ያለው ምርጫ የፓለቲካ ስርዐት ለውጥ ብቻና የህወሃት ስልጣን ዘመን እንዲያከትም መታገል ነው፣ የርስዎስ (በሃይሉ አ.ተገኝ)

0

“ወታደራዊና የደህንነት መቃቅሩን፣ ፖለቲካዊ ስልጣንንና አኮኖሚያዊ የበላይነቱን ለራሱና በራሱ ቁጥጥር ስር አድርጎ የያዘን አፓርታይዳዊ ወያኔን የስልጣን ዘመኑ እስካላከተመ በስሩ ለሚቆጣጠራቸው እነዚህ መንግስታዊ መዋቅሮች ፍፁም ታማኝነት /pledge allegiance/ ለሌለው ወይም ለማይኖረው ግለሰብን ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ ከሾመ ስልጣኑን በፈቃዱ ለመልቀቅ ወስኗል ማለት ነው። ይህንን ካደረገም ህወሃት አምባገነን ሣይሆን ዲሞክራት ነበር ማለት ነው።

በህወሃት መዳፍ ስር ያሉት መንግስታዊ መዋቅሮች ሳይነኩና አፓርታይዳዊው ስርዐትና “የጎሣ ፌደራሊዝም’ ርዕዮቱ ሣይፈርስ፤ እንኳን እነ አቶ ለማ ወይም አቢይ ይቅርና፤ ክርስቶስ፣ ነብዩ መሃመድና ቡድሃ በጥምር (coalition of the the three) በህወሃት ስር በጠቅላይ ሚኒስትርነት ቢሾሙ መሠረታዊ ለውጥ ሊያመጡ ቀርቶ አይሞክሩትም። የሚኖራቸው ሚናም ህወሃት-ወያኔን በታማኝነት ማገልገል ብቻ ነው።

ፓለቲካው የዘነጋው ዋነኛ ጉዳይ ለጠቅላይ ሚኒስትርነት የታጩት እነዚህ ግለሰቦች በነፃና ፍትሃዊ ምርጫ የተመረጡ የህዝብ ተወካዮች ሣይሆኑ፤ ህወሃት ከራሱ ጋር ተወዳድሮ 99.6% በማግኘት “ያሸነፈው” ምርጫ ማግስት የሾማቸው ናቸው። ህወሃት ከአምስት ሚሊዮን ያነሰ ህዝብ ከሚኖርበት ትግራይ መጥቶ ፓለቲካውን የሚዘውረው አብላጫ ህዝብ ቁጥር ካላቸው ጎሣዎች እኩል 45 ድምፅ ይዞ ነው። ህወሃት በአንድ ጀምበር ጠፍጥፎ በአምሣያው ከሠራቸው ከመጠሪያቸው ቀጥሎ ‘ዴን’ ወይም ‘ዴድ’ ያላቸው የህወሃት ፓለቲካዊ የንግድ ድርጅቶች ናቸው። ክርስቶስን ያለክርስትና፤ ነቢዩ መሀመድ ያለ እስልምና ሃይማኖት በዲያቢሎስ ዓለም ቢመጡ ሊያራምዱ የሚችሉት የዲያቢሎስን አረመኔያዊ እምነትን እንጂ ዓለም የተቀበለውን የነርሱን ሃይማኖት ከቶውንም ሊሆን አይችልም።”

# ፓለቲካ የቀን ህልምን እንጂ፤ የቀን ህልም ፓለቲካን አይፈታም!

# የፓለቲካ ሹመኞችን በመቀያየር ፓለቲካዊ ስርዐትን መቀየርና ስርነቀል ለውጥ ማምጣት አይቻልም!

# የጥገና ለውጥ ህልምን ትተን ለዴሞክራሲያዊ ስርነቀል ለውጥና ለህግ የበላይነት መስፈን እንፋለም!