የአማራ ሕዝብን ማዕከል ያደረገ ህጋዊ ፓርቲ ለመመስረት ሲንቀሳቀሱ የታሰሩት 19 ሰዎች ተፈቱ

አባይ ሚዲያ ዜና
አቢሰሎም ፍሰሃ

የአማራ ሕዝብ ማንነቱን እና ጥቅሙን በተገቢው ሁኔታ ወክሎ ሊታገልለት የሚችል የፖለቲካ ፓርቲ ያስፈልገዋል በሚል ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዕውቅናን አግኝተው ህጋዊ የፖለቲካ ፓርቲ ለመመሥረት በእንቅስቃሴ ላይ እንዳሉ በመንግስት ፖሊሶች ተይዘው ላለፉት አስራ ሁለት ቀናት በእስር መቆየታቸውን በተደጋጋሚ እንደዘገብነው ይታወሳል።

ዛሬ 4 ኤፕሪል 2018 እኤአ ከስፍራው በደረሰን መረጃ መሰረት 19ኙም ታሳሪዎች ምንም አይነት ክስ ሳይመሰረትባቸውም ሆነ ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ በመታወቂያ ዋስ መፈታታቸው ታውቋል።

ከእስር ከወጡ በኋላ ሰላማዊና ሕጋዊ መንገድ ተከትለን የሰፊውን የአማራ ሕዝብ ጥቅም ለማረጋገጥ እስከመስዋዕት የደረሰ ዋጋ ለመክፈል ተዘጋጅተናል ሲሉ ተደምጠዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የዋልድባ አባቶችን እና የአማራ ወጣቶች ከፋሲካ በዓል በፊት ካልተፈቱ ከሚያዚያ 3, 2010 እስከ ሚያዚያ 6, 2010 የሚቆይ አድማ እና አመፆች የመላው አማራ ተጋድሎ በመላው አማራ ከተሞች መጥራቱን ይታወሳል።