ቤኒሻንጉል – የደም ጎርፍና መፈናቀል (ሐይሉ አባይ ተገኝ)

በሰማዕታት ሣምንት የተተገበረ ወያኔያዊና አረመኔያዊ የዘር ማፅዳትና የዘር ፍጅት በቤኒሻንጉል እንመክት!

ወያኔ አማራን ማጥፋት የትግል ግቡ ያደረገው ዛሬ አይደለም:: ወያኔ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያውያንን የሚያየው በጣሊያን ዓይን ነው:: የሚገለውም ጣሊያን በቅርስነት ጥሎለት በሄደው ጭካኔና አረመኔነት ነው:: የዘር ማፅዳት ዓለማቀፋዊ ወንጀል ነው:: የተባበሩት መንግስታት የሴኩሪቲ ካውንስል ውሳኔ ቁጥር 780 የዘር ማፅዳት ወንጀልን “በአንድ የተወሰነ መመልክዐምድር የሚኖሩን ሲቪል የጎሣ አባላትን በተቀነባበረ ፖሊሲ በሌላ የጎሣ አባላት በማስጠቃትና በማሸማቀቅ ከሚኖሩበት መንደር ማፈናቀልና ማባረር ነው” ይላል::

ዛሬ ላይ ልክ እንደትላንቱ በተለይ በቤኒሻንጉል ክልል በአማራ ላይ ያነጣጠረ የዘር ማፅዳትና የዘር ፍጅት (Ethnic Cleansing & Genocide) ለምን ይፈፀማል? የዚህ ወንጀል አቀነባባሪ ህወሃት ወያኔ ነው:: ይህም ጂኦ-ፖለቲካዊ አንደምታ አለው:: የቤኒሻንጉል ክልል የተፈጠረው በወያኔ ከተቆረሰ የአማራ ክልል ነው:: የዘር ማፅዳትና የዘር ፍጅት የሚካሄደው በሚከተሉት ምክንያቶች ነው::

  1. በክልሉም የበርታ ጎሣ 25.41%፣ አማራ 21.69%፣ ጉምዝ 20.88%፣ ኦሮሞ 13.55%፣ ሺናሻ 7.73% እና 4.22% አገው – አዊዎች ናቸው::
  1. የህዳሴው ግድብ የሚገኘውም ቤኒሻንጉል ክልል ነው::
  2. የትግራይ ወያኔ ልክ እንደ ወልቃይት የነዋሪውን ቁጥር በዚህ የዘር ማፅዳትና የዘር ፍጅትዘዴ በመቀነስና በማጥፋት ድምፀ አልባ በማድረግ ይህን ክልል ከነግድቡ ወደትግራይ ለመጠቅለል በወያኔ በመወሰኑ በትግራይ ተወላጆች ሰፋፊ መሬቶችን መያዙን ቀጥሏል:: ይህም የተጠና ወያኔያዊ ፖሊሲ ነው:: ይህን የዘር ማፅዳትና የዘር ፍጅት ብአዴንን እንዲያስቆም መጠየቅም ለህወሃት ማመልከቻ ማቅረብም ነው:: የሟችን ገዳይ በገዳዩ ማስፈለግ ነው::

መፍትሄውስ:-

  1. የአማራው ህዝብ እራሱን ከጥቃት ለመከላከል እራሱን በታጠቁ ግለሰቦች ድንበር ዘለል የፈጥኖ ደራሽ ቡድን ከአጎራባች መንደሮች ማደራጀትና መመከት ነው::
  1. አፋጣኝ መፍትሄው ግን በመላው የአማራ ክልሎች ይህን የዘር ማፅዳትና የዘር ፍጅት በመቃወም የአድማ ጥሪ ሳይውል ሳያድር ተግባራዊ ማድረግን ይጠይቃል:: ለዚህም የሶሻል ሚዲያን መጠቀምን ይበጃል::

“It’s easier to resist at the beginning than at the end”

Leonardo da Vinci