩን ብር ከፍ ማለቱ ተገልፆል፡፡ በ2009ዓ/ም መደበኛው በጀት 82 ቢሊዩን ብር ከፍ ማለቱ በአንድ ግዜ የ31 ቢሊዩን 712 ሚሊዩን ብር ጭማሪ ህብረተሰቡን ለከፍተኛ ግብር እንደዳረገው የምጣኔ ሃብት ጠበብት በማስረጃ ለህዝብ ያቀርባሉ፡፡

ህወሃት በመላ ሃገሪቱ ‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ›› በማወጂ፣በተለይ በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች የተነሳውን ህዝባዊ እንቢተኝነትና ተጋድሎ ለማፈን ከ2008 እስከ 2009 ዓ/ም መጨረሻ፣ ኮማንድ ፖስቱ ለመንግስት ሠራተኛና ለመከላከያ ሠራዊት  ደሞዝና አበል እንዲሁም ስራ ማስኬጃ የመኪና ነዳጅ፣ ለስራ ማስኪጃ፣ ለስብሰባ፣ለኮንፍረንስ፣ለመጎጎዣ፣ለአዲስ እስር ቤቶች መገንያና ለፖሊስ ጣቢያዎች መስሪያ ወዘተ የተለያዩ  ወጭዎች፣ በብዙ መቶ ቢሊዩን ብር የሚገመት ኪሣራ ተከናንቦል፡፡ ይህ ያገሪቱ አንጡራ ሃብት ለልማት ሥራ ውሎ ቢሆን፣በትንሹ ለተራቡ ወገኖቻችን በደረስልላቸው ነበር፡፡ ይህ በእንዲህ እያለ አዲሱን 2010 ዓ/ም አመታዊ ባጀት መንፈቅ ዓመት ተጨማሪ 14 ቢሊዮን ብር በጀት ለወታደሩ ደሞዝ፣ለሥራ ማስኪጃ ወጪ ለማዋል ታቅዶል፡፡ የወያኔ መንግስት ወታደራዊ ወቺ በየግዜው በመጨመሩ የተነሳ ብዙ ሜጋ ፕሮጀክቶች ለካፒታል በጀት የተያዘ 115 ቢሊዩን ብርና፣ ለክልሎች 117 ቢሊዩን ብረና ለክልሎች ለዘላቂ ልማት ግቦች ማስፈፀሚያ  ሰባት ቢሊዩን ብር የተደለደለው በጀት ‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ›› ኮማንድ ፖስት ለወታደራዊ ወጪ መደልደሉን ታውቆል፡፡ የወያኔ መንግስት ቤሳቢስቲ ከካዝናው የለውም፡፡  በ2010 ዓ/ም  የተመደበው የፌዴራል መንግስት ባጀት የገቢ ምንጮች ከአገር ውስጥ ታክስና ታክስ ያልሆኑ ገቢዎች፣ ከውጭ ብድርና እርዳታ የሚሞላ መሆኑ ተገልፆል፡፡ በአገሪቱ አምራቹ የሰው ሃይልና ግብር ከፋይ ዜጋዎች አምራች ባልሆኑ በሰው ተከሻ የሚኖሩ ጥገኛ የመንግስት ሹማምንት፣ካድሬዎች ሠራተኛና ለመከላከያ ሠራዊት  ደሞዝና አበል ቀለብ ሲሰፍር ይኖራል፡፡  

ከነጋድራስ ገብረህይወት ባይከዳኝ ‹መንግሥትና የህዝብ አስተዳደር›በሚል ርዕስ በ1916 እኢአ የታተመ መፅሃፋቸው ውስጥ የዛሬ ዘጠና ዓመታት እንዲህ ብለው ነበር፡፡ ‹‹ብረት ሠሪውም ማረሻ አበጅቶ ጤፍ ይቀበላል፡፡ አራሹም ጤፍ ሰጥቶ የተሻለ ማረሻ ያገኛል፡፡በሌላም ነገር ሁሉ እንደዚሁ ነው፡፡ ዕውቀት ባለው ሕዝብ መካከል ግን በከንቱ የሚሰጥ ሰው የለም፡፡ በከንቱም የሚበላ ሰው የለም፡፡ የሁሉም  ትዳሩ ተለዋውጦ ነውና እንካ ሥራ አምጣ ሥራ ይባባላል፤ይህ ሳይሆን ቀርቶ በላተኛው ከሠራተኛው ሲበዛ በማናቸውም ቤት ሀብት ሊገባ አይችልም፡፡ ዕውቀትም ከሌለው ሕዝብ ውስጥ ከሠራተኛው በላተኛው፣ሹም ወታደር ነጋዴ እየሆነ ይበዛልና ባገሩ ሀብት ሊከማች አይችልም፡፡ የሥራው ፍሬ እንደ ገባ ወዲያው ያልቃል፡፡  ከነጋድራስ ገብረህይወት ባይከዳኝ (መንግሥትና የህዝብ አስተዳደር ገፅ 64)

ለ/ ለካፒታል ፕሮጀክቶች ባጀት

በተመሳሳይ ለካፒታል ፕሮጀክቶች በጀት ከሃገሪቱ ዓመታዊ ባጀት የካፒታል ባጀት በየግዜው እየጨመረ በመሄድ ላይ ይገኛል፡፡ በ2002 እኢአ 29.1 ቢሊዩን ብር፤ከሃገሪቱ ዓመታዊ ባጀት(45.12) በመቶኛ የነበረ ሲሆን፣ በ2004 እኢአ  48.0 ቢሊዩን ብር፤ከሃገሪቱ ዓመታዊ ባጀት (40.75) በመቶኛ የነበረ ሲሆን፣ በ 2006 እኢአ  64.29 ቢሊዩን ብር፤ ከሃገሪቱ ዓመታዊ ባጀት (41.49) በመቶኛ የነበረ ሲሆን፣ በ 2007 እኢአ  66.99 ቢሊዩን ብር፤ ከሃገሪቱ ዓመታዊ ባጀት የካፒታል ፕሮጀክቶች ባጀት  (37.51) በመቶኛ እድገት አሳይቶል፡፡ የ2008ዓ/ም የሃገሪቱ አጠቃላይ በጀት 223.3 ቢሊዩን ሲሆን ከዚህ ውስጥ፣ ለካፒታል ፕሮጀክቶች በጀት 84,300,732,449  ቢሊዩን ብር መሆኑ ተጠቅሶል፡፡

የ2009 ዓ/ም የሃገሪቱ አጠቃላይ በጀት 321.8 ቢሊዩን ሲሆን ከዚህ ውስጥ፣ ለካፒታል ፕሮጀክቶች በጀት 115  ቢሊዩን ብር መሆኑ ተጠቅሶል፡፡ የ2009 ዓ/ም የተያዘው በጀት ከአለፈው ዓመት የ30 ቢሊዩን 700 ሚሊዩን ብር ማለትም 73 በመቶ የበጀት ጭማሪ አሳይቶል፡፡

ሐ/ የክልል መንግስት ድጋፍ ባጀት

የኢትዬጵያ ፌዴራል መንግስት ዓመታዊ ባጀት ለክልሎች መንግስት ድጋፍ ወይም ድጎማ ከ20.9 ቢሊዩን ብር ወደ 117 ቢሊዩን ብር እድገት ማሳየቱ ይስተዋላል፡፡ በ2002 እኢአ 20.9 ቢሊዩን ብር፣በ2004 እኢአ 31.4 ቢሊዩን ብር፣ በ2006 እኢአ 43.09 ቢሊዩን ብር፣ በ2007 እኢአ 51.50 ቢሊዩን ብር፣በ2008 እኢአ 76.8፣በ2009ዓ/ም 117 ቢሊዩን ብር አድጎል፡፡

የመንግስት ለብሄራዊ ክልላዊ መንግስታት የሚደረገው ጠቅላላ የክፍፍል ባጀት ድጎማ በየግዜው እየጨመረ በመሄድ ላይ ይገኛል፡፡ በ2002 እኢአ 20.9 ቢሊዩን ብር፤ከሃገሪቱ ዓመታዊ ባጀት የክልል ባጀት (32.4) በመቶኛ የነበረ ሲሆን፣ በ2004 እኢአ  31.4 ቢሊዩን ብር፤ከሃገሪቱ ዓመታዊ ባጀት የክልል ባጀት (26.7)በመቶኛ የነበረ ሲሆን፣ በ 2006 እኢአ  43.09 ቢሊዩን ብር፤ ከሃገሪቱ ዓመታዊ ባጀት የክልል ባጀት (27.8) በመቶኛ የነበረ ሲሆን፣ በ 2007 እኢአ  51.50 ቢሊዩን ብር፤ ከሃገሪቱ ዓመታዊ ባጀት የክልል ባጀት (28.8) በመቶኛ እድገት አሳይቶል፡፡

የኢትዬጵያ ፌዴራል መንግስት የ2009 ዓ/ም ዓመታዊ በጀት

የኢትዬጵያ ፌዴራል መንግስት የ2009ዓ/ም ዓመታዊ በጀት 321.8 ቢሊዩን ብር ሲሆን ይህም በዩኤስ 14  ቢሊዩን ዶላር ይተመናል፡፡ ከመደበኛና ከካፒታል ወጪ ውስጥ ከፍተኛ ድርሻ ያገኙት እነማን እንደሆኑ አልተገለፀም፡፡ በአጠቃላይ ለመሠረተ ልማት፣ለኢትዩጵያ መንገዶች ባለሥልጣን፣ ለትምህርት ዘርፍ፣ ለውሃ፣ ለጤና፣ ለገጠር ኤሌክትሪፊኬሽን፣የውጭ ዕዳ ክፍያ ወጪ፣መከላከያ ሚኒስቴር፣ግብርና ሚኒስቴር ስንት ቢሊዩን ብር በጀት እንደተመደበላቸው አልተገለፀም ነበር፡፡

የኢትዬጵያ ፌዴራል መንግስት የ2010 ዓ/ም የተያዘው ዓመታዊ በጀት 321.8 ቢሊዩን ብር መሆኑን የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትር ዶክተር አብርሃም ተከስተ ገልጧል፡፡ ከዚህ በጀት ለመደበኛ 82 ቢሊዩን ብር፣ ለካፒታል 115 ቢሊዩን ብር፣ ለክልሎች 117 ቢሊዩን ብረና ለክልሎች ለዘላቂ ልማት ግቦች ማስፈፀሚያ  ሰባት ቢሊዩን ብር መደልደሉን አስታውቀዋል ነበር፡፡

በዚህ መሠረት ከአገር ውስጥ ገቢ ስንት ቢሊዩን ብር ለመሰብሰብ እንደታቀደ፤ እንዲሁም ከመሠረታዊ አገልግሎት፣ ከፕሮጀክት ዕርዳታ፣ከፕሮጀክት ብድር በድምሩ ስንት ቢሊዩን ብር  እንደሚሰበስብ አልተገለፀም ነበር፡፡

የ2009 ዓ/ም በጀት ለመሸፈን መንግስት ከጠቅላላ ዓመታዊ ባጀት ውስጥ የ53.9 ቢሊዩን ብር ጉድለትን ለመሸፈን ያቀደው ከአገር ውስጥ ብድር፣ማለትም ከባንኮች እንዲሁም ከውጭ ዕርዳታና ብድር እንደሚሸፈን ተገልጾል፡፡ የኢትዬጵያ ፌዴራል መንግስት የ2009ዓ/ም ዓመታዊ በጀት 9.6 በመቶ የ2008ዓ/ም ዓመታዊ በጀት ብልጫ እንዳለው ተገልፆል ነበር፡፡

የ2010 ዓ/ም በጀት

  • ከኦሮሚና ከሶማሌ ክልሎች ለተፈናቀሉ አንድ ሚሊዮን ወገኖች 14 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት በህዝብ ተወካች ምክር ቤት ፀደቀ፡፡ የወያኔ መንግስት መንንም ተጠያቂ አላደረገም፡፡
  • በህዝብ አመጽ እየወደሙ ያሉት ንብረቶች በብዙ ቢሊዮን ብር ይገመታል፡፡በአገሪቱ በተፈጠረው የፖለቲካና የፀጥታ ችግር የተነሳ የንግድ እንቅስቃሴዎች መቀዝቀዛቸውና መሽመድመዳቸው ሰተዋላል፡፡ ከግንባታ በፊት ውይይት ይቅደም፡፡ የሰው ነፍስ ማጥፋት ህዝባዊ አመፅና የግንባታ ውድመት ያስከትላል፡፡

የ2009 እኢአ ለክልሎች ድጎማ

የ2009 እኢአ ለክልሎች ድጎማ የፀደቀው ባጀት 117 ቢሊዩን ብር ሲሆን፣ለክልሎች የተመደበው ባጀት ክፍፍል ለህዝብ በይፋ አልተገለፀም፡፡ የ2009ዓ/ም በጀት በ40 ቢሊዩን 192 ሚሊዩን ብር ማለትም 66 በመቶ እድገት ከአለፈው ዓመት በጀት ብልጫ እንዳለው ማስተዋል የቻላል፡፡ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ያፀደቀው ቀመር የበጀት ክፍፍል ምደባ አድሎዊነት በተለያዩ ክልሎች ተቃውሞ ከገጠመው አመታት ቢቆጠርም ህወኃት መንግስት ተሰሚነት አላገኘም፡፡

ህወሃት የጦር አበጋዞች መንግስት ለመከላከያ ዘርፍ የሚመድበውን በጀት ወጪ፣ በክልሎች ድጎማ ስም በመመደብ በመላ ሃገሪቱ ‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ›› ኮማንድ ፖስት፣በተለይ በአማራና በኦሮሚያና በሁሉም ክልሎች የተነሳውን ህዝባዊ እንቢተኝነትና ተጋድሎ ለማፈን ለመከላከያ ሠራዊት  ደሞዝና አበል እንዲሁም ስራ ማስኬጃ የመኪና ነዳጅ፣ ለስራ ማስኪጃ፣ ለስብሰባ፣ለኮንፍረንስ፣ለመጎጎዣ፣ለአዲስ እስር ቤቶች መገንያና ለፖሊስ ጣቢያዎች መስሪያ ወዘተ የተለያዩ  ወጭዎች፣ በብዙ ቢሊዩን ብር ከክልሎች ድጎማ በጀት ለመከላከያ ወጪ እንደሚሆን ባለሙያዎች በመረጃ ይተነትናሉ፡፡ 

ለክልሎች የሚደረግ የበጀት እርዳታ/ድጎማ

የኢትዬጵያ ፌዴራል መንግስት ለክልሎች የበጀት ድጎማ ሚያደርግበት ሁለት መሠረታዊ ምክንያቶች አሉት፡፡ የመጀመሪያው ምክንያት የክልሎች መንግስታት ያላቸውን የተፈጥሮ፤ የሰው ሃይልና ካፒታል ሃብቶችን በአግባቡ ማደራጀት ባለመቻላቸው የተነሳ፣ አስተዳደራዊ ወጫቸውን መሸፈን ባለመቻላቻ ምክንያት ነው፡፡ ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ መንግስት በሁሉም ክልሎች እኩል የሆነ የኢኮኖሚ እድገት ማምጣት ሃላፊነት ስላለበት ነው፡፡ መንግስት በሁለተኛው ምክንያት የተነሳ እኩል ያልሆነ የሃብት ክፍፍል ፖሊሲ በመንደፍ በክልሎች መኃል እኩልነት መፍጠር ይሻል፡፡

የመንግስት ለክልሎች የሚያደርገው የእርዳታና ድጎማ ስርዓት ለክልሎች እድገት ጠቃሚ መሣሪያ በመሆን የኢኮኖሚና የማህበረሰብ እድገት ለማፋጠን ታላቅ ጠቄሜታ ሳያስገኝ ቀርቶል፡፡ በዚህም ምክንያት ለብሄራዊ ክልላዊ መንግስታትና አስተዳደር የሚደረገው ጠቅላላ የካፒታል ባጀት ክፍፍል ድጎማ በየግዜው እየጨመረ ቢሄድም በክልሎች መኃል የተፈጠረው ያልተስተካከለ ዕድገት በተለይም በትምህርት፣ በጤና፣ በመብራት፣ በቴሌኮሙኒኬሽን፣ በመሠረተ-ልማት ማለትም በመንገድ ሥራ፣ በባቡር መስመር፣ በኤርፖርት፣ በግድቡ፣ በኢንዱስትሪያል ዞኖች ግንባታ አይን ያወጣ አድሎ እንደአለ ገሃድ ሆኖል፡፡

የኢትዬጵያ ፌዴራል መንግስት ለክልሎች የበጀት ድጎማ መሠረታዊ ደንብና መመሪያ ሲኖረው የኢኮኖሚውን እድገት ቱሩፋት በፍታዊነት ለማከፋፈል ዋናው መሥፈርቶች መኃል፤የክልሎች የህዝብ ብዛት፣የእድገታቸው ደረጃ፣የገቢ ምንጫቸው ከካፒታል ባጀት ጋር ያለው የንፅፅር ድርሻ፣በማስላት ላይ ያልተመሠረተ መሆኑን አጥኝዎች ይገልፃል፡፡

የኢትዬጵያ ፌዴራል መንግስት አጠቃላይ ባጀት (Regional Government Budget)፤ የፌዴራል ገንዘብ ክፍፍል ለክልሎች ባጀት በመቶኛ (Federal money as % of total) እና የነፍስ ወከፍ ካፒታል የፌዴራል ገንዘብ ድርሻ ( Percapita share of Federal Money) ከአዲስ አበባ በስተቀር ሁሉም ክልሎች የፌዴራል ገንዘብ ተደጎሚዎች እንደሆኑ ማስተዋል ይቻላል፡፡ለክልሎች የበጀት ድጎማ መሠረታዊ ደንብና መመሪያ ቢኖረውም በፍትሃዊና እኩልነት ላይ የተመሠረተ ቢመስልም፤በሌላ ገፅታው ሲታይ በሌሎች ተለዋዋጭ ምክንያቶች የክልሎች የፌዴራል ገንዘብ ክፍፍል ኢፍትሃዊነትና አድሎን ያሳያሉ፡፡

አንደኛ በለጋሺ ሃገራት ተጨማሪ የባጀት ድልድል በሚያገኙ ክልሎች ክፍፍሉን የተዛባ ያረገዋል፣ዝቅተኛውን የነፍስ ወከፍ ካፒታል የፌዴራል ገንዘብ ድጋፍ ያገኘ ክልል ሌላ የገንዘብ ምንጭ ስለሚያገኝ የመንግስት ድጎማን ኢፍታዊና አድሎዊ ያደርገዋል፡፡

ሁለተኛ የነፍስ ወከፍ ካፒታል የፌዴራል ገንዘብ፣ወይም አጠቃላይ የፌዴራል መንግስት የገንዘብ እርዳታ ድምር ሂሳብ በማየት ፍትሃዊነትና እኩልነት መኖሩን ማረጋገጥ አይቻልም፡፡ ውስጣዊ ክፍፍልና ዳግማዊ ክፍፍል ጥቅምና የጥቅሙን የማግኛ መድረሻና መግቢያ ዘዴ መንገድ ማወቅ  ትልቅ ተፅዕኖ  ያደርጋሉ፤በክልሉ ህዝብ በእኩልነት የኢኮኖሚ እድገቱን ቱሩፋት ለመቆደስ አይቻልም፡፡ በኢትዩጵያ ኃላቀር ክልሎች በተለይ የጋምቤላ፣ ሱማሌ፣ አፋር፣ቢኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች በጣም ኃላ ቀር የኢኮኖሚ እድገት እንዳላቸው ይታወቃል፡፡ በዚህም የተነሳ ባለፉት 26 ዓመታት አንባገነናዊ አገዛዝ፣ የህወኃት የጦር አበጋዞች መንግሥት ፍትሃዊ የበጀት ክፍፍል በፌዴራል ሥርዓቱ እንደሌለ ህዝቡ ተገንዝቦል፡፡

{3}የባህር ማዶ ልማት ትብብር (ODA፡ Official Development Assistance) ከ1991 እኤአ እስከ 2012 እኤአ ለህወሃት/ኢህአዴግ መንግስት አርባ ቢሊዩን ዶላር የልማት እርዳታ ሰጥተዋል፡፡ በአለፉት ሃያ ዓመታት ውስጥ በአማካኝ በአመት ሁለት ቢሊዩን ዶላር እርዳታ ሃገሪቱ እንዳገኘች ያስረዳል፡፡ በይፋ የተለያዩ ለጋሽ ሃገራት የሰጡትን ገንዘብ ብዛትን ለማስላት ያህል በትንሹ ስምንት ታላቁን የህዳሴ ግድብ ኤሌትሪክ ማመንጫን የሚችል ሜጋ ፕሮጀክቶችን በእርዳታ ገንዘቡ መስራት የሚያስችል ነበር፡፡ አልያም የቻይና መንግስት በ200 ሚሊዩን ዶለር ያሰራውን የአፍሪካ ህብረት አዳራሽ ህንፃን ዓይነት ሁለት መቶ ህንፃዎች ሊገነባ የሚችል ገንዘብ ነበር፡፡ የባህር ማዶ ልማት ትብብር እርዳታ ከ2008 እስከ 2015እኤአ ያለውን ብቻ ብናይ ከ3 እስከ4 ቢሊዩን ዶላር ሃገራችን የልማት እርዳታ አግጥታለች፡፡ በኦዲኤ ዋና ዋናዎቹ እርዳታ አድራጊ መንግስቶችና ተቆማት አሜሪካ መንግሥት፣ የእንግሊዝ መንግሥት፣ የአውሮፓ ህብረት ኢንስቲቲዉሽኖች፣ ኢንተርናሽናል ዲቨሎፕመንት አሲስታንስና ግሎባል ፈንድ ናቸው፡፡  የህወሓት/ ኢህአዴግ ፋሽስታዊ መንግሥት ለሦስተኛ ጊዜ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ›እንዲያነሳ ጫና እንዲደረግበት የዲያስፖራው የትግል እንቅስቃሴ በነዚህ አገሮችና ድርጅቶች ላይ ማነጣጠር ይኖርበታል፡፡ ወያኔ የተነቃነቀ በትረ ሥልጣኑን ዴሞክራሲን በማፈን፣ ስብዓዊ መብቶችን በማፈን፣ ህገ-መንግስቱን በመጣስ የኢትዮጵያ ህዝብን አፍኖ በመግዛት ላይ መሆኑን በሠላማዊ ሠልፍ መግለፅ አስፈላጊ ነው፡፡

የህወሓት መንግሥትን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ›የሃገሪቱን የፖለቲካ አቅጣጫ የዴሞክራሲ ስርዓት የሃዲድ መሥመር የጣሰና ወደ አንባገነን ስርዓት የጨለማ ሃዲድ የዘረጋ በመሆኑ የባህር ማዶ ልማት ትብብር  አጋር አገራቶች  ድጋፍ ለኢትዮጵያ ይቀንሳል ብሎም ይቆማል፡፡

የዲጅታል ቴክኖሎጅ ወጣት ትውልድ የዴሞክራሲ ስርዓት ለመገንባት፣ በሃገሪቱ ዴሞክራሲያዊ አስተዳደር ለመመስረት የብዙሃን ፓርቲዎች የውድድር ሥርዓት ዘርግቶ፣ በህዝብ ድምፅ አሸናፊው ሥልጣን የሚይዝበት የምርጫ ስርዓተ-አሥተዳደር መገንባት አለበት፡፡ በኢትዩጵያ የወያኔ ልማታዊ መንግሥት› ስም የወያኔ መንግሥታዊው ዘርፍ(ኢፈርት ሜቴክ፣ ኢዛና፣ ጥረት፣ ዲንሾ፣ ወንዶ ወዘተ) የግሉን ዘርፍ ኃብትና ሊሠራ የሚችለውን ኢንቨስትመንት ሥራ ሁሉ በመሻማት የግሉን ዘርፍ እድገትና ሚና በመላ ሃገሪቱ አጨናግፎታል፡፡ የወያኔ ኢፈርት ኢንተርፕራይዞች፡- በወያኔ ባለሥልጣኖች የሚተዳደሩ የሜቴክ ድርጅቶች የሙስና መፈልፈያዎች፣ የእውቀትና የብቃት ችግር የተንሠራፋባቸው፣ በሥልጣን በመጠቀም የግል ፍላጎት ተጠቃሚነትን የሚያስፋፉ፣እንዲሁም ከለላን የሚያበረታቱ፣ የፖለቲካና የዝምድና አሰራር የነገሰበቸው ናቸውና ለቀጣዮ ትውልድ የሥራ ዕድል ሊፈጥሩ አይችሉም፡፡  በሃገሪቱ 30 ሚሊዮን ወጣቶች ሥራ አጥ ናቸው፡፡ ወጣቶች በሃገራቸው ሠርተው መኖር መብት አላቸው፡፡ አድሎዊና ተመጣጣኝ ያልሆን የክልሎች እድገት ይወገድ!! በክልላችን የሚካሄድ የመሬት ቅርምት ይቁም!! በክልላችን ኃብት የዘረፉ ለፍርድ ይቅረቡ! ያለ ኢኮኖሚ ነፃነት የፖለቲካ ነፃነት የለም! ወጣቶች የሚሉት ለዚህ ነው፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ የኢህአዴግ መንግሥት ያወጣውን ‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ›› ተቃወመ የህዝቡን የመሰብሰብና ሃሳብ መግለጽን መከልከልን፣ የዴሞክራሲዊ መብቶችን የመጸፍ፣ መናገር፣ መደራጀት፣ የሠላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ማካሄድና መሰረታዊ መብቶች ክልከላ መፍትሄ አይሆንም በማለት ምክረ ሃሳባቸውን አካፍለዋል፡፡ የኢህአዴግ መንግሥት በሃገሪቱ ዴሞክራሲን ማስፈን፣ የምጣኔ ሃብት እድገት ማስመዝገብ፣ ለህዝቡ ብልፅግና ሰላምና መረጋጋት ያመጣል እንጂ የስድስት ወር ‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ›› ማወጅ መፍትሄ አይሆንም በማለት ኮንነዋል፡፡ እንዲሁም የአውሮፓ ህብረት አገራቶች የኢህአዴግ መንግሥት ያወጣውን ‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ› ተቃውመዋል፡፡

{4} ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ፍሰት (Foreign Direct Investment Inflows) ‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ›› ለሃገሪቱን የኢኮኖሚ ዘርፍ የሚያስከትለው ጉዳት በተመለከተ በሃገሪቱ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ፍሰት ይቀንሳል፡፡ ሰላም በሌለበት ሃገር የባህር ማዶ ኢንቨስተሮችን አይስብም፣ እንዲያውም ያፈሰሱትን ምዋለንዋይ ሸጠው ለመውጣት  ይገደዳሉ፡፡ በሃገራችን የኢኮኖሚ ነፃነት ከሚገለፅባቸው ዋና ዋና መርሆዎች ውስጥ አንዱንም አታሞላ፡፡ አንደኛው የህግ የበላይነት፣የፍትህ ሥርዓት መከበር፣የንብረት ባለቤትነት መብት መከበር፣ የመንግሥት ሙስናን ለመዋጋት ያለው አቅም የመሳሰሉት ይጠቀሳሉ፡፡ የሃገር ውስጥና የባህር ማዶ ኢንቨስተሮች የህግ ሉዓላዊነት ያለበት ሃገር መዋለ-ንዋያቸውን አፍሰው በነፃነት ኃብት ማፍራት ይሻሉ፡፡ ህግና ፍትህ ባለበት ሃገር ቀጥተኛ የውጪ ኢንቨስትመንት ፍስት ከአመት አመት እንዲጨምር ያደርጋል፡፡ በኢትዩጵያ ህግ የለም፣ ፍትህና ርትህ አይሠራም፣ የዜጎች ንብረት የማፍራት መብት የለም፡፡ በኢትዩጵያ የህወሓት መንግሥት በሞኖፖል የተያዙ ንብረቶችና ኃብቶች መካከል፡-በሃገሪቱ የመሬት ኃብት የህወሓት መንግሥት በመሆኑ የግብርና፣የማኑፋክቸሪንግና አገልግሎት ዘርፍ ክፍለ ኢኮኖሚ እድገቱ የቀጨጨ ለመሆን በቅቶል፡፡ ህዝባችን የመሬት ኃብት ንብረት የመያዝ መብትና ነፃነት ስለሌለው በርሃብ አለንጋ ይሰቃያል፡፡ ህዝቡን መመገብ የማይችል መንግሥት ህዝቡን መግዛት አይችልም፡፡ በሃገሪቱ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ፍሰት በ2008እኤአ (109 ሚሊዮን ዶላር)፣በ2009እኤአ (211 ሚሊዮን ዶላር)፣በ2010እኤአ (288 ሚሊዮን ዶላር)፣በ2011እኤአ (627 ሚሊዮን ዶላር)፣በ2012እኤአ (279 ሚሊዮን ዶላር)፣በ2013እኤአ (1281 ቢሊዮን ዶላር)፣በ2014እኤአ (2132 ቢሊዮን ዶላር)፣በ2015እኤአ (2168 ቢሊዮን ዶላር)፣2016እኤአ (አልተገለጸም)፣ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ፍሰት ነበር፡፡‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ምክንት ቀጥተኛ የውጪ ኢንቨስትመንት ፍስት በጣም ይቀንሳል፡፡››

{5} ከሆቴልና ቱሪዝም የሚገኝ ገቢ ይነጥፋል፣  ባህር ማዶ ጎብኝዎችንና በኢትዮጵያ ቁጥር ይቀንሳል በዚህም ምክንያት ከቱሪስቶች የሚገኝ ገቢ ያሽቆለቁላል፣ የውጭ ምንዛሪ ገቢ ይቀንሳል፣

በ2008 እኤአ ኢትዩጵያን የጎበኙ ቱሪስቶች ቁጥር 383 ሽህ  ሲሆን ከዘርፍ 355400 ሚሊዩን ዶላር ገቢ ተገኝቶ ነበር፡፡ የቱሪዝም ዘርፍ አስተዋፅኦ ለአጠቃላይ አገር ውስጥ ምርት(ጂዲፒ) 10.4 በመቶ እንዲሁም ለሥራ ዕድል 6.3 በመቶ አበርክቶ ነበር፡፡ በ2014 እኤአ 770 ሽህ ጎብኝዎች ወደ ሃገራችን መጥተው ነበር፣ በ2015እኤአ 717 ሽህ ቱሪስቶች መጡ (በ60 ሽህ ቀነሰ) በ2016እኤአ 491 ሽህ ሃገር ጎብኝዋች መጥተው ነበር(279 ሽህ ጎብኝዎች ቁጥር ቀነሰ)፡፡ ከ2008 እስከ 2009ዓ/ም  ወያኔ  ‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ› አውጆ የነበረበት ዓማታት መሆኑን ልብ ይበሉ፡፡

በ2014 እኤአ ኢትዩጵያን የጎበኙ ቱሪስቶች ቁጥር 770 ሽህ  ሲሆን ከዘርፍ 730436 ሚሊዩን ዶላር ገቢ ተገኝቶ ነበር፡፡ የቱሪዝም ዘርፍ አስተዋፅኦ ለአጠቃላይ አገር ውስጥ ምርት(ጂዲፒ) 9.6 በመቶ እንዲሁም ለሥራ ዕድል 5.8 በመቶ አበርክቶ ነበር፡፡ በ2015አና 2016እኤአ የቱሪስቶች ቁጥር መቀነሱን፣የቱሪዝም ዘርፍ አስተዋፅኦ ለአጠቃላይ አገር ውስጥ ምርት(ጂዲፒ) መቶኛ እንዲሁም ለሥራ ዕድል መቶኛ ቀንሶል ይታያል፡፡ የተገኘው ገቢ መጨመሩን ግን ያሳያል ከሠንጠረዡ ማስተዋል ይቻላል፡፡ ከ2008ዓ/ም እስከ 2010ዓ/ም በተቀሰቀሰው የኦሮሚያ ህዝብ የአንገዛም እንቢተኝነት ትግልና የአማራ ህዝብ ተጋድሎ ምክንያት ወያኔ ‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ›› ምክንት የቱሪዝም ዘርፍ በቱሪስቶች ቁጥር መቀነስና  የዘርፍ አስተዋፅኦ ለአጠቃላይ አገር ውስጥ ምርት(ጂዲፒ) መቶኛ እንዲሁም ለሥራ ዕድል መቶኛ ቀንሶል ይታይ ነበር፡፡ ከዚህ መረጃ በመነሳት የካቲት 9 ቀን 2010 የታወጀው ‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ›› የሃገሪቱን ኢኮኖሚ ያሽመደምደዋል፣ የሆቴሎች ገቢ ይቀንሳል፣ የቱሪስት አስጎብኝ ድርጅቶች ገቢ ይቀንሳል፣ የውጪ ምንዛሪ ገቢ ይወድቃል፡፡

በ2008፣በ2009ና 2010ዓ/ም በኦሮሚያ ህዝባዊ እንቢተኛነትና በአማራ ህዝባዊ ተጋድሎ የግብርና የታክስ ገቢ ቀንሶል፣ ‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ›› ምክንት ለመከላከያ  ሠራዊቱ፣ የፖሊስ ኃይል፣ ሚሊሽያ ወዘተ ከመደበኛ በጀት ሌላ ከፍተኛ ወጭ ያስከትላል፡፡ በ2010እኤአ 14 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት አስከትሎል፡፡ ከህዝብ ታክስ መሰብሰብ ያልቻለ መንግሥት በህዝብ የተጠላ መንግሥት ነው፡፡ የስልጣን እድሜውም አጭር ነው፡፡ ህወሓት በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች ህዝብ ግብር በመሰብሰብ የንግዱን ህብረተሰብ ላይ ከፍተኛ ግብር በመጣል ህዝቡን በማሰቃየት ላይ ይገኛል፡፡  ወያኔ ‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ›› ዳግም በማወጅ በጉልበት ግብር ሊሰበስብ ይፈልጋል፣ የህዝብ ልጆች እየገደለ መግዛት ይፈልጋል፣ በሙስናና በኮንትሮባንድ ንግድ የከበሩ አይነኬ የጦር መኮንኖች በመላ ሃገሪቱ ህገወጥ የድንበር ዘለል ንግድ በመዘርጋት የሃገሪቱን ኢኮኖሚ አውድመዋል፡፡ ‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ›› የህዝቡን በነጻነት ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሶ የመስራት ኢኮኖሚ ነፃነት ያሳጣዋል፡፡ የወያኔ ኢፈርትና ሜቴክ ድርጅቶች ንግድን በወያኔ መንግሥት ሠራዊት እየተጠበቁ እንዲነግዱ ሲያመቻች የግል ዘርፉን ንግድ እንቅስቃሴ እንዲታሸግ፣ የግብር ጫናና አድሎ በኮማንድ ፖስቱ ይፈፀምባቸዋል፡፡ በዚህም የግሉ ዘርፍ ኢኮኖሚ፣ የንግድ መዛባትን በመፍጠር፣ ውድድርን በማክሰም፣ በመንግሥት እጅና ጥበቃ ከውድድር ውጭ ሆነው የሚተዳደሩ ድርጅቶች ይፈጠራሉ፡፡

ከ2008 እስከ 2009/2010ዓ/ም በኦሮሚያና አማራ ክልሎች በሁልም ክልሎች በተነሳ ህዝባዊ አመፅ የሃገር ውስጥ የባህር ማዶ ኢንቨስተሮች ንብረት የሆኑ ፋብሪካዎችና እርሻዎች መውደም ምክንያት የታቀደው አልተሞላም፡፡‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ›› የውጭ ንግድ ገቢ አሽቆለቆለ፣ በአንጻሩ የገቢ ንግድ ወጪ በማደጉ የንግድ ሚዛኑ ተናግቶል፡፡ በዚህም የተነሳ ያልተረጋጋ የብር ምንዛሪ ተመንና የውጭ ምንዛሪ ክምችት እጥረት፣ የመንግሥትና የልማት ድርጅቶች በዕዳ ክፍያ ጫና ተከስቶል፡፡ በአጠቃላይ  የአገሪቱ የፋይናንስና የባንክ ኢንዱስትሪው ልማቱ የሚጠይቀውን ፋይናንስ የማቅረብ ብቃት ወድቆ ነበር፡፡ በሃገሪቱ የፋይናሻል ዘርፍ ውድቀትና ኪሣራ ደርሶባቸዋል፡፡ በሃገሪቱ ኢኮኖሚ የዋጋ ግሽበቱንና የኑሮ ውድነቱን አባብሶታል፣ የውጪ ንግድ ገቢ በድርቅ ተመቶል፣ የውጭ ምንዛሪ እጥረት በጣም ተባብሶል፣ በእጥረቱ ምክንያት የኮንስትራክሽን ስራዎች በአብዛኛው ተቆርጠዋል፣ ሜጋ ፕሮጀክቶች ቆመዋል፣ በሃገሪቱ በታወጀው ‹አስቸኮይ ጊዜ አዋጅ› የተነሳ በባህር ማዶ ኢንቨስተሮች ሽሽት የተነሳ፣ ይደረግ የነበረው ቀጥተኛ የውጭ ኢንቨስትመንት ፍሰት አሽቆልቁሎል፣ የሆቴልና ቱሪዝም ገቢም ይነጥፋል፡፡ ከዚህ ባለመማር ወያኔ ዳግም ‹አስቸኮይ ጊዜ አዋጅ› አውጆል፡፡

የኢትዮጵያ ህዝብ በርሃብ፣በድህነት፣በበሽታ፣በስደትና በጦርነት አዙሪት ቀለበት ውስጥ ይገኛሉ፡፡ በሃገሪቱ ውስጥ የፖለቲካ መረጋጋት አለመኖር፣ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት አለማበብ፣ የመልካም መሪዎችና መልካም አስተዳደር እጦት፣ የስራ አጦች ብዛት፣ ገበያ መር የኃብት አጠቃቀም አለመኖር፣ የረዥም ግዜ  ኢንቨስትመንት እቅድ አለመኖር፣ የተትረፈረፈ ምርቶች ለውጭ ንግድ አለማምረት፣ የውጭ ምንዛሪ እጦት እንዲሁም የተረጋጋ የማክሮ ኢኮኖሚክ ስርዓት ዘላቂ ያልሆነ፣ ፊሲካልና ከዓለም አቀፍ ንግድ የውጭና የገቢ ንግድ የተዛባ ሚዛን፣  የንግድ ኪሳራ መሆን በችግር ቀለበት ውስጥ እንድትሽከረከር ያደርጋታል፡፡ይህን ችግራችንን ‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ›› እና ኮማንድ ፖስቱ አይፈቱትም፣ ከመካላከያ ሠራዊት መደበኛ የደሞዝ፣ የቀን አበል፣የትራንስፖርትና የነዳጅ ወጪ በጀት መጨመር ሌላ ለሃገሪቱ ኃብት አይጨምርም፡፡  ከመካላከያ ሠራዊት በሃገሪቱ ኢኮኖሚ ዘርፍ አምራች ሳይሆን እንደ ጥገኛ ተሃዋሲያን ሆኖ አምራች ኃይሉን የሚጣባ ወታደራዊ ዘርፍ ነው፡፡ ከግብርናው ዘርፍ አምራቹ ገበሬና ከማኑፋክቸር ዘርፍ ከላብአደር አምራች ከሚሠበሰብ ገቢ መንግሥት የግብርና የታክስ ቀረጥ ሰብስቦ ደሞዝ የሚከፈላቸው ናቸው፡፡ የህወሓት የጦር አበጋዞች መንግሥት፣ ‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ›› ወደ ሌላ ‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ››  መሸጋገር ኢትዩጵያ ከደካማ መንግስትነት (weak states)፣ ወደ ሚሰበርና የሚፈረካከስ ሃገር (fragile states)፣ብሎም ወደ ወደቀች መንግስት  (failed states) ጎራ የመቀላቀላችን ግዜ  በእርስ በእርስ ጦርነት እየተፋጠነ መምጣቱ  አይቀሬ ነው፡፡ ከዚህ የወያኔ የጥላቻ ፖለቲካ የሚከሰተው የዘር ፍጅት (የጀኖሳይድ) አዙሪት ቀለበት ውስጥ  ለመውጣት፣ ከዚህ ከማያባራ የህዝብ አመፅ፣ እንቢተኝነትና ተጋድሎ ለአንዴና ለዘለቄታው ለመውጣት፣ ብሄራዊ እርቅና የሰላም ጥሪ ውይይትና የዴሞክራሲ ስርዓት ሀ፣ሁ ለመገንባት የሽግግር መንግሥት መመሥረት ግዜው አሁን ነው፡፡ ‹‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ››  እንዲነሳ ህዝባዊው አመፅ በኢትዮጵያ ምድር ተቀጣጥሎ ወያኔ ይወገዳል፣ እንደ ግብፅ፣ ቱኒዚያ፣ ሊቢያ ህዝባዊ ትግል፣ ጭቁን መከላከያ ሠራዊት ከህዝብ ጋር ወግኖ ታሪክ እንደሠራ የእኛም ሠራዊት አፈሙዙን ወደ ገዥዎቹ አዙሮ ህዝባዊውን ትግል ይቀላቀላል፡፡

ዳክተር ፍቅሩ ማሩ፣ አንዳርጋቸው ፅጌ፣ መቶ አለቃ ማሽረሳ ሰጤ ይፈቱ!!!

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ›› በህዝብ ትግል ይነሳል!!!

ያለ ኢኮኖሚ ነፃነት የፖለቲካ ነፃነት የለም!!!

ኮማንድ ፖስቱ የሚወጣው የመከላከያ ሠራዊት በጀት ህዝባዊ አይደለም!!!

ሰው ሰው ያልሸተተ ልማት፣ መጨረሻው ጥፋት ነው!!!

የታሠሩ የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ!!!

የወያኔ ባለሥልጣኖች፣ አንባሳደሮችና ጀነራል መኮንኖች ኩብለላ ይቀጥላል!!!

የወያኔ ሹማምንቶችና የጦር መኮንኖች ወደ ወደ ሃገረ ቻይና ይኮበልላሉ!!!