በግብጽ በባቡር ግጭት በርካታ ሰዎች ህይወታቸው ማለፉ ተዘገበ

አባይ ሚዲያ ዜና

በሰሜናዊ ግብጽ በደረሰ የባቡር አደጋ በትንሹ 15 ሰዎች ህይወታቸው እንዳለፈ ከቦታው የሚወጡ ሪፖርቶች እየገለጹ ይገኛሉ።

በዚሁ የባቡር አደጋ ህይወታቸውን ካጡት በተጨማሪ ወደ 40 የሚጠጉ ሰዎች መጎዳታቸውን የትራንስፖርት ሚንስትሩ ቃለ አቀባይ ገልጸዋል።

አደጋው የተከሰተው ተሳፋሪዎችን የጫነ ባቡር ከካርጎ ባቡር ጋር በመጋጨቱ እንደሆነ ተዘግቧል። የአገሪቷ የትራንስፖርት ሚንስትር አደጋው የተከሰተበትን ቦታ እንደሚጎበኙ የአገሪቷ ካቢኔው ባወጣው መግለጫ አሳውቋል።

ባሳለፍነው ጥቅምት ወር በግብጽ በተከሰተ የባቡር ግጭት 42 ሰዎች ህይወታቸው ሲያልፍ ወደ 100 ሰዎች መጎዳታቸው ይታወሳል።