የአማራን ህዝብ መሰረታዊ ግልጋሎቶችን በመከልከል የፋሽስት ትህነግ በአማራው ህፃናት ላይ ያደረሰው ኢሰብአዊ ድርጊት ሲጋለጥ (በአምባ የአማራ ባለሙያዎች ማህበር)

 የአዮዲን እጥረት ችግር ምንድን ነው?

አዮዲን በተፈጥሮ በውሃና በአፈር ውስጥ የሚገኝ ንጥረ ነገር ነው። አዮዲን በባሕር ውስጥ በብዛት የሚገኝ ንጥረ ነገር ሲሆን በመሬት እና በንጹህ ውሃ ላይ ያለው ስርጭት ግን ከቦታ ቦታ ይለያያል። በጊዜ ብዛት በአፈር ውስጥ ያሉት የተፈጥሮ ንጥረ ነገሮች መመናመን የአዮዲንንም መጠን በከፍተኛ ደረጃ የቀነሰው በመሆኑ በርካታ የኢትዮጵያ መሬት በተለይም ተራራማው የሆነው የዐማራ መኖሪያ ቦታዎች የተፈጥሮ አዮዲኑ ተመናምኗል። ስለዚህም በአለም በሙሉ እንደሚደረገው ለህዝብ በሚቀርበው ጨው ላይ አዮዲን መጨመር የተለመደ ነው። በቂ አዮዲን ያላገኙ ሰዎች የታይሮይድ ሆርሞን እጥረት (hypothyroidism) ያጋጥማቸዋል ውጤቱም የታይሮይድ ዕጢ እብጠት (እንቅርት) ይሆናል። ይህም በህጻናት ላይ ሲደርስ እድገትን ያቀጭጫል፤ የአእምሮ እድገትን በከፍተኛ ደረጃ ይጎዳል።

የአዮዲን እጥረት በዓለም አቀፍ ደረጃ የአእምሮ ዝግመት እና የማይመለስ ከፍተኛ የአንጎል ጉዳት ከሚያደርሱት ዋነኛው መንስኤ ነው። የአዮዲን እጥረት ከፍተኛ ጉዳት የሚያደርሰው ነፍሰጡር እናቶች በቂ አዮዲን ሳያገኙ ሲቀሩና ህጻናት ከተወለዱም በኋላ በጨቅላ እድሜያቸው ወቅት ነው። የእናቶች አዮዲን እጥረት የፅንስ መጨንገፍና ሌሎች የእርግዝና ችግሮች ለምሳሌ ያለጊዜው መወለድ እና መሃንነት የመሳሰሉትን ሊያስከትል ይችላል። የአዮዲን እጥረት ለልጆች የመማርና የማሰብ ችሎታ (IQ) በከፍተኛ ደረጃ መቀነስ ዋነኛ መንስኤ ነው።በኢትዮጵያ በተለይም የ “አማራ ክልል” በተባለው አካባቢ እጅግ በጣም በርካታ ህጻናት በወቅቱ በቂ አዮዲን ባለማግኘታቸውና ለአዮዲን እጥረት በመጋለጣቸው ምክንያት እድገታቸው ቀጭጯል ለአእምሮ ዝግመትም ተዳርገዋል።

የትህነግ(ወያኔ) አምባገነን ሥርአት ስልጣን በሚቆጣጠርበት ጊዜ ሁኔታው ምን ይመስል ነበር?

ኢትዮጵያ እኤአ በ1990ዎቹ መጀመሪያ አካባቢ በዓለም ዙሪያ አዮዲን ያለው ጨው ማምረት ከጀምሩት አገሮች አንዷ ነበረች ፤ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ከ80% በላይ የሚሆኑት የኢትዮጵያ ቤተሰቦች አዮዲን ያለው ጨው ያገኙ ነበር። ይህም የተቻለው ቀደም ሲል አሰብ ወደብ ላይ በተተከሉት የአዮዲን ማምረቻ ማሽኖች አማካኝነት ነበር። ስለዚህ ወያኔ ሲረከባት ኢትዮጵያ አዮዲን ያለው ጨው አቅርቦትን ሙሉ በሙሉ ለማዳረስ ተቃርባ ነበር።

እኤአ ከ2000 እስከ 2012 ምን ተከሰተ

የትኞቹ ትህነግ(ወያኔ) የፈጠራቸው “ክልሎችስ” በወያኔ እንዝላልነትና በቀልተኛነት ምክንያት ከባድ ጉዳት ደረሰባቸው?

የኢትዮ-ኤርትራ የፖለቲካ ግጭት የአሰብ ወደብን ከጥቅም ውጭ አደረገው። በዚህም ምክንያት የኢትዮጵያ የአዮዲን ጨው አቅርቦት ተስተጓጎለ።   በአጠቃላይ እኤአ በ2005 አዮዲን ያለው ጨው የሚያገኙ ቤተሰቦች ከነበረው 80% ወደ 4.2% አሽቆለቆለ። (ብሄራዊ Micronutrient Survey 2005)። በዚህም ምክንያት ኢትዮጵያ በአለም በጣም ዝቅተኛ አዮዲን ያለው ጨው ከሚያቀርቡ አገሮች ምድብ ውስጥ ገባች። የኢትዮጵያና የኤርትራ ግጭት እየተባባሰ ሂዶ ሁለቱ አገሮች ወደጦርነት ሲገቡ እና የአሰብ ወደብን አዮዲን ያለው ጨው ማምረቻ ፋብሪካ ጥቅም ላይ መዋል አለመቻሉ በግልጽ እየታወቀ ሲመጣ ዩኒሴፍና ሌሎችም አጋሮች የሚከተሉትን እርምጃዎች ወሰዱ።

እኤአ በ2003 በአራት “ክልሎች” የሚገኙ የጨው አምራች ማህበራት አዮዲን ያለው ጨው ማምረት እንዲችሉ የማሽኖች እርዳታና ስልጠና ተሰጣቸው ከጤና ጥበቃ ሚኒስትር ጋርም ስምምነት ተፈራረሙ ፤ አዮዲን ያለው ጨው ማምረትም ጀመሩ። ይህም ጥረት አዮዲን ያለው ጨው አቅርቦትን በከፍተኛ ደረጃ ወደነበረበት እንደሚመልሰው እምነት ተጥሎ ነበር። ሆኖም በጤና ጥበቃ ሚኒስትር በነበረው የአመራር ለውጥ ምክንያት ማለትም የትህነግ ከፍተኛ አመራር አባል የሆኑት ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም የጤና ጥበቃ ሚኒስትር መሆናቸውን ተጠቅመው ስምምነት ያደረጉት የቀድሞ የትህነግ (ወያኔ)ታጋዮች የአሁኖቹ ጨው አምራቾች ስምምነታቸውን አፍርሰው አዮዲን የሌለው ጨው ማምረትና ማከፋፈል እንዲችሉ ጠየቁ፡ ሚኒስትሩም ፈቀዱላቸው። በሚኒስትሮች ምክር ቤት አዮዲን የሌለው ጨው እንዳይሰራጭ ያግድ የነበረውም ህግም ታገደ። በዚህም ጊዜ ይህ አደገኛ እርምጃ ያሳሰባቸው ባለሙያዎች የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ ሀሳባቸውን እንዲቀይሩ፤ ህጉ ባለበት እንዲቀጥልና ጨው አምራቾችም አዮዲን ያለበት ጨው ብቻ እንዲያከፋፍሉ እንዲያደርግ ቢያሳስቧቸውም ሊቀበሉ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ይሀው ህግ እኤአ እስከ 2012 ድረስ ማለትም ለ8 አመታት ያህል ታግዶ ቆይቷል።  ኢትዮጵያውያን እንደገና አዮዲን የሌለው ጨው መጠቀም ግዴታቸው ሆነ። በዚህም ምክንያት አዮዲን ያለው ጨው አቅርቦት በከፍተኛ ደረጃ ቀነሰ፤ ስለሆነም እኤአ በ2005 ከ100 ሰዎች መካከል 40ዎቹ ለእንቅርት በሽታ ተዳርገው ነበር። እንቅርት ከፍተኛ የአዮዲን እጥረት ምልክት ሲሆን ከፍተኛ የአዮዲን እጥረት የህፃናትን የአእምሮ እድገትን ያቀጭጫል። የሚገርመው አብዛኛው ኢትዮጵያውያን ስለዚህ ክስተት ግንዛቤ የሌላቸው መሆኑ ነው።

ምስል 1: አዮዲን ያለው ጨው ስርጭት በኢትዮጵያ

file1

የ“አማራ ክልል” ባሉት ውስጥ በአማራ ህጻናት ላይ የደረሰው ጉዳት ምን ይመስላል?

በ “አማራ ክልል” በቡሬ እና ወምበራ ወረዳዎች ውስጥ በተደረገ ጥናት 54% የሚሆኑት ህጻናት የእንቅርት በሽታ ነበራቸው። በአለም አቀፍ ደረጃ ከ30% በላይ የሆኑ ህጻናት በአዮዲን እጥረት ተጠቂ ከሆኑ ከፍተኛ የአዮዲን እጥረት መኖሩን ማረጋገጫ ነው። እንዲሁም በሌላ ሁሉንም “ክልሎች” በሸፈነ ጥናት በ “አማራ ክልል” ከተባለው ውስጥ ከሚገኙ ቤተሰቦች ውስጥ 90% የሚሆኑት አዮዲን የሌለው ጨው ያገኙ የነበረ ሲሆን በ“ክልሉ” 10% ብቻ አዮዲን ያለው ጨው ያገኙ ነበር። በተጨማሪ በ2007 በተደረገ አንድ ብሔራዊ ጥናት እንዳረጋገጠው ከ6 እስከ 12 ዓመታት እድሜ ያላቸው ህፃናት በጠቅላላው ከ4 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ በእንቅርት በሽታ በኢትዮጵያ ተጠቅተው ተገኝተዋል።

የአዮዲን እጥረት በነበረባቸው አመታት የተወለዱትና ጉዳት የደረሰባቸው ህጻናት በአሁኑ ጊዜ እድሜአቸው ከ6 እስከ 13 አመታት የሚሆናቸው ሲሆን በሌላ አነጋገር በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ያሉ በመሆኑ የሚመለከታቸው የትምህርትና የእድገት ክትትል ባለሙያዎች ጥናት ቢያደርጉ የጉዳቱን መጠን ለመረዳትና ምናልባትም ልዩ እገዛ የሚያስፈልጋቸውን ልጆች ለመለየትና የተቻለውን ያህል እርዳታ ለማድረግ ያስችል ይሆናል። ህፃናት የወደፊት ተረካቢ እና ተስፋዎች እንደመሆናቸው በተለይ የ“አማራ ክልል” የተባለው ውስጥ ያሉ የአማራ ህፃናት የአዮዲን እጥረት ከፍተኛ ተጠቂዎች እንደመሆናቸው እና የትህነግ መንግስት ደግሞ ዐማራን ጠላት ብሎ የፈረጀ ድርጅት እንደመሆኑ ትህነግ ዐማራን ሊጎዳ ሁሉን ነገር ስለሚያደርግ ሃላፊነት የሚሰማው ሁሉ ይህ የዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም እና አጋሮቻቸው የዐማራ ልጆችን ትህነግ(ወያኔ) ትውልድን የማጥፋት እኩይ አላማ ሰለባ እንዳይሆኑ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶት ወጣቱን ትውልድ የደረሰበትን የአእምሮ ጉዳት ማዳን እንኳን ባይቻል ቢያንስ የተሻለ ውጤታማ እንዲሆኑ ርብርብ ማድረግን ይጠይቃል።

ምስል 2: በ “ክልሎች” በየቤተሰቡ የነበረው አዮዲን ያለው ጨው ስርጭት

file2

የትህነግ(ወያኔ) “መንግሰት” ለምን በጊዜው እርምጃ አልወሰደም?

ከተለያዩ ከመንግስትና መንግስታዊ ካልሆኑ መስሪያ ቤቶች የተውጣጡ ባለሙያዎች ይህ አዮዲን የሌለው ጨው እንዲከፋፈል የሚፈቅደው እርምጃ አደገኛ መሆኑን፤ አዮዲን የሌለበት ጨው ለህዝብ መከፋፈል እንደሌለበት በየጊዜው ለማስረዳት ሞክረው ተቀባይነት አላገኙም። ይህ ጥፋት የደረሰው አዮዲን ያለው ጨው ማምረት ስላልተቻለ ወይም አዮዲን ያለው ጨው ለመግዛት የገንዘብ እጥረት አጋጥሞ አይደለም። እንደሚታወቀው የትህነግ (ወያኔ) መንግስት ለቱባ ባለስልጣናቱ በርካታ የቅንጦት እቃዎችን እና ውድ መኪናዎችን ጨምሮ በርካታ ውድ ነገሮችን በየጊዜው ይገዛል። ይህ አዮዲን የሌለው ጨው ሊከፋፈል የቻለበት አንዱና ዋነኛው ምክንያት አዮዲን የሌለው ጨው አቅራቢዎቹ የቀድሞ የትህነግ(ወያኔ) አባላት በመሆናቸው ትውልድን ገድሎም ቢሆን ደጋፊዎቻቸውን ለመጥቀም በማሰብ ይመስላል። በሌላ በኩልም የ ትህነግ (ወያኔ) ባለስልጣናት አገር የሚመሩት በእውቀታቸው ህዝብ መርጧቸው ሳይሆን በጠመንጃ ሃይል ከያዙት ስልጣናቻው የሚመነጭና የባለሙያ ምክርንም ለመቀበል ፈፅሞ ፍላጎት የሌላቸው በመሆናቸው ነው። ይህ በአለም አቀፍ ደረጃ የሚያስጠይቅ ወንጀል ሆኖ ሳለ የዚህ ወንጀል ዋና አስፈጻሚ የነበሩት የወቅቱ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ለፍርድ ቀርበው የእጃቸውን ማግኘት ሲገባቸው እነሆ አለም ፍርደ ገምድል ሆነችና የቀድሞው ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ለፈፀሙት ኢሰብአዊ ወንጀል መጠየቅ ሲገባቸው እንዲያውም ተሹመው ባሁኑ ሰአት የአለም የጤና ድርጅት ሃላፊ ሆነው ተሹመው እየሰሩ ነው። ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖምም ሆኑ ትውልድን አብረው ያጠፉ ተባባሪዎቻቸው በአለም አቀፍ ፍርድ ቤት መዳኘት ሲገባቸው ዛሬም ድረስ ማንም ሳይጠይቃቸው የኢትዮጵያ ህዝብም የፍትህ ያለ እንዳለ እስካሁን ድረስ አለ።

አምባ የአማራ ባለሙያዎች ማህበር የዚህ ወንጀል ፈፃሚዎች ለፍርድ እንዲቀርቡና ከዚህ በኋላ ተመሳሳይ ትውልድን የሚጎዱ ወንጀሎች እንዳይፈፀሙ ከሚመለከታቸው ጋር በመሆን ፍትህ እንዲሰፍን የተቻለውን ሁሉ ጥረት ያደርጋል።

አምባ የአማራ ባለሙያዎች ማህበር

ግንቦት 2010

ዋሽንግተን ዲሲ፤ የተባበሩት የአሜሪካ ግዛቶች