የአማራ ገበሬን ትጥቅ የማስፈታት ዘመቻው ተጀምሯል

አባይ ሚዲያ ዜና
አቢሰሎም ፍሰሃ

ህዛባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ (ህወሃት) በበላይነት በሚቆጣጠረው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከዚህ በፊት በታወጅበት ጊዜ አማራን በሶስት ዙር ትጥቅ የማስፈታት ዘመቻ ጀምሮ እንዳልተሳካለት ይታወሳል።

በመጀመሪያ ዙር ትጥቅ ለማስፈታት የወሰነው የአማራ ልዩ ኃይልን ነበር። በመቀጥል የአማራ ሚሊሻዎች፣ ሶስተኛው እና የመጨረሻው ዙር ትጥቅ የማስፈታት ዘመቻው ያነጣጠረው የአማራውን ገበሬ ቢሆንም ገበርዎቹ በቀላሉ ትጥቅ የሚፈቱ ስላልሆኑ የማስፈታቱ ጉዳይ ለጊዜው በይደር የተተወ ነበር።

አሁን በድጋሚ ያወጁትን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተከትሎ ሶስተኛውንና የመጨረሻ ዙር ያሉትን የአማራ ገበሬን ትጥቅ የማስፈታት ዘመቻን አጠናክረው ከጀመሩባቸው ቦታዎች በጎጃም ይልማና ዴንሳ በጎንደር ታች አርማጭሆ በተጨማሪ ጋይት፣ ደብረታቦር፣ ፎገራ፣ እብናት፣ ሰሜን ጎንደር ሙሉ በሙሉ ለማስፈታት የታቀዱባቸው ቦታዎች ናቸው።

በሰሜን ጎንደር አረባያ በለሳ ውስጥ መሳሪያ ለመቀማት በተንቀሳቀሱ ወታደሮች እና በአካባቢው ነዋሪዎች መካከል ከፍተኛ የተኩስ ልውውጥ እንደነበረ የታወቀ ሲሆን በግጭቱም የሞቱ እና የቆሰሉ እንዳሉ የደረሰን መረጃ ያሳያል።

በተያያዥ ዜና የአማራ ወጣቶች ”ፋኖ” ይህን አማራን ትጥቅ የማስፈታት ህገ ወጥ ዘመቻ ለማስቆም በመላው አማራ ክልል ከፊታችን ሰኞ መጋቢት ሶስት ጀምሮ አድማ መጥራቱ ታውቋል።

ፋሽስት ጣሊያን ኢትዮጵያን እንደተቆጣጠረ ከሁሉ አስቀድሞ ያደረገው ነገር ቢኖር የኢትዮጵያን አርበኞች ያዳክማል ያለውን የትጥቅ ማስፈታት ዘመቻ ማካሄድ እንደነበር ታሪክ ያስታውሳል።