‘ህገ ወጦች’ ተብለው ከቤንሻንጉል ክልል የተፈናቀሉት አማሮች ስቃይ ላይ መሆናቸው ተሰማ

አባይ ሚዲያ ዜና
አቢሰሎም ፍሰሃ

ጥቅምት 16 ቀን 2010 ዓ.ም በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል በሁለት ግለሰቦች ፀብ አንድ የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ተወላጅ በመገደሉ ምክንያት የተባረሩት 527 አባወራዎች ሲሆኑ በአጠቃላይ የቤተሳባቸው ብዛት ከሁለት ሺ በላይ መሆኑን ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የጻፉት ደብዳቤ ያሳያል።

እነዚህ ሀብት ንብረታቸውን ተዘርፈው የተባረሩት ተፈናቃዮች የክልሉ መንግስት ሕገ ወጦች ቢላቸውም ግብር የከፈሉበት ደረሰኝና የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ያላቸው መሆኑ ታውቋል። ተፈናቃዮቹ በባህር ዳር ጊዮርጊስ ቤተ ክርስትያን ተጠልለው የሚገኙ ሲሆን ከመካከላቸውም ስኳርን ጨምሮ በተለያዩ በሽታዎች የሚሰቃዩ ቢኖሩም ህክምና እያገኙ እንዳልሆነ ለማወቅ ተችሏል።

ባለፈው ጥር ወር ላይ በወልድያ፣ በቆቦ እና በመርሳ የትግራይ ክልል ወታደሮች በንጹሃን ላይ የወሰዱትን ጭፍጨፋ ተከትሎ አማራው ራሱን የመከላከል ርምጃ ሲወስድ ብአዴን የትግራይ ተወላጆች ተጠቁ ብሎ መግለጫ ማውጣቱ ይታወሳል።

ብአዴን ላለፉት 27 አመታት አማራ ባገሩ ስደተኛ ሆኖ ሲፈናቀልና ሲገደል ምንም አይነት መግለጫ አውጥቶ አለማወቁ እና አሁንም የዜጎች ጉዳይ በክልሉ ሚዲያ እንዳይዘገብ ማድረጉ ብዙዎችን አስቆጥቷል።