የኦሮሚያ ፍትህ ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ሃላፊ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተነገረ

አባይ ሚዲያ ዜና
አሰግድ ታመነ

በኦሮምያ ክልላዊ መንግሥት ፍትህ ቢሮ የኮምኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ፣ አቶ ታዬ ደንዳዓ፣ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተነገረ።

የፍትህ ቢሮ ኮምንኬሽን ጉዳዮች ሃላፊ አዲሱ ገበያ ከሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ወደ ሥራ ቦታቸው ሲያቀኑ በታጠቁ የፌደራል ፖሊስ አባላት እንደተያዙ ሪፖርቶች ያመለክታሉ። 

የመንግስት ወታደሮች በሞያሌ ከተማ በንጹሃን ነዋሪዎች ላይ በከፈቱት ተኩስ ያደረሱት እልቂት ሆን ተብሎ የተፈጸመ እንደሆነ የፍትህ ቢሮ ኮምንኬሽን ጉዳዮች ሃላፊ አስተያየታቸውን መስጠታቸው ይታወሳል።

በሞያሌ የደረሰውን ጭፍጨፋ መንግስት በስህተት እንደሆነ ቢገልጽም  አቶ ታዬ ደንዳዓ ግን መንግስት የተናገረውን ለማመን እንደሚቸገሩ በሰጡት መግለጫ አሳውቀዋል።

የፍትህ ቢሮ ኮምንኬሽን ጉዳዮች ሃላፊው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በመጣስ በሞያሌ የንጹሃን ኢትዮጵያኖችን ህይወት የቀጠፈውን የመንግስት እርምጃ በይፋ መኮነናቸው በኮማንድ ፖስቱ ለእስር ሊዳርጋቸው እንደቻለ ተንታኞች እየገለጹ ይገኛሉ።

የኦሮምያ ፍትህ ቢሮ የኮምኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ፣ አቶ ታዬ ደንዳዓ፣ በአሜሪካ እና በጀርመን ድምጽ ሬዲዮ በመቅረብ የመንግስት ወታደሮች በሞያሌ ስላደረሱት እልቂት መግለጫዎች መስጠታቸው ይታወሳል።