ክቡር ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ:-ሕዝቡ ግን በደም-ድምፅ በትዕግስት እያደመጠዎት ነው፤በዕርግጥ አልተዋሹም (ዐቢይ ኢትዮጵያዊ)

0

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር አብይ አህመድ፣ለመንግሥትዎ የሚያደርጉለት ዕርዳታ ሁሉ ያስመሰግነዎታል፤ሕዝቡ ግን በደም-ድምፅ በትዕግስት እያነበበዎት ነው።

      ጥረትዎ ያበረታታል፤ዳሩግን ከሚፈሰው ደም እና ከሚገበረው ሕይወት አንፃር ሕዝብ በጉርሻዎ አይሞኝምና በጊዜዎት ያስቡበት።ከታሪክ ብዙ ተምረዋል ብዬ አምናለሁ፤በተግባር ግን ብዙዎች ያዩትን ያህል ያውቃሉ ብዬ አላምንም። ስለዚህም የትንሿን ብሎን(በምሳሌ በምድረ-እንግሊዝ የሚታወቀውን ልስጥዎትና ወደ መሠረታዊ ጥፋቷ እንገባለን።ንግስቲቱ ሰረገላዋን በሚጎትቱት ስድስት ፈረሶች ያልታወቀ ሰበብ ደንብረው እንድትከሰከስ በማድረጋቸው አደጋ ደረሰባት፤…የዚያ ሁሉ ጥፋት ግን ኮቴው ላይ ያለአግባብ የተመታው ሚስማር መጣመም ሆኖ ተገኘ።በዕውነተኛ ታሪኩ ውስጥ የነበረው ክስተት)በሶስት ሞቶ ገፆች መጽሐፍ ግን አልተጠናቀቀም፤ላሳጥረው ብዬ እንጂ።

   ክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴራችን ዶክተር አብይ አህመድ ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ፣ኮነሬል መንግሥቱ ኃይለማሪያምም ሆነ፣ፕሬዘዳንት ነጋሶ ጊዳዳ፣ፕሬዘዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስም አሊያም ፕሬዘዳንት ሙላቱ ተሾመ በሥልጣነ-መንበራቸው ላይ እንዳሉ፣ባገኙት አጋጣሚ በተቀመጡበት “ዙፋን” ወቅት የሰሯቸው ጥፋቶች ሁሉ በአንድ መሠረታዊ ጥፋት ምክንያት ላይ የተገነቡ ስለሆኑ መረገም ከጀመሩ አርባ አራት ዓመታት በላይ ሆኗቸዋል። በጠቅላይ ሚኒስቴሮች ላይ እየተላከከ{(ወቸገል ዜናዊ ለራሱ በሚያመቸው አሰራር የሰፋውን የስልጣን ጥብቆ)፣በፓርቲ ተንኮል እየታከከ ዛሬም ሊቀጥሉበት እና ጉደኞችን(ፕሬዘዳንት ተብለው)እንዳላዩ እንዳልሰሙ በማድረግ በመጎለት በሕዝብ ሥም ሲቀለድ ምንም የማይሉት ሳንናገር ሃያሰባት ዓመታት ስውር ምትሃት አስመስለናቸው}ቆይተናል፤እንገንዘበውና።እናም የነበሩት ሁሉም መሪዎችም ሆኑ ጠቅላይ ሚኒስቴሮች የሰሩት መሠረታዊ ስህተት ዲሞክራሲን መከልከላቸው ብቻ ሳይሆን የሕዝብ ንብረት እንደሆነ ዛሬም አለመገንዘባቸው ነው።

      ሁሉም የየዘመኑ መንግሥታት ነበርን ወይም ነን ባዮች ባለጊዜዎች፦የፈፀሙት የማይቀር ጥፋት ዲሞክራሲ ቢኖር ኖሮ ወዲያው በግልፅነት ይታረምና ያ መኩሪያችን የሆነው የሦስት ሺህ ዘመን የነበረን የሥልጣኔ ጉዞ ይቀጥል ነበር።

      በደም ሳይጨማለቁ፣የሰው ሕይወት ሳይቀጥፉ፣ወንበራቸው ላይ ሳይሸኑ፣በሥልጣናቸው ሕዝብ ላይ ሳያስታውኩ፣አፋቸው እንደከብት ተከፍቶ “ባአአ”እያለ ሳይጮሁና፣እንደ አህያ ሳያናፉ፣አሊያም በድድብና “ብላብላብላ”እያሉ ያለዕውቀት የሚያሰለቹ ማብራሪያቸውን ሳይሰጡ፣ሲብስም የቁንጥጫ አነጋገር ለአዋቂ እንደማይገባ ባማሩ አነጋገሮች እንዳይነገሩ፣ከጀግናና ቆራጥ መሪ መቅለስለሶች አይሰነዘሩም ነበር።ይልቅስ በግልፅነት ፍርጥርጥ፣ቅልብጭ፣ፍንትው በማድረግ መተማመን ይሆን ነበር እንጂ።

      እንደው መናገርና ማድረግ በተግባር የተለያዩ ቢሆኑም ሁለቱም የፈተናዎች እርከን አላቸውና ሊወዳደሩ አይገባም፤እንዲያውም በየፊናቸው ሊገመገሙ የግድ ይለናል።”ቃል…” አሉ ዶክተር አቢይ አህመድ፣እንደመጽሐፍ ቅዱሳችን አጀማመር፦”ቃል” ምን ያህል መለኮታዊ እና መሠረታዊ እንደሆነ ሲያብራሩልን፣ሃያል ነው ብለው ጠልቀዋል።የሳይንሳዊነቱንም አገላለፅ አልገፉበትም እንጂ “ቃል!” በአውሬዎች ላይ ቢሰማ ምን ያህል እንደሚያስደነግጥ ሁላችንም ልንገነዘበው እንችላለን። ዶክተር አቢይ በኦሮምኛ ለኢትዮጵያውያን ሲናገሩ ባይገባንም እንኳ የሰው ቋንቋ ነውና ቃል ነው፤ምንም እንኳን የቃሉን ትርጉም ለማናውቀው”ብላብላብላ…” ቢሆንብንም።ሌላ አገር ቢሰማ ከቛንቋነቱ ይልቅ በሰውነቱ ተቀባይነት ያግኝ እንጂ ባይረዱትም አያስገርምም። ቁምነገሩ ቃሉ ዋጋ የሚያገኘው ባልተጠበቀ ቦታ ለባለቤቱ ሲነገር ነው፤በትግርኛ ኦሮሞው ሲናገር ከተገኘ።እኛ ሰፈር ያለው ውሻ ገበያ ሄዶ ማንበልበሉን ቢሰሙ ለሰፈርተኛው እንግዳ ባይሆንም ይህ መሆኑን ባለሥልጣናት ቢያውቁ፦ወዲያው የሚታያቸው፦ ስንት ቱሪስት ወደ አገራችን መጥቶ ከተጎበኘ በኋላ የሚገኘው የምንዛሪው ብሊዮን ዶላር ነው፤ችግራቸው ነውና፣ለእኛ “ለሕዝቡ”ግን ፍጹም ይህ አይደለም የሚታየን። የምን ዶላር?የምን ጉድ?የምን ምንዛሪ?ሰው እየተገደለ…እየተራበ…እየታነቀ…ሕፃናት እየተደፉ..እየተቀበሩ…።

     ሕዝብ”ቃል”አወጣህ ተብሎ፣መናገር እየቻለ አፉ ሲለጎም፣ለምን ተናገርክ ተብሎ ሲገደል፣አየኸን ተብሎ ሲታነቅ፣ለምን አነበብክ ተብሎ በቁሙ ሲታረድ ነው የሚገርመንና እያወቅን ዝም የምንለው።ዶክተር አቢይ አህመድ ነገ ሕዝብ በተሰበሰበበት አደባባይ ስለዲሞክራሲ ሰፊ ማብራሪያ ሲሰጥ{(ለምን ማብራሪያ ያስፈልጋል?ዲሞክራሲ’ኮ የሕዝብ ነው።)ፊቱ ላይ ዝምብ ብታስቸግረው በግራ መዳፉ”እሽ!”ሲላት ድንገት ጉንጩ ላይ ተለጠፈችና ቀረች።ሕዝብ እያየው ነው፣ተለጥፋለች ሪዙ ላይ ግማሽ ጎኗ ቀርቷል፤ከሕዝብ መሃል አንዱ ድምፁን ከፍ አድርጎ ተነስቶ ጮኸ!ዶክተሩም ሰሙ መሃረብ አውጥተ ጠርገው ንግግራቸውን ቀጠሉና ጥያቄ ካላችሁ ብለው ቁጭ አሉ።ሌላው ተነሳና ይሄ ሁሉ ማብራሪያ ለዲሞክራሲ አያስፈልግም የኛው ልጅ ነው የመንግሥት አይደለም፤መንግስት ግን ሕዝብ የቀጠረው(የመረጠው) ሞግዚት ነው፤}ስለዚህ አታስረዳን አለና ተቀመጠ።ሹመት?ጉብኝት?ውይይት?ጭቅጭቅ?ብወዛ?በዲሞክራሲ ቤት ይሄ ሁሉ አያስፈልግም፤ሕዝባዊ መንግስት።

       ከዚህ ስዕላዊ ድርሰት መሰል መረጃ ምን እንገነዘባለን?የዲሞክራሲ እጦት ለሕዝብ የጥፋቶች ሁሉ መነሻ እና ለመንግሥት ግን የግንባታ ዕቃ ነው፤ ካልተጠቀሙበት ግን የማፍረሻ ዕቃ ሆኖ ይቀራል፤እናም ሕዝብ ሥልጣን አይፈልግም፤የኢኮኖሚ እምርታን አይሻም፤ የዶላር ምንዛሪም ሞልቷል፤የፖለቲካ ቡድኖችም ሞልተዋል::አንፈልግም:: የጦርና የመከላከያ እና የደህንነት ድርጅቶችን አንሻም::በቅድሚያ የራሳችንን ዲሞክራሲን ለሕዝብ እንጠቀምበት፤ነፃነታችን ነው።ይህ ካልሆነ ግን ከሚፈሰው ደም እና ከሚገበረው ሕይወት አንፃር ሕዝብ በጉርሻዎ  አይሞኝምና በጊዜዎት ያስቡበት።

ማሳረጊያ ትሁነን።

     xxx …የርግብ አትጠብቁ። xxx

እስኪ ለኢትዮጵያችን ዛሬን እንኳን ንቁ፤

ከእባብ እንቁላል የርግብ አትጠብቁ።

በጥራት ፃፉና፤

መረጃ አጣፉና።

ባገር ውስጥም ሆነ ካገር ውጭ ያሉ፤

የሕዝብ ደም ለመምጠጥ ዋግምት የተከሉ።

ለወያኔ ያደሩ፤…

በንግድ የሚሰሩ፤…

በየስም ሙያቸው ፃፉና ዘርዝሩ።

ለእኛም አሳውቁን እነሱም አያፍሩ፤

ካለም ፎቶግራፍ መረጃ ጨምሩ፤

በእጅጉ ይረዳል ሲመጣ የምሩ።

አትጠራጠሩ እንደ’ነዚህ ያሉ፤

የወያኔን ፍትፍት በደም ይበላሉ።

ፖለቲካ አይወዱም ለአገር አያስቡም፤

ገበያና ሽያጭ አውርተው አይጠግቡም።

እንደጣሊያን ቅዠት ማውራት ነው ግንባታ፤

ዶሮን ሲያታልሏት እንዳሞኟት ማታ።

እስኪ አናቱን በሉት ሙያውን አትፍሩት

በልሣን አሰሙን በብዕር ውገሩት።

ስንት አባቶቻችን ለመንፈስ ያደሩ፤

ያለሰው ዋጋ-ቢስ መሆኑን ሐገሩ፤

ነጻነት የእግዜር ነው ብለው እያስተማሩ፤

ዘመን አሻግረዋል ሳይፈርስ ድንበሩ።

በምን አንጀታቸው እንውረድ ይላሉ፤

የኛን ሥጋ በደም በጥሬው እየበሉ።

እኛው አስገድደን ሐቅ እያጋትናቸው ፤

ካልቀደምን በቀር ሞተን አናያቸው።

ስለዚህ እመኑኝ በመግደል አምነዋል፤

ዝም እንበላቸው? ? ?

በትዕቢት ተንኩለው፤

በእኛው ደም አብጠዋል።