የኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ እና ተቀናቃኛቸው ራይላ ኦዲንጋ እርቅ ሊያወርዱ ነው

0

አባይ ሚዲያ ዜና
አቢሰሎም ፍሰሃ

የኬንያ ፕሬዚዳንት እና የተቃዋሚው መሪ ባለፈው ዓመት የተካሄደው ምርጫ ብዙ ህይወት ቢያስከፍልም የእርቅ ሂደት እንደሚጀምሩ ቃል ገብተዋል።

ከምርጫው በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ህዝባዊ ስብሰባ ያደረጉት ሁለቱ መሪዎች በኬኒያ ብሔራዊ ቴሌቪዥን ንግግር ማድረጋቸው ታውቋል። በንግግራቸውም ላይ ፕሬዚዳንት ኬንያታ ኦዴንጋን ወንድሜ ሲሉ ተደምጠዋል።

በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ ነበር ራይላ ኦዲንጋ እኔ የህዝብ ፕሬዜዳንት ነኝ ሲሉ ቃለ መሃላ በመፈጸም የሁሩ ኬንያታን አሸናፊነት ውድቅ ያደረጉት።

ሁለቱ ተፎካካሪዎች በህዝባቸው እና በውጭ ዲፕሎማቶች ሲቀርብላቸው የነበረውን የማግባባት ሙከራ ሳይቀበሉ መቆየታቸው ይታወሳል። 

ፕሬዝዳንት ኡህሩ ኬንያታ በአንድነታችን እና በልዩነታችን ላይ የመነጋገር ሂደቱን እንጀምራለን ሲሉ ኦዴንጋ በበኩላቸው ችግሮቻችንን ለመፍታት ጊዜው አሁን ነው ብለዋል። ከምርጫው ጋር በተያያዘ ከ150 ሰው በላይ መገደላቸው ይታወቃል።