ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ አገራት የዴሞክራሲ ትንቅንቅ እስከ 2022

0

አባይ ሚዲያ ዜና
ጋሻው ገብሬ

ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ አገራት የዴሞክራሲ ትንቅንቅ እስከ  2022

በዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ የአገር ፖሊሲ ነዳፊዎች በተለያዩ ርእሶች ጥናት አድርገው የሚያቀቡላቸው ብዙ የተለያዩ ተቋማት አሉላቸው። እነዚህን (Think tank) የሀሳብ ማዳበሪያ\የጥናት ማእከል ይሏቸዋል። ከነዚህ ተቋማት ስለ አገራት ስለ አሀጉራት፣ የፖለቲካ፣ የንግድ፣ የጸጥታ ጉዳዮችን አስመክልክቶ የረቀቀ ጥናት ለመንግስት ተቋማት ይቀርብላቸዋል። በህግ አውጭዎች ቢሮ የሚሰሩ ረዳቶች ደግሞ ከነዚህ ተቋማት የሚወጣውን መረጃ ጨምቀው ለአለቆቻቸው ያቀርባሉ።

ባለፈው ሜይ 23 ቀን ከሀሳብ ማዳበሪያ\የጥናት ማእከሎች ባአንደኛው አፍሪካ ነክ ዘገባ ቀርቦ ውይይት ተካሂዶ ነበር።

የአፍሪካ ነክ ዘገባውን ያቀረበው ሲ ኤስ አይ ኤስ (Center for Strategic Intelligence Service CSIS) አንዱ  የጥናት ተቋም ነው። ሲ ኤስ አይ ኤስ  በአራት ዓመታት አንዴ የዓለምን ሁኔታ የሚቃኝ መሪ ጥናት ያቀርባል። ይህ ተቋም የዛሬ ሀምሳ አመታት በፊት የተቋቋመ ነው። በዓለም አቀፍ ደረጃ በውጤቱ ታዋቂነት ያተረፈ ነው።

የዚህ ዓመቱ አንዱ ሲ ኤስ አይ ኤስ  ዘገባ ስለ አፍሪካ አሀጉር ነው። ከሰሃራ በታች ባሉ አገራት የዴሞክራሲ ትንቅንቅ እስከ  2022 ዓ ም ተብሎ ለህዝብ የቀረበ ዘገባ ነው። (Sub-Saharan Africa: Pitched Contests for Democratization Through 2022)

ሪፖርቱ የሚከተሉትን ይዟል፡

  • ከሰሃራ በታች ያሉ አገራት ለየት ወዳለ ጊዜ እየተዛወሩ ነው።በመንግስታት እና በህዝቦች መካከል ዴሞክራሲን አስመልክቶ ትንቅንቅ ጨምሯል። ይህም እስከ 2022 ዓም በቀጣይ ሁኔታ ውጥረትን የሚያስከትል ነው።
  • የሀይል ሚዛን በአገራት ዋና መሪዎችና የመንግስት ተቋማት መካከል በፈረቃ ይዘዋወራል።ይህም በዴሞክራሲ መስፈን ላይ እስከ 2022 ዓ.ም ጫና ይኖረዋል። አንዴ ዴሞክራሲያዊ አንዴ አምባገነንነት መገላበጦች ይኖራሉ።
  • ከላይ ባለው ሁኔታ የተነሳ ምራቡ ዓለም ከአፍሪካ ህዝቦች “እንትዳኙንም ወይ” የሚል አቤቱታ በዴሞክራሲ ጉዳይ ይመጣበታል። ለምእራቡ ነባር ወዳጆች የሆኑ አምባገነኖች ሳይቀሩ ምራቡ ዓለም ላይ ኩርፊያ ሊኖራቸው ይችላል፤ በወስጠ ጉዳያችን ገባችሁ በማለት።
  • ሆኖም ግን ምራቡ ዓለም የዴሞክራሲ መስፋፋትን ባንድ በኩል ደግፎ በሌላ ደግሞ ስትራቴጅያዊ የጸጥታ ግቡን፤ሽብርተኝነትን ለመዋጋት ያለውን ዓላማም ማሳካትን ሁለቱንም ሊቀናው ይችላል።
  • በአፍሪካ ያሉ አምባገነን መንግስታት በተለይ ከምራቡ “ሽብርተኛነት ለመዋጋት” በሚል ሰበብ እርዳታ የሚያገኙት እርዳታውን የራሳቸውን በግዛት ዘመን መሰበቻ ጨቋኝ የጸጥታ ተቋም ይገነቡበታል። ብዙ አገራት ኢትዮጵያንም ጭምሮ ጋምቢያ፤ጋና፤ናይጄሪያ፤ደቡብ አፍሪካ፤ታንዛኒያ፤ኡጋንዳ እና ዜንባብዌ እንዲህ ያሉ ናቸው። ይህን የሚያጋልጡት መልካም ግምት የሚሰጣቸው የሰባዊ መብት ጥሰት የሚከታተሉ ተቋማት ናቸው።
  • በኬንያ፣ ኒጄር፣ናይጄሪያ፣ ህዝብ በገፍ ይታሰራል። ያለፍርድ ይሞታል። ሰቆቃ መፈጸም የመንግስት የለት ተለት ስራ ነው። ኢትዮጵያና የኬንያ መንግስታት በዚሁ መልክ ተገልጸዋል።
  • ዴሞክራሲ በሚገባ ከሰፈነ በአፍሪካ የፌዴራል ስራት ይመረጣል ይላል ምራቡን ዓለም አስተሳሰብ ሲያጸባርቅ
  • ስለአፍሪካ ስንናገር ስለመጭው ዓለም እየተናገርን ነው። በ2050 ከዓለም 25% የህዝብ ብዛት አፍሪካ ነው በማለት ያስገነዝባል።

ሙሉውን(የእንሊዝኛ) ጽሁፍ እና ሙሉ ዘገባ ከዚህ በታች ባለው መስፈንጠሪያ ማግኘት ይቻላል።

Trends In Democratization In Sub – Saharan Africa

https://soundcloud.com/csis-57169780/trends-in-democratization-in-sub-saharan-africa

https://csis-prod.s3.amazonaws.com/s3fs-public/event/Sub-Saharan%20Africa%20-%20Pitched%20Contests%20for%20Democratization%20Through%202022.pdf?6UWIeJSC9.Vvm6pibQ_fw60IfEvUP_2N