የወልድያ እግር ኳስ ቡድን የይግባኝ ውሳኔውን ዛሬ አግኝቷል

አባይ ሚዲያ ዜና
አቢሰሎም ፍሰሃ

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በወልድያ እና ፋሲል ከነማ መሃል በነበረው ጨዋታ ዙሪያ ያስተላለፈውን ውሳኔ እንደዘገብን ይታወሳል።

ውሳኔውንም ተከትሎ የወልድያ ከነማ የእግር ኳስ ቡድን ያቀረበው ይግባኝ ውሳኔ እንደተሰጠበት ታወቀ።

ውሳኔ
1. 250,000 ብር የነበረው የገንዘብ ቅጣት ወደ 150,000 ዝቅ ብሏል
2, ሜዳው ለአንድ አመት ውድድር እንዳይካሄድበት ተወስኖ የነበረው ቅጣት ወደ 3 ጨዋታ ዝቅ ሲልለት ክለቡ ከሜዳው ውጭ እንዲጫወት የተወሰነውም ቅጣቱ ቀንሶለታል።

ነገር ግን ክለቡን ስጋት ላይ የጣለው ውሳኔ የብሩክ አንድ አመት ቅጣት መጽናት እንደሆነ ሲታወቅ ፌደሬሽኑ የቅጣት አቁአሙን ለምን እንደቀየረ የታወቅ ነገር ባይኖርም አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች አሁንም ውሳኔው ፖለቲካዊ መሆኑን ይገልጻሉ።