የሳውዲው አልጋ ወራሽ ልኡል መሀመድ ቢን ሳልማን ግብጽ ገቡ

አባይ ሚዲያ ዜና 

የሳውዲው አልጋ ወራሽ ልኡል መሀመድ ቢን ሳልማን  ለሶስት ቀናት ለሚቆይ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ወደ ግብጽ ማቅናታቸው ተዘገበ።

የአልጋ ወራሽነት ስልጣን ከተረከቡ ለመጀመሪያ ጊዜ እያደረጉ ባለው የውጭ አገር የስራ ጉብኝታቸው ልኡል መሃመድ ቢን ሳልማን ካይሮ ገብተዋል። አልጋ ወራሹ ከግብጽ ፕሬዝዳንት አብድል ፈታ አል ሲሲ ጋር ውይይት እንዳደረጉ እና በሁለቱ ሃገራት መካከል ያለውን ግንኙነት የሚያጠነክር ስምምነት ላይ እንደደረሱ ተነግሯል።

በሳውዲ ከሙስና ቅሌት ጋር በተያያዘ ክስ ባለሃብት ልኡሎችን እና ባለስልጣናትን በእስር እንዲቆዩ አልጋ ወራሹ ማድረጋቸው አይዘነጋም። 

በአገራቸው በቅርቡ የሚደረገውን የፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ያለ ብዙ ድካም እንደሚያሸንፉ የተነገረላቸው የግብጹ አብድል ፈታ አል ሲሲ የሳውዲ  አጋር እንደሆኑ ይታወቃል።

የሳውዲው አልጋ ወራሽ ከግብጽ ጉብኝታቸው በኋላ ወደ ብርታኒያ እና ወደ ዩናይትድ ስቴትስ እንደሚያቀኑ የሚወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ።