ለባድመ መሬት ደረቴን አልመታም! (ሐይሉ አባይ ተገኝ)

0

(ኦሮማይ!)

“እምባ እምባ ይለኛል፣ እምባ ከየትአባቱ፣

ደርቋል ከረጢቱ።

ሣቅ ሣቅም ይለኛል፤ ስቆ ላይስቅ ጥርሴ፣

ስቃ እያለቀሰች መከረኛ ነብሴ::”

(በዓሉ ግርማ)

  1. የህወሃት የሽፍታ መንግስት እ.አ.አ ሚያዝያ 27/1993 ኤርትራ ከኢትዮጲያ ተገንጥላ እራሷን የቻለች ሃገር እንድትሆን ለተባበሩት መንግስታት ደብዳቤ በመላክ ሉዓላዊ ሃገር እንድትሆን አድርጓል::
  2. ህወሃት የጎንደርን መሬት ለሱዳን ሸጧል:: የወሎን መሬት ነጥቋል:: ሰሜናዊ አፋርን አመቻችቷል:: የግዛቱን አካል እስከ ጋምቤላ እንደሚሆን ካርታ ሠርቶ አሳይቷል::
  3. ህወሃት ባድመንም ኤርትሪያ እንድትወስድ አልጄርስ ላይ እ.አአ በዴሴምበር 12/2000 ተስማምቷል:: አሁን የሆነው ተግባራዊነቱ ብቻ ነው::

እናስተውል እንጂ!

እኔን የሚያሳስበኝ ትግራይ አካሏ የሆነው የባድመ መሬት ወደ ኤርትርያ የመካተት ጉዳይ አይደለም:: ይልቁንም ከባድመ የተሻለ ለሱዳን የሸጠችውና በሃይል ነጥቃ የያዘችው የጎላን ከፍታ መሣዩ የወልቃይት፣ የጠገዴ፣ አላማጣ፣ ራያና ቆቦ ጠፍ መሬት በግዛት ተስፋፊነት ልትደምረው ያሰበችው የአፋርና የጋንቤላ መሬት ጭምር ነው::

ለኤርትራም መገንጠል ይሁን የባድመንም ለኤርትራ መሰጠት የፈረመው ህወሃቱ መለስ ዜናዊ ነው::

ህወሃትና ትግራይ ኢትዮጵያዊ ሆነው የሚቆዩት ህወሃት ስልጣን ላይ እስካለ ነው:: የህወሃት ቆይታ ከተመቸውና ኢትዮጵያን መግዛት እስከቻለ፤ ይህን ካልቻለ የትግራይ ሪፑብሊክ እንደሚመሰርት ለዚህም አንቀፅ 39 በማያሻማ መልኩ አስቀምጧል:: ደብረፅዮን በቅርቡ “ወደአልፈለግነው መንገድ እየገፉን ነው (እንድንገነጠል)” ብሎናል:: ታዲያ አሁን የማየው ጫጫታ ህወሃት የባድመ አካሏን ቆርጣ ለኤርትራ መሰጠት ጉዳይ ይሆን? ይህ የህወሃትና የትግራይ ህዝብ ጉዳይ ነው:: እኔንም ሆነ እናንተን ሊያሳስብ የሚገባን ፈቅዶ የሚሰጠው በህወሃት ስልጣን ስር ያለው የህወሃት ግዛት ሣይሆን ህወሃት ከኛ ነጥቆ የሚሄደው ከላይ የተጠቀሱና በመስፋፋት የተያዙት ጠፍ መሬቶች ጉዳይ ብቻ ነው:: ህወሃት ለኤርትሪያ የሰጠው የተራቆተ የባድመ ድንጋይ መሬት ሲሆን ዘርፎ የወሰደው ኢትዮጵያዊ ለም መሬት ነው:: የትኛው ያማል?

በእርግጥ ባድመ ላይ እብሪተኞች በቀሰቀሱት ጦርነት የኢትዮጵያውያን ህይወት ተገብሯል:: ማስተዋል ያለብን ህወሃት ትርፍ እስካገኘ እንኳን ባድመን የትግራይን ህዝብም ይሸጣል:: ከባድመ በላይ ደምና አጥንት የተገበረለትን ኢትዮጵያዊ ነፃነትና ክብር ሸጧል:: ዳር ድንበሯን ደፍሯል:: አስደፍሯል። ኢትዮጵያ እራሷን ለራሱ ሸጧል:: ገዝቷል::

ከዚህ ህወሃታዊ ውሣኔ ጀርባ ምዕራባውያን እንዳሉበት፣ ከውሣኔው ጀርባ ህወሃት ማካካሻ ከኢትዮጵያውያን የነጠቀውን መሬትን መያዙ፣ ከዚህ ውሣኔ ጀርባ በኤርትራ በኩል መቀመጫው ላይ የተሰካውን ፖለቲካዊ እሾክ በመንቀልና ተቃዋሚዎቹን የኤርትሪያ ድጋፍ በማሳጣት ረገድ ህወሃት አትራፊ መሆኑን ነው የምረዳው:: ይህን ለመገንዘብም የሮኬት ሣይንቲስትን መሆን አይጠይቅም።

ጩኸት የሚያምረው የሚሰማ ጆሮና የሚያስጮህ ምክንያት ሲኖር ነው:: ከእኛ ይልቅ የባድመ ጉዳይ ሊያስጮሃቸው የሚገባው የትግራይ ህዝብን ነው:: እነርሱ ከጮሁ ጩኸታቸውን እናደምቃለን:: አለበለዚያ እኛ ለነርሱ ባልወሠድነው ወይም እነርሱ ባልሰጡን ውክልና ስለነሱ ብንጮህ ይገርመኛል:: ያሾፉብናልም። እንድእኔ ህወሃት ትላንት፣ ዛሬና ነገ በጉልበቱ ነጥቆ ህዝብን አባሮ ለያዛቸው መሬቶች ሃዘኔ በርትቶ ቱቢት (ጥቁር ልብስ የሃዘን) ለብሻለሁ:: ህወሃት-ወያኔ ከ25 ዓመት እንድትገነጠል ላመቻቸላት ኤርትሪያም ሆነ ከ20 ዓመት በፊት በጥቁር ገበያ ለሸጣት ባድመ ግን እዬዬ ሲደላ ነውና ደረቴን አልመታም:: ከ25 ዓመታት በፊት አልቅሼ ወጥቶልኛልና አሁን እምባም የለኝም። የሠው ልጅ የሚሠናበተውና ሲለየው የሚያነባው እንዲለየው ያልፈለገውን ነገር ግን መመለስም ለማይችለው ነው።

‘ተረኛ ነኝና እንዳትሸበሪ፣

ስለይሽ አዝናለሁ ባድመ ደህና እደሪ።’

‘መሸጥ የለመደ እናቱን ያስማማል!’

ሞት ለወያኔ!