የግብርና እና እንስሳት ሚኒስቴር አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ሙስና ሲጋለጥ

0

ዜና
አቢሰሎም ፍሰሃ

በቀድሞው ትምህርት ሚኒስትር እና የደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት፣ የአሁኑ የግብርና እና እንስሳት ሚኒስቴር አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ባለቤትነት እና የአክሲዮን ድርሻ እንዳላቸው የሚታወቀው ይርጋለም ኮንስትራክሽን ወልቂጤ ዩኒቨርስቲ ውስጥ በሚሰሩ የኮንስትራክሽን ስራዎች ላይ በከፍተኛ ሙስና ደረጃውን ያልጠበቁ ግንባታዎች እየፈጸመ መሆኑን የኬርሻዶ ምንጮች ጠቆሙ።

አንድ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ገለሰብ የአቶ ሽፈራው የሙስና ሰንሰለት እስከ ወረዳዎች ድረስ የተዘረጋ ነው ብለዋል። ለዚህ ዋንኛ ማሳያ ደሞ በሳቸው የሚተዳደረው ይርጋለም ኮንስትራክሽን ነው ሲሉ ይገልጻሉ።

ይርጋለም ኮንስትራክሽን በጉራጌ ዞን እና እንዲሁም በወልቂጤ ዩኒቨርስቲ ውስጥ የተለያዩ ጨረታዎችን እያሸነፉና ከደረጃ በታች የሆኑ ስራዎችን እያቀረቡ ገንዘብ እየዘረፉ ይገኛሉ።

የወልቂጤ ዩኒቨርስቲን በምሳሌነት የጠቀሱት የኬርሻዶ ምንጮች፤ የወልቂጤ ዩኒቨርስቲ ኮብል ስቶን በነበረ ጊዜ ኮብልስቶን ሲያነጥፍ የነበረው ይርጋለም ኮንስትራክሽን ነው፤ በ12 ሚሊየን ብር የዩኒቨርሲቲው መግቢያ በር የሰራውም ይርጋለም ኮንስትራክሽን ነው፤ በ 800 ሚሊየን ብር አዲስ የሚሰራውን የአስተዳደር ህንጻ የሚገነባውም ይርጋለም ኮንስትራክሽን ነው ብለዋል።

ይርጋለም ኮንስትራክሽን ይሄንን ሁሉ ግንባታዎች ሲያከናውን ፣ ከጉልበት ሰራተኛ እስከ መሀንዲስ ያለው የሲዳማ ተወላጅ ብቻ መሆናቸውን በመናገር ይርጋለም ኮንስትራክሽን ማለት አንድ ኮንትራክተር ሳይሆን የዩኒቨርሲቲው የግንባታ ክፍል ነው ማለት ይቀላልም ብለዋል። 

የዚህ ሁሉ የሙስና ሚስጥር የዩኒቨርሲቲው የቦርድ አባል የሆኑ ከፍተኛ ባለስልጣናት ፣የዩኒቨርስቲው አመራሮችና የደኢህዴን ካድሬዎች በጥቅም መተሳሰር ጭምር መሆኑን ጠቁመዋል።

ይሄ ይርጋለም ኮንስትራክሽን የተባለ ተቋራጭ ከዚህ በፊት ሃላባ ወረዳ ውስጥ ከሙስና ጋር ተያይዞ ችግር የነበረበት ሲሆን፣ እንዲሁም በደቡብ ኦሞ ጂንካ ከተማ በ2003 ዓ/ም በ20 ሚሊየን ብር የገነባው ስታዲየም በሁለት አመቱ መደርመሱ ይታወሳል።