በዋሽንግተን ዲሲ ታላቅ ህዝባዊ ስብሰባ ተጠራ

አባይ ሚዲይ ዜና
ጋሻው ገብሬ

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የአርበኞች ግንቦት 7 ሊቀመንበር ከአቶ ነአምን ዘለቀ ጋር በመሆን በዋሽንግቶን ዲሲ ህዝባዊ ስብሰባ ላይ እንደሚገኙ ታውቋል። ሁለቱ የአርበኞች ግንቦት 7 መሪዎች  በዋሽንግተን ዲሲ ህዝባዊ ስብሰባ ላይ የሚገኙት ሜይ 20 ቀን 2018 ነው።

የአባይ ሚዲያ ቃል አቀባዮች ወቅታዊ የሆኑ የአገራችን ጉዳዮች የህዝባዊ ውይይቱ ይዘት እንደሚሆኑ አስረድተዋል። የኢትዮጵያ ህዝብ ዛሬ የዴሞክራሲ ትግሉ ከደረሰበት ደረጃ አያይዞ የሚኒሱ ወቅታዊ ጥያቄዎች መልስ እንዲያገኙ የሚሻ በመሆኑ የአርበኞች ግንቦት 7 የዋሽንግተን ዲሲ እና  የላስ ቬጋስ ቻፕተሮች  የሊቀመንበሩን ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋን አሜሪካ መገኘት አጋጣሚ ተጠቅመው ዝግጅቶቹን አድርገዋል በማለት ቃል አቀባዮቻችን ተናግረዋል።

በተመሳሳይ ፕሮግራም ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ሜይ 23 ቀን በላስ ቬጋስ ከተማ እንደሚገኙ ምንጮቻችን ገልጸዋል።