የኢትዮጵያ አየር መንገድ አለም አቀፍ በረራ ሙሉ በሙሉ መቋረጡ ተነገረ

አባይ ሚዲያ ዜና
አሰግድ ታመነ

በአቪዬሽን ባለስልጣን የበረራ ተቆጣጣሪዎች ላይ ከዘር ጋር በተያያዘ በክፍያ እና አንዳንድ ጥቅማ ጥቅሞች በተለይም የአማራና የኦሮሞ ተወላጆችን በአገለለ መንገድ መሰራቱን በመቃወም የስራ ማቆም አድማ በማድረጋቸው በረራዎች ተስተጓጉለዋል።

ጥያቄ የሚያቀርቡትን በማሸማቀቅ፣ ከደረጃ ዝቅ በማድረግ፣ አልፎ አልፎም በማባረርና በማሰር ምላሽ መሰጠቱ የታወቃል። በቅርብ ቀን አየር መንገድ እና አቪዬሽን ያለው አሰራር እንደተለወጠና እጅግ በመተማመን እና ለሰራተኞች ምቹ እንደሆነ በመንግስት ሚዲያዎች በሰፊው ተዘግቧል። ይህ ዘገባ ሰራተኞቹን በእጅጉ እንዳስቆጣና በውሸት እኛን ሊነገድብን አይገባም በማለት ሁኔታዎች እንዲስተካከሉ በተደጋጋሚ ቢጠይቁም  ምላሽ የሚሰጣቸው በማጣታቸው ዛሬ የስራ ማቆም ማድረጋቸውና በዚህም አየር መንገዱ ሙሉ በሙሉ በረራ ማቋረጡ ተነግሯል።

በአየር መንገድ ከፍተኛ መተራመስ እና መጉላላት እየታየ ሲሆን እነዚህን ሰራተኞች ለማስፈራራት የተደረገው ሙከራ ባለመሳካቱ ወደ ልመና ቢገባም ምላሽ ካልተሰጠን አንሰራም ማለታቸው ተነግሯል።

ይህ ዜና እስከተጠናከረበት በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር አስከ ቀኑ 7.00 ድረስ በረራዎች መቋረጣቸው ታውቋል።