ታዬ ደንደአ፣ ስዩም ተሾመ እና ኮ/ል ኢያሱ አንጋሱ ከእስር መፈታታቸው ተነገረ

አባይ ሚዲያ
በአሰግድ ታመነ

በኦሮሚያ ክልል  ተቀጣጥሎ ባለው የለውጥ ጥያቄ የተነሳ አሳባቸው ያለፍርሀት ሲገልፁ ከነበሩት መካከል በኮማንድ ፖስቱ በርካቶች የተገደሉ ሲሆን የቄሮን መሰረት አጠፋለው ብሎ የተነሳው የአገዛዙ ታጣቂዎች በርካቶችን ማሰሩ ይታወሳል።

ከታሰሩትም ውስጥ የአሮሚያ ክልል የፍትህ ቢሮ የኮሙኒኬሼን ጉዳዮች ኃላፊ የነበረዉ አቶ ታዬ ደንደአ: በአምቦ ዩኒቨርሲቲ መምህርና የድረ ገፅ ፀሐፊው አቶ ስዩም ተሾመ እና ኮ/ል ኢያሱ አንጋሱ ይገኙበታል።

የህዝቡ ንቅናቄ በፈጠረው ጫና ባሁን ሰሃት ታዬ ደንደአ፣ ስዩም ተሾመ እና ኮ/ል ኢያሱ አንጋሱ ከእስር መፈታታቸው  ተነግራል::

ለተፈቱትና ለመላው የነፃነት ታጋዩች እንኳን ደስ አላቹ።