ኢትዮጵያ ባድሜን በስምምነቱ መሰረት ለኤርትራ አስረክባለሁ አለች

0

አባይ ሚዲያ ዜና
ሱራፌል አስራት

የኢትዮጵያ መንግስት ከአሁን በፊት በቀድሞው ጠቅላይ ሚንስቴር መለሰ ዜናዊና በኤርትርው ፕሬዘዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በአልጀርስ ላይ የተደረገውን ስምምነ ወደተገባር ለመቀየር ዝግጁ ነኝ ማለቱ ታወቀ። የኢህአ ዴግ ማእከላዊ ኮሚቴ ትላንት ማክሰኞ ባካሄደው ስብሰባ ላይ ከኤርትራ ጋር ለወደፊቱ ለሚደረገው የሁለትዮሽ ስምምነት የአለጀረሱን ስምምነት መቀበል የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ወደተሻለ ደረጃ ከፍ ያደርገዋል ሲል በድርጅቱ መግለጫ አሳታውቋል።

እንደ ፈረንጆች አቆጣጠር ከ 1998 እስከ 2000 አም በሁለቱ ሀገሮች በተደረገው አስከፊ ጦርነት ከሁለቱም ሀገራት ከ 70 ሺ ወታደሮች በላይ አንደተገደሉ የተለያዩ መረጃወች ይጠቁማሉ። ከጦርነቱም በሆላ ሁለቱን ሀገሮች ለማስማማት በተደረገው ጥረት በሚያዚያ 13, 2000 አም ሄግ ኔዜርላንድ በሚገኘው የቋሚ ግልግል ህጋዊ ኮሚቴ አጨቃጫቂ የሆነውን የባድሜ ቦታ ለኤርትሪያ ይገባታል ብሎ ፍርድ መስጠቱ ይታወቃል። ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ መንግስት ባድሜን አላሰረክብም በማለት በሁለቱ ሀገረት ፍጥጫው ለለፉት 18 አመታት እንደቀጠለ ይታወቃል።