አባይ ሚዲያ ዜና
ቀማው ደባልቄ

እሁድ ማርች 4,2018 በሎስ አንጅለስ ከተማ በተካሄደው የአርበኞች ግንቦት 7 ህዝባዊ ስብሰባ ላይ የኢትዮጵያ ህዝብ የጀመረውን ህዝባዊ እንቢተኝነት ያለ የሌለ ሀይሉን አስተባብሮ በወያኔ ሀርነት ትግራይ የተጫነበትን የእልቂት አዋጅ እንዲሰብር አቶ ነአምን ዘለቀ የአርበኞች ግንቦት 7 የሥራ አስፈፃሚ አባል ጠይቀዋል።

አቶ ነአምን ዘለቀ በንግግራቸው ይህን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የአሜሪካን መንግስት በመቃወም ጠንካራ ተቃውሞ ከማቅረብ ጀምሮ የአውሮፓ ህብረት የስዊድን መንግስትና የተለያዩ መንግስታት ጭምርም አዋጁን በመቃወም የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ የፖለቲካ ቀውሶች ሁሉን አቀፍ በሆነ የብሔራዊ ውይይት እንዲፈታ ቢመክሩም ወያኔ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በሚሰጠው ህጋዊ ጭምብል መንግስታዊ ሽብርን ለማፋፋም፣ የህዝብን የለውጥ ፍልላጎት ለማዳፈንና ወደ ፍርሀት ቆፈን ውስጥ እከተዋለሁ በሚል ስሌት የስልጣን እድሜውንና የትግራይን የበላይነት በጉልበት ለማስቀጠል የታወጀ አዋጅ ነው ብለዋል ።

የህውሐት መራሹ አገዛዝ የህዝብን የለውጥ ትግል ለማዳፈን እየወስዳቸው የሚገኙት የሀይል እርምጃዎች አብዛኛውን የኢትዮጵያ ህዝብ የበታች አድርጎ ከ100 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ህዝብ ውስጥ 6%ፐርሰንት ብቻ የሆነውን የትግራይን ህዝብ እንወክላለን የሚሉ በአንጻሩ በኢትዮጵያ ውስጥ በሁሉም መንግስታዊ ተቋማት በፖለቲካው በኢኮኖሚው በንግዱ በወታደራዊና በደህንነት አንዲሁም በሌሎች ተቋማት “አይንን በጨው በታጠበና ምንም ሀፍረትም ይሉኝታም በሌለው አሳፋሪ ሁኔታ” የትግራይን የበላይነት ማስፈኑ ብቻ ሳይሆን በክፋትና በጭካኔ በወንጀልና በአብዛኛው የኢትዮጵያ ህዝብ ኪሳራ በዘረፋ የከበሩበት የደለቡበት የህውሃት አባላትና ደጋፊዎች በፍፁም ሊዋጥላቸው የሚችል የለውጥ ሂደት ባለመሆኑ ነው ሲሉ አቶ ነአምን ተናግረዋል

አቶ ነአምን ዘለቀ በንግግራቸው ላይ የኢትዮጵያ ህዝብ ህውሃት/ኢህአዴግን እንቢኝ አልገዛም ማለቱን መቀጠል እንዳለበት ከመግለፃቸውም በላይ በተለይ የትግራይ ህዝብም ከህውሃት መላቀቅ ያለበት ወቅት አሁን ነው ካሉ በኋላ በማከልም ህውሃት የትግራይን ህዝብ ከሌላው ኢትዮጵያዊው ወገኑ ለመለየት የሸረበውን ደባ በመበጣጠስ እንደሌላው ኢትዮጵያዊ ሁሉ ለለውጡ እንዲነሳ ጥሪ አቅርበዋል ።