የአለማችን የፊዚክስ ሊቅ ስቲፈን ሆኪንግ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

አባይ ሚዲያ ዜና
አቤኔዘር አህመድ

የአለማችን የፊዚክስ ሊቅ እንግሊዛዊው ስቲፈን ሆኪንግ በ76 ዓመታቸው ከዚህ አለም በሞት ተለዩ።

በመኖሪያ ቤታቸው ውስጥ ያረፉት እኚሁ የፊዚክስ ሊቅ “ሪላቲቪቲ” እና “ብላክ ሆልስ” በሚባሉ የፊዚክስ ስራዎቻቸው የሚታወቁ ሲሆን በርካታ የሳይንስ መፅሃፎችን ፅፈው ለዓለም አበርክተዋል።

እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ጥር 8᎖ 1942 ላይ በእንግሊዟ ኦክስፎርድ ከተማ የተወለዱት ስዪፈን ሆኪንግ በ22 ዓመታቸው ባጋጠማቸው የነርቭ ህመም ምክንያት ያለ ድጋፍ ሰጪ መሳሪያ መናገርም ሆነ መንቀሳቀስ አይችሉም ነበር።

ሞተር ኒውሮን ተብሎ በሚታወቀው የነርቭ በሽታ የተጠቁት እኚህ የፊዚክስ ሊቅ በወቅቱ፣ ከዚህ በኋላ በህይወት የሚኖሩት 2 ዓመት ብቻ ነው ተብለው ነበር።

የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ከኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ የተፈጥሮ ሳይንስ በማጥናት ያገኙት ስቲፈን ሆኪንግ የዶክትሬት ዲግሪያቸውን ደግሞ ከካንብሪጅ ዩኒቨርስቲ አግኝተዋል።