ኢት-ኢኮኖሚ           /ET- ECONOMY

 “It doesn’t matter if a cat is black or white, so long as it catches mice.”Deng Xiaoping Quotes

የኢትዬጵያ የውጪ ብድር ክምችት፣ ከብሄራዊ አማካይ ጠቅላላ አመታዊ ምርት ድርሻ በ2011 እኤአ 19.9 በመቶ የነበረ ሲሆን በ2014 እኤአ 27 በመቶ ነበር፡፡ የመንግሥታዊ ልማት ዘርፎች ብድር  ከብሄራዊ አማካይ ጠቅላላ አመታዊ ምርት ድርሻ በ2011እኤአ 20.9 በመቶ የነበረ ሲሆን በ2014 እኤአ 42.0 በመቶ ሆኖል፡፡ በ2016/17 እኤአ የህወሓት መንግስትና ብሄራዊ ባንክ ባለሞሎች የሃገሪቱን ልትወጣ በማትችለው የውጪ ብድር ክምችት ከተው ኢኮኖሚውን አዘቅት እንደሚከቱት አጥኝዎች ተንብየዋል፡፡ ለዚህም ግልፅ ማሽረጃ የ2009 ዓ/ም ዓመት እቅድና አፈጻጸም፣ በተለይ የውጪ ንግድ ገቢ ማሽቆልቆል፣ የውጪ ብድር መክፈል አቅም መሽመመድና የውጪ ምንዛሪ እጥረት በቀጣይነት ተከስቶል፡፡ በ2008ዓ/ም የውጭ ዕዳ ክፍያ  አንድ ቢሊዩን ዶላር ለመክፈል ተገዶል፡፡ የወለድ ክፍያው በዓመት ከ350 ሚሊዩን ዶላር ከፍ ብሎል፡፡ በ2009ዓ/ም የውጭ ዕዳና የወለድ ክፍያ 1.5 ቢሊዩን ዶላር ለመክፈል ተገዶል፡፡ የኢትዬጵያ የውጭ ብድር 40 እስከ 50 ቢሊዩን ዩኤስ ዶለር ሲገመት ይህውም ከአመታዊ አጠቃላይ የአገር ውስጥ ምርት($69) ቢሊዬን ዩኤስ ዶለር (GDP) 58% እጅ ይይዛል፡፡ ወያኔ ሃገሪቱን  በእዳ ወጥመድ ውስጥ ከቶ ገንዘቡን ዘርፎል፣ አሽሽቶል፡፡

‹‹የኢትዮጵያ የዕዳ መጠን እየጨመረ ነው›› ግንቦት 2 ቀን 2010ዓ/ም (ቢቢሲ አማርኛ ዜና ሜይ 10 ቀን 2018ዕኤአ)

አለም አቀፍ የገንዘብ ተቆም አይ ኤም ኤፍ ባወጣው የአፍሪካ ሃገራት  ምጣኔ ሀብታዊ ዘገባ፤ የኢትጵያ የእዳ ጫና መጠን ከአጠቃላይ የሃገር ውስጥ ምርት 56.2 በመቶ ድርሻ እንደሚይዝ ገለፀ፡፡  ባሳለፍንው አመት የ10.9 በመቶ እድገት ያስመዘገበችው ሃገር ይህን ያክል ዕዳ መሸከሞ አስጊ የሚባል ደረጃ ላይ እንደሆነች ያሳያል ብሎል መግለጫው፡፡ ከሳህራ በታች የሚገኙ የአፍሪካ ሃገራት በፍጥነት በማደግ ላይ የሚገኘውን ምጣኔ ሃብታቸውን ለማሥቀጠል ሲሉ ከፍተኛ የሆነ ዕዳ ውስጥ እየገቡ እንደሆነ በየዓመቱ የሚወጣው ዘገባ ያትታል፡፡ 40 በመቶ የሚሆኑት ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የአፍሪካ ሃገራት ከፍተኛ የሚባል የዕዳ መጠን አስመዝግበዋል፤ ወይም ወደዚያ እየተጠጉ ነው የሚለው ዘገባው እነዚህ ሃገራት በቅርብ ጊዜ ውስጥ የማይወጡት ችግር ይገጥማቸዋል ሲል ይተነብያል፡፡ ኢትዮጵያ እና ዛምቢያ ከአጠቃላይ ሃገራዊ ምርታቸው ጋር ያተመጣጠነ ዕዳ እያስመዘገቡ መሆኑን የዓለም አቀፍ ተቆም ጥናት ያሳያል፡፡ በ2016 የኢትዮጵያ ዕዳ መጠን ከሃገራዊ አጠቃላይ ምርቶ 55 በመቶ የነበረ ሲሆን በ2017 ደግሞ ቀላል የማይባል ለውጥ በማሳየት ወደ 56 በመቶ አድጎል፡፡ ኢትዮጵያን ጨምሮ አብዛኛዎቹ የአፍሪካ ሃገራት አሁንም የመሠረተ ልማት ሥራዎቻቸውን ለማስቀጠልና ማህበራዊ ዋስትናን ለማረጋገጥ ወደ ብድር መግባታቸው አይቀርም የሚለው ዘገባው ቀጣይነት ያለው እድገት ማስመዝገብ ካለባቸው ግን የብድር መጠናቸውን መቀነስ ግድ ይላል፡፡ የዓለም ባንክ ኢትዮጵያ መንግሥት None concessional loan ብቻ እስከ 400 ሚሊዮን ዶላር በታች እንዲበደሩ ማስጠንቀቂያ ሠጥተዋል፡፡ ሃገሪቱ ባለባት ብድርና የእዳ ጫና ምክንያት  የኢትዮ ቴሌኮም፣የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ የኤሌትሪክ ኃይል ማመንጫዎ እና የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክድርጅት፣ የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ፣ የኢትዮጵያ ስኮር ኮርፖሬሽን፣የኢንዱስትሪ ፓርኮች፣ የሆቴል ለቻይና መንግሥትና የወያኔ ኢፈርትና ሌሎች አበዳሪ ድርጅቶች በፕራይቬታይዤሽን ተሸተው እዳችንን እንድንከፍል መንግሥት ተስማምቶል፡፡ የግሪክ መንግስት በብድር ጫና ምክንያት የባህር ወደቦቹን ለቻይና፣ ኤፖርቶቹን ለጀርመን፣ ባቡሩን ለጣሊያን መንግሥት ሸጦል፡፡

የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ፣ እልም አለ ባቡሩ፣ ቻይና ይዞት በሙሉ!  ጭንቅላቱን መሸከም የማይችል ፖለቲከኛ፣  በእናንተ ጭንቅላት የተመራ አገር! መንግሥት የአንበሳውን ድርሻ ሌላውን በአክሲዮን ወደ ግል ዘርፍ ይዛወራል ይሉናል፡፡ ሃቁ ግን በብድርና በእዳ ጫና ወለድ መክፈል ባለመቻል ተሸጦል፡ የዓለም ባንክ ኢትዮጵያ ከ400 ሚሊዮን ዶላር በታች ነን ኮንሽናል ሎን ብቻ እንድትበደር ቅጭን ትእዛዝ ሰጥቶል፡፡ 

‹‹የኢትዮ ቴሌኮም፣የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ የኤሌትሪክ ኃይል ማመንጫዎ እና የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክድርጅት፣ የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ፣ የኢትዮጵያ ስኮር ኮርፖሬሽን፣የኢንዱስትሪ ፓርኮች፣ የሆቴልና የተለያዮ የማኑፋክቸሪንግ ድርጅቶች ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ትልቁን የአክሲዮን ድርሻ መንግስት ይዞ ቀሪው በአክሲዮን ሽያጭ ወደ ግል ዘርፍ ለሃገር ውስጥ እና ለውጭ ባለሃብቶች እንዲተላለፍ ተወሰነ፡፡››  23 ግንቦት 2010ዓ/ም የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ፡፡ ኃብቱ የጥቁር(የኢትዮጵያ ) ሆነ የቢጫ (የቻይና )ግድ የለም፣ እስከተጠቀምኩበት ድረስ!!! 

{1} አየር መንገድ፣ (5.6 ቢሊዮን ዶላር) ለቻይና የወያኔ ኢፈርት/ጎሽ ድርጅቶች ይሸጣል፣

2} ኢትዮጵያ ቴሌኮምኒኬሽን፣ (4.8 ቢሊዮን ዶላር) ለቻይና የወያኔ ኢፈርት ድርጅቶች ይሸጣል፣

{3} የኢትዮጵያ መብራት ኃይል፣(5.4 ቢሊዮን ዶላር) ለቻይና ለ50 አመት ይሸጣል፣

{4} ኢንዱስትሪያል ፓርኮ (10 ቢሊዮን ዶላር) ለቻይና የወያኔ ኢፈርት ድርጅቶች ይሸጣል፣

{5} የኢትዮጵያ ስኮር ኮርፖሬሽን (5.5 ቢሊዮን ዶላር) የወያኔ ኢፈርት ድርጅቶች ይሸጣል፣

{6} የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን (5.9 ቢሊዮን ዶላር) ለቻይና ለ50 አመት ይሸጣል፣

{7} የኢትዩጵያ ንግድ መርከብ ድርጅት (301.5 ሚሊዩን ዶላር) ለቻይና፣ የወያኔ ኢፈርት/ኤክስፕሬስ ትራንዚት ሰርቪስ ካንፓኒ ይሸጣል፣

{8} የኢትዩጵያ ንግድ ባንክ (300 ሚሊዩን ዶለር) ተበድረዋል፡፡ የወያኔ ኢፈርት/ወጋገን ባንክ ይሸጣል፣

የህወሓት የጦር አበጋዞች መንግሥት በሃያ ሰባት ዓመታት ውስጥ ሃገሪቱን በብድርና በእዳ ጫና ከተው ኃብቱን ዘርፈውና አሽሽተው በኢኮኖሚ በሁለት አሃዝ አድገናል ተመንድገናል ይሉናል፡፡ ዘራፊዎቹ የወያኔ ኢፈርትና ሜቴክ ድርጅቶች ንብረቶች መጀመሪያ በአክሲዮን ለህዝብ ይሸጡ!!! ኢፈርት 57 ቢሊዮን ብር ያለው ድርጅት እንደሆነ አስታውቆል ድርጅቶቹን ይገዛል፡፡ ወያኔ በብድርና የእዳ ጫና ምክንያት ፕራይቬታይዝ አደረግሁ አለ እንጂ የተበደረውን የብድር ወለድ እንኮ መክፈል ስለተሳነው ድርጅቶቹን ለአበዳሪዎቹ እንዲሸጥ የተደረገው ሃቁ እንደ ውስጥ አዋቂዎቹ ይሄ ነው፡፡  የዓለም ባንክ ኢትዮጵያ መንግሥት None concessional loan ብቻ እስከ 400 ሚሊዮን ዶላር በታች እንዲበደሩ ማስጠንቀቂያ ሠጥተዋል፡፡

የቻይና መንግስት ለኢትዬጵያ 11.4 ቢሊዬን ዩኤስ ዶለር አበድሮል የዛሬ ስምንት ካዛ በሆላ ወያኔ የተበደረው የትየለሌ ነው፣ የተዘረፈው እኮ የብድር ገንዘብ ነው፡፡ በአዲስ አበባና ክልል ከተሞች የሚገነቡት ፎቆች ከህዝብ በተዘረፉ ፕሮጀክቶች ኃብት ነው፡፡ የወያኔ መንግሥት ሙሰኛችንና ሌቦችን ኃብትና ንብረት ወርሶ ሲያስከፍል አይታይም፡፡ የሙስና ቀይ መብራት ተጥሶ ሌቦቹ ተለቀዋል፡፡ ከሳውዲ አረቢያ ንጉስ ከ100 ቢሊዮን ዶላር በላይ ከሙሰኞች አስመልሶል፣ አላሙዲን በሳውዲ ስታር የ4 ቢሊዮን ዶላር ሌብነት ዘብጥያ ወርደዋል፡፡ የህዝብ ሃብት ከሆኑ በብድር ከሚሠሩ ፕሮጀክቶች የተዘረፈ ሃብትና ንብረት ሳይመለስ በሃገሪቱ ፍትህ አይሰፍንም፡፡ ወያኔ የሙስናና ሌብነት ሮል ሞዴል በመሆን በትውልድ ይታወቃል፤ ዓየር መንገዳችንን፣ቴሌን፣ ባቡሩን ወዘተ የሃገሪቱ መታወቂያችንን አሳጣን፡፡ የሃገረ ግሪክ ወደቦን ቻይና ገዝቶታል፡፡ በዲሴንበር 6/2011እኤአ  ከጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ዘመነ መንግስት የቻይና አስመጭና ላኪ ባንክ (Chinese Export and Import Bank) በኩል የቻይና መንግስት ለኢትዬጵያ መንግስት 11.4 ቢሊዬን ዩኤስ ዶለር(272.2 ቢሊዩን ብር) እንዳበደሩ  በግዜው ገልጸዋል፡፡ ብድሩ ለናሙና ያህል ለመግለፅ፡-የኢትዬጵያ ስካóY ኮርፖሬሽን 500 ሚሊዩን ዩኤስ ዶለር ብድር ከቻይና ልማታ ባንክ (China Development Bank Corp.)  ጋር ተፈራረመ፡፡ ባንኩ የቻይና ኮምኒስት ፓርቲ መንግስታዊ ንብረት እንደሆነ ይታወቃል፡፡ የኢትዬጵያ ስካóY ኮርፖሬሽን በብድሩ ሁለት ትልልቅ የስካóY ድፍድፍ ማጣሪያዎች ፋብሪካዎች ይገነባል፡፡  አንዱ ፋብሪካ በደቡብ ኢትዬጵያ ኦሞ ዞን ውስጥ የሚገነባ ሲሆን ሁለተኛው ፋብሪካ በሰሜን ምዕራብ አፋር ክልል ውስጥ በሜታል ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ኢትዬጵያዊ መንግስታዊ ድርጁትና በቻይና ኮምፕላንት ግሩፖ ኢንክ (China Complant Group Inc) የሚገነባ ሲሆን ምርቱን በ2025 እኤአ አስር እጥፍ ለማድረግ ታቅዶል ነበር፡፡የኢትዬጵያ ስኮር ኮርፖሬሽን የወንጂ ሸዋ ፣የመተሃና የፊንጫ ስኮር ፋብሪካዎችን ጠቅልሎ በመያዝ በበላይነት እያስተዳደረ ይገኛል፡፡ኮርፖሬሽኩ በደቡብ ክልል ሰባት፣ በአማራ ክልል ሦስት፣ እንዲሁም በትግራይ ክልል አንድ (የአፋር ክልልን መሬት ወደ ትግራይ ክልል በመከለል የተወሰደ መሆኑን ልብ ይሎል)  ፋብሪካን ጨምሮ በድምሩ 12 አዳዲስ ስኮር ፋብሪካዎችን የክልሎችን መሬት በፌዴራል መንግስት ስም በመንጠቅ በመገንባት ላይ ይገኛል፡፡አስራ ሁለት  የሸንካራ አገዳ እርሻና ፋብሪካዎች በመገንባት የስኮር ምርትን አሁን ካለው ምርት 265000 ሽህ ሜትሪክ ቶን ወደ 2.3 ሚሊዩን ሜትሪክ ቶን ከፍ በማድረግ ወደ ውጭ ሃገራት በተለይ ለአፍሪካ ቀንድ አገራት ለመላክ ሲሆን አገሪቶን በ2025 በዓለም ካሉት አስር የስኮር ላኪ አገሮች ጎራ ለማስገባት በሚል የፕሮፖጋንዳ ፍጆታ ተወጥኖል፡፡ የኢትዬጵያ ስኮር ኮርፖሬሽን አጠቃላይ የግንባታ ስራ ወጭ 100 ቢሊዩን ብር (5.5 ቢሊዩን ዩኤስ ዶለር) እንደሚሆን ሲገመት ማሽነሪዎች ለመግዛት ግማሹ በውጭ ምንዛሪ ገንዘብ ይሻል፡፡ የኢትዬጵያ ስኮር ኮርፖሬሽን በአፋር ክልል ትንዳሆ 30 በመቶ ምርት በማምረት ላይ ሲገኝ በአሁኑ ግዜ በ394 ሚሊዩን ዩኤስ ዶለር ብድር ከህንድ አስመጭና ላኪ ባንክ(Export-Import Bank of India) በተገኘ ብድር የፋብሪካው ግንባታ ሥራ በህንድ (India’s Overseas Infrastructure Alliance) በመከናወን ላይ ይገኛል፡፡የኢትዬጵያ ስኮር ኮርፖሬሽን በጥናት ላይ የተመሰረተ ሥራ እንደማይሰራ በምሁራኖች ዘንድ ይታወቃል፡፡ የምስራቅና ምዕራብ አፍሪካ የንግድና ልማት ባንክ (ፒቲኤ ባንክ) ለኢትዬጵያ ስኮር ኮርፖሬሽን 25 ሚሊን ዩኤስ ዶለር ብድር ለመስጠት ስምምነታ ላይ ተደርሶል፡፡ዲሴንበር 6/2011እኤአ  የቻይና አስመጭና ላኪ ባንክ( Chinese Export and Import Bank)ለኢትዬጵያ ዩኤስ 400 ሚሊዩን ዶለር (6.9 ቢሊዬን ብር) ሁለት  የብድር ስምምነቶች አድርገዋል፡፡ከጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ጋር የባንኩ ምክትል ፕሬዜዳንት ዘሁ ሆንጃይ( Zhu Hongjie) እንደገለጹት ባንኩ 1.81ቢሊዬን ዩኤስ ዶለር(31ቢሊዩን ብር) እንዳበደሩ ገልጸዋል፡፡አንዱ ስምምነት ባንኩ 100 ሚሊዩን ዶለር ለአዲስ አበባ የውሃ ሥራዎች አቅርቦት ፕሮጀክቶች ግንባታ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ከኢትዬጵያ ንግድ ባንክ ጋር 300 ሚሊዩን ዶለር የባንኩን የብድር አቅርቦት ከፍ ለማድረግ እንደሆነ ተዘግቦል፡፡ ዘሁ ሆንጃይ እንደገለፁት ከሆነ ባንኩ እስካሁን 11.4 ቢሊዬን ዩኤስ ዶለር(272.2 ቢሊዩን ብር) እንዳበደሩ ገልጸዋል፡፡

Meles on the occasion lauded the Chinese government and the banks for their contribution towards success of Ethiopia’s development endeavours. The Premier also said the relation between the two countries is laid on firm foundation and expressed Ethiopian government’s commitment to further work in collaboration with China.

Zhu Hongjie on his part said the bank will further strengthen existing relation with Ethiopia as the country has registered sustainable growth during the last eight years. The bank has provided 11.4 billion USD loan for implementation of various development projects in Ethiopia, he said.

የኢትዬጵያ የስሊጥ ምርት  ኢትዬጵያ ቻይና የሠራችላትን የመሠረተ ልማት ዕዳ ለመክፈል አጠቃላይ የስሊጥ ምርቷን ወደ ቻይና ተጭኖ እንደሚላክ  ታወቀ፡፡ በ2002 እኤአ ኢትዬጵያ 38000 ሜትሪክ ቶን ሰሊጥ በማምረት ትታወቅ ነበር፡፡ በተባበሩት መንግስተሰት የምግብና የእርሻ ድርጅት ጥናት መሰረት በ2011 እኤአ 320000  ሜትሪክ ቶን ሰሊጥ በማምረት ከአፍሪካ በምርት ትልቁን ድርሻ ስትይዝ ከዓለም ደግሞ አራተኛ ሰሊጥ አምራች አገር ለመሆን በቅታለች፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ቻይና ደግሞ ከሰሊጥ ላኪ አገርነት  ኢትዬጵያ ሰሊጥ ወደ ቻይና በማስገባት ትታወቅ ጀመር፡፡ የሰሊጥ ምርት ለዳቦ፣ ለቅመማ ቅመም ማጣፈጫነት፣  ተጨምቆ ወደ ዘይት ምርትነት እንዲሁም ለዶሮ እርባታ ከፍተኛ የፕሮቲን ገንቢ ግብአትነት በማገልገል ይታወቃል፡፡ ለኢትዬጵያ ቻይና የፍብሪካዎች ምርቶች ወደ ሃገር ውስጥ መግባት፣የብድር አገልግሎት መመቻቸትና አዳዲስ የመሠረተ ልማት ግንባታ ስራ አወዳጅቷቸዋል፡፡ የቻይና ልማት ባንክ 25 ሚሊዩን ዶለር ብድር ለእርሻው ዘርፍ ኢንተርፕራይዝ ሰጥተዋል፡፡እንዲሁም የቻይና አስመጭና ላኪ ባንክ 3.3 ቢሊዩን ዶለር ብድር ከኢትዬጵያ ወደ ጅቡቲ ነጋድ ወደብ ለሚዘረጋ የባቡር ሐዲድ መስመር ዝርጋታ ሰጥታለች፡፡ በ2011 እኤአ ኦክስፋም ጥናት መሠረት ከሆነ በኢትዬጵያ 600 000 አነስተኛ መሬት ያላቸው ገበሬዎች ሰሊጥ በማምረት ይተዳደራሉ፣ትንሽ መሬት፣የዘር ችግር፣ጥራት አልባ ምርትና በብድር አቅርቦት  እጦት እንደሚቸገሩ ይታወቃል፡፡ ታዲያ በኢትዬጵያ ንግድ ባንክ የሰሊጥ ምርት ተሰብስቦ ወደ ቻይና መላክ የአነስተኛ ገበሬዎችን የገቢ ምንጭ በመቀነስና ገበሬዎች ለማምረት ይበረታታሉ ለማለት አያስደፍርም፡፡ እንደ ደርግ ወታደራዊ አገዛዝ ዘመን  ገበሬዎች ለእርሻ ሰብል ገበያ ድርጅት (እሰገድ) ምርታቸውን ማስረከብ ይጠበቅባቸው ነበር፡፡ ድመቲቱ ጥቁር ትሁን ነጭ ግድ የለም፣ ዓይጥ እስከያዘች ድረስ! In return, Ethiopia has effectively been using sesame seeds to repay Chinese loans. Foreign currency earned by selling sesame is passed over to the state-owned Commercial Bank of Ethiopia and used to secure and repay loans provided by China, according to Deborah Bräutigam, senior research fellow at the International Food Policy Research Institute. The relationship is likely to have started in 2005-06 as a shortage of sesame seeds in China and a favourable tariff policy (set by China) kickstarted the rise in Ethiopian exports, which are regulated largely by the state-owned Ethiopian commodities exchange. Bräutigam says China is unlikely to have stipulated that Ethiopia export its sesame, which is now its second most valuable export after coffee. “The ‘guaranteed supply’ of whatever export is already going to China is simply the mechanism for ensuring repayment of the loan,” she says. The Government of Ethiopia is planning Potashe mining as acollatoral for  repayment of the  Chinese loans.

ኢህአዲግ መንግስት ከ2005 እኤአ ጀምሮ የሰሊጥ ምርት ወደ ቻይና በመላክ ኢትዬጵያ የተበደረችውን ዕዳ በመክፈል ላይ ትገኛለች፡፡ በ2006 እኤአ የቻይና ዜድቲኢ(ZTE) ካንፓኒና የኢትዬጵያ ቴሌኮምኒኬሽን ኮርፖሬሽን (አሁን ኢትዬቴሌኮም) የ1.5 ቢሊዬን ዩኤስ ዶለር ብድር በመፈራረም የእዳው ክፍያም የሠሊጥ ምርት ወደ ቻይና በመላክ የንግዱ ስምምነት በኢትዬጵያ ኮሞዲቲ ኤክስቼንግ ተከናውኖል፡፡ ከሠሊጥ ምርት ሺያጭ የተገኘውን የውጭ ምንዛሪ ገቢ በኢትዬጵያ ንግድ ባንክ በኩል  ተሰባስቦ የቻይና መንግስት ዕዳን ለመክፈል ይውላል፡፡ ቻይና የኢትዬጵያን ሠሊጥ ወደ ሃገሮ በማስገባት ከዓለም ትልቆ ሃገር ለመሆን ችላለች፡፡ Ethiopia’s ruling People’s Revolutionary Democratic Front (EPRDF) similarly exploits Chinese demand for biofuels to boost exports and buttress its statist agenda. Since 2005, the regime has relied on sesame exports to repay Chinese loans. A portion of the 2006 $1.5 billion credit signed between China’s ZTE and Ethiopia’s Telecommunications Corporation (now Ethio Telecom) provided for repayment in sesame seeds, with the terms of trade set by the Ethiopian Commodity Exchange. Foreign currency earned through the sales is appropriated by Ethiopia’s state-owned Commercial Bank and used to fund Chinese projects in what effectively amounts to a revolving credit facility. China today is the world’s largest net importer of Ethiopian sesame.

ለማጠቃለል የኢትዬጵያ አጠቃላይ የአገር ውስጥ ምርት (GDP) አነስተኛ መሆን ምክንያት የሃገሪቱ የኢኮኖሚ እድገት፣ በተቆለለ የውጭ ብድር ክምችትና የእዳ ክፍያ ምክንያት በረጅም ግዜያት ውስጥ እንደሚናጋ ይጠበቃል፡፡ የኢትዬጵያ የውጭ ብድር በ1975 እኤአ የኢትዬጵያ የውጭ ብድር 343.7 ሚሊዩን ዩኤስ ዶለር የነበረ ሲሆን ይህውም አመታዊ አጠቃላይ የአገር ውስጥ ምርት (GDP) 14% እጅ ይይዝ ነበር፡፡ በ1991 እኤአ የኢትዬጵያ የውጭ ብድር 9.1 ቢሊዬን ዩኤስ ዶለር የነበረ ሲሆን ይህውም አመታዊ አጠቃላይ የአገር ውስጥ ምርት (GDP) 214% እጅ ይይዝ ነበር፡፡ በጁን 30 1999 ይሄ አሃዝ 10.2 ቢሊዬን ዩኤስ ዶለር ከፍ ብሎል፡፡በ2011እኤአ የኢትዬጵያ የውጭ ብድር 7.102 ቢሊዩን ዩኤስ ዶለር የነበረ ሲሆን ይህውም አመታዊ አጠቃላይ የአገር ውስጥ ምርት (GDP) 23.5% እጅ ይይዝ ነበር፡፡ 2012እኤአ የኢትዬጵያ የውጭ ብድር 12 ቢሊዩን ዩኤስ ዶለር የነበረ ሲሆን ይህውም አመታዊ አጠቃላይ የአገር ውስጥ ምርት (GDP) –% እጅ ይይዝ ነበር፡፡ 2013እኤአ የኢትዬጵያ የውጭ ብድር 16.11 ቢሊዩን ዩኤስ ዶለር የነበረ ሲሆን ይህውም አመታዊ አጠቃላይ የአገር ውስጥ ምርት($46) ቢሊዬን ዩኤስ ዶለር (GDP) 35% እጅ ይይዝ ነበር፡፡ 2016/17እኤአ የኢትዬጵያ የውጭ ብድር 40 ቢሊዩን ዩኤስ ዶለር ሲገመት ይህውም ከአመታዊ አጠቃላይ የአገር ውስጥ ምርት($69) ቢሊዬን ዩኤስ ዶለር (GDP) 58% እጅ ይይዛል፡፡ እንደ ዶክተር ሰዒድ ኑሩ ገለፃ ‹‹የውጭ ምንዛሪ የሚገኙባቸው የታወቁ ናቸው፡፡ የመጀመሪያው ከኤክስፖርት፣ከውጭ በዕርዳታና ለብድር፣ በውጭ የሚኖሩ ሰዎች የሚልኩት ነው፡፡ ከእነዚህ ውስጥ በእጃችን ላይ ያለው ኤክስፖርት ነው፡፡ ኤክስፖርት ደግሞ ያለው አፈጻጸም ደካማ ነው፡፡ የውጭ ዕርዳታ እየቀነሰ ነው፡፡ ለምግብ እርዳታ እንኮ እየቀነሰ ነው፡፡ ብድር አስቸጋሪ ነው፡፡ የውጭ ብድር የሚመሠረተው በኤክስፖርት አፈፃፀም ጥንካሬ ነው፡፡ የአበዳሪዎች ዋነኛው ጥያቄ መክፈል ይችላሉ ወይ ነው፡፡ እንዲህ ከሆነ የበጀት ጉድለት ባይኖር እንኮን በጀቱ በአገር ውስጥ ቢሸፈን እንኮ፣ ይሄን 320.8 ቢሊዩን ብር እዚሁ ብንሸፍን በብር አሁን ባለንበት ሁኔታ ትራንስፎርሜሽኑ ያቀደቸውን ከማሳካት አንፃር የውጭ ምንዛሪ የግድ ነው፡፡ ስለዚህ ትርጉም ባለውና ከአጠቃላይ በጀቱ ውስጥ ጎላ ባለ ደረጃ በውጭ ምንዛሪ መገኘት አለበት፡፡››ይላሉ፡፡ ለዚህ ነው ሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ሃገሪቱን በብድር መቀመቅ ውስጥ ከቶት ለሽያጭ ያበቃት፡፡

{1} የቻይና የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ቻይና በቀጥታ ኢንቨስትመንት በማድረግ ከ2012 እስከ 2013እኤአ በኢትዮጵያ ውስጥ 155 ፕሮጀክቶች የነበሩ ሲሆን ካፒታላውም 358,642,000 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር መሆኑን ጥናቱ ያረጋግጣል፡፡ በ2013 እኤአ፤በአፍሪካና በቻይና መካከል 210.2 ቢሊዩን ዶላር ዓመታዊ የንግድ ልውውጥ ተካሂዶል፡፡ከዚህ ውስጥ ቻይና ወደ አፍሪካ አገራት የምትልካቸው ሸቀጦች ዋጋ ከ117 ቢሊዩን ዶላር በላይ ናቸው፡፡ ኢትዩጵያ በአፍሪካ 21ኛዋ የቻይና የንግድ መዳረሻ ስትሆን በአሁኑ ወቅት ሁለቱ አገራት ዓመታዊ የንግድ ልውውጥ 2.2 ቢሊዩን ዶላር መድረሱ ታውቆል፡፡የባህር ማዶ፣ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት በኢትዬጵያ ከአፍሪካ አገራቶች ጋር ሲወዳደር በጣም አነስተኛ መሆኑን መሳተዋል ይቻላል፡፡‹‹የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት በኢትዩጵያና በአፍሪካ ኢኮኖሚ›› (Foreign Direct Investment (FDI) in the Ethiopian/African Economy) በሚል ርዕስ፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ ዲፓርትመንት መምህር ከአለማሁ ገዳ [email protected]: www.alemayehu.com, በማርች 25ቀን 2016 እኤአ፣በጊዬን ሆቴል ባቀረቡት ጥናታዊ ፁሁፍ መሠረት የቻይና ፋይናንሲንግ በኢትዩጵያ ከቀጥተኛ ኢንቨስትመንት በተጨማሪ በዋና ኢንቨስትመንት እንቅስቃሴዎች በመንገድ ሥራዎችና በባቡር ግንባታ ዝቅተኛ የጨረታ ዋጋ በማቅረብ 10 የቻይና ኩባንያዎች በበላይነት ይቆጣጠራሉ፡፡የኤሌትሪክ ኃይል ማመንጨት በፋይናንስ ማመቻቸትና በዝቅተኛ የጨረታ ዋጋ ያቀርባሉ፡፡ እንዲሁም በቴሌኮምኒኬሽን ፕሮጀክቶች  በፋይናንስ ማመቻቸት  በመሳሰሉት ፕሮጀክቶች የቻይና መንግስትና ኩባኝያዎች በስፋት ይሳተፋሉ፡፡  ሲጠቀሱ የኢትዩጵያ መንግስት ኢንቨስትመንት ወጪ እንጂ የቻይና ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት አይደለም፡፡

እንደ ቻይና ዓለም አቀፍ ኢንቨስትመንት ምንጭ  በ2016 እኤአ መሠረት፡- የቻይና ኢንቨስትመንትና የተለያዩ ፕሮጀክቶች ኮንትራት ውል በኢትዩጵያ ከ2005 እስከ 2016 እኤአ 17.6 ቢሊዩን ዶላር ይገመታል፡፡በ2013 እስከ 2015 እኤአ የቻይና ኢንቨስትመንትና የተለያዩ ፕሮጀክቶች ኮንትራት ውል በኢትዩጵያ 7.39 ቢሊዩን ዶላር ሲገመት በአንጻሩ የቻይና የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት በኢትዩጵያ 122 ሚሊዩን ዶላር በ2012 እኤአ እንደ ዓለም ባንክ መረጃ መሠረት፣ እናም 600 ሚሊዩን ዶላር ስቶክ በ2012 እኤአ፣ በግብርና ዘርፍ 650 ሚሊዩን ዶላር፣ በኢነርጅ 5.85 ቢሊዩን ዶላር ፣ በሪል እስቴት 1.63 ቢሊዩን ዶላር ፣በቴክኖሎጅ 3.2 ቢሊዩን ዶላር፣በትራንስፖርት ዘርፍ 6.29 ቢሊዩን ዶላር  ነበር፡፡

According to the China global investment tracer, (2016), Chinese investments and contracts in Ethiopia from 2005 to 2016 is about $17.62billion. The same source claim from 2013 to 2015, Chinese investments and contracts in Ethiopia to a level of $7.39billion./Compare this to FDI of 122mln in2012 (WB) and 600mln Stock here in 2012/ Agriculture: 650 million, Energy: $5.85billion Real Estate: $1.63billion, Technology $3.2billion, Transport $6.29billion. The official figures of FDI greatly understated the actual investment engagement of the Chinese in Ethiopia   as well as in other African countries

Chinese firms are thus dominating big projects in Telecommunication and Power Road and Rail Sector. Telecom and Power One of the biggest Chinese telecom company, ZTE, secured for Ethio telecom a credit (vendor financing) to the tune of 1.5 bln US$ secured from the Chinese Exim bank. This offer is conditional on ZTE doing the job without bidding. This credit is perhaps equivalent to the total current worth of the Ethiopian telecom.  This has increased to close $3bln (with addition of about 1.3blin) in the 2nd phase. Power transmission for GRD (=US$ 1 bln) Road and Rail Construction Chinese firms are also dominating both rural and urban road construction in Ethiopia. (over 60%  in 2010) This dominance is partly due to low bid prices and partly owing to the diplomatic and political ties the Chinese government made with the Ethiopian government.

Provision of financing by the Chinese government for its firms in Africa, is another reason for this success. The over 2000km national and about 36Km Addis Ababa railway construction is totally dominated by Chinese firms that brought with them financing. The railway deal with China is estimated at US$3 billion. (US$2.1 billion for national and about US$0.5 billion light city rails for Addis Ababa).

የቻይና ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት በኢትዮጵያ Foreign Direct Investment (FDI) በኢትዮጵያ በግብርና ዘርፍ 33 ፕሮጀክቶች4,015,596,000 ቢሊዮን ብር ፣በማዕድን  ዘርፍ 11 ፕሮጀክቶች 166,288,000,ሚሊዮን ብር ፣,በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ 532 ፕሮጀክቶች30,290,675,000 ቢሊዮን ብር ፣በትምህርት ዘርፍ 5 ፕሮጀክቶች 5,430,000 ሚሊዮን ብር ፣በጤና ዘርፍ 16 ፕሮጀክቶች 40465 ሚሊዮን ብር ፣በሆቴለተና ሞቴል  ዘርፍ 72 ፕሮጀክቶች 589745000 ሚሊዮን ብር ፣በትራንስፖርትና አስጎብኝ ዘርፍ 11 ፕሮጀክቶች 19,485,000 ሚሊዮን ብር ፣በሪልስቴት ግንባታ ዘርፍ 143 ፕሮጀክቶች 1,699,064,000 ቢሊዮን ብር ፣የጉድጎድ ውኃ ቁፋሮ ድርጅት 108 ፕሮጀክት 4,138,716,000 ቢሊዪን ብር ፣ ልዮ ልዮ 7 ፕሮጀክቶች 62,130,000 ሚሊዮን ብር ሲሆን በአጠቃላይ የቻይና ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት 938 ፕሮጀክቶ 41,027,594,000 ቢሊዮን ብር መሆኑ ታውቆል፡፡ የቻይና መንግሥት ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት በጣም ዝቅተኛ ሲሆን የቻይና መንግሥት ለኢትዮጵያ መንግሥት ብድር በማበደርና የፕሮጀክቶቹ ስራ ተቆራጭ በመሆን እስከ 17.6 ቢሊዮን ዶላር እንደሚደርስ በጥናት ተረጋግጦል፡፡

ዳግማዊ የመንግሥታዊ ዘርፍ፤ ነቀላና ተከላ!!! ‹‹የሀብት ዝውውርን በተመለከተ ለፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ የሚሆን ተሞክሮ ይገኛል፡፡ ፕራይቬታይዜሽን የሚለው ቃሉን ራሱን የፈጠሩት ማርጋሬት ታቸር መሆናቸው ይነገርላቸዋል፡፡ የእንግሊዞ ጠ/ሚ/ር ማርጋሬት ታቸር የሀገራቸውን ሃድሮ ፓወር ማመንጫ ጣቢያ ለአንድ ሚሊዮን ዜጎች ነበር በአክሲዮን የሸጡላቸው ይህንን ልምድ ኢትዮጵያ ውስጥ ላለው የፕራይቬታይዜሽን ትግበራ ለማዋል እንዴት አልተቻለም?፡፡››1  የህወኃት/ኢህአዴግ መንግሥታዊ የኢኮኖሚ ዘርፍ ወደ ግል ዘርፍ ኃብትና ንብረት የማዘዋወር፣ነቀላና ተከላ በኢትዮጵ ምድር አልሰመረም፡፡ በኢትዬጵያ የመንግስታዊ ሃብት ዘርፍ አፈጣጠር ታሪካዊ ሁኔታ ስንዳስስ (nationalized: state-owned/ publicly owned) በ1967 ዓም የኢትዬጵያ ወታደራዊ መንግስት፣ በሃገሪቱ ውስጥ የሚገኙ በግል ዘርፍ የሚንቀሳቀሱ፣ ባንኮችና ኢንሹራንሰ ኩባንያዋችን፣ ፋብሪካዎች፣ እርሻዎች፣ የገጠር መሬት፣ የከተማ ትርፍ ቤቶች፣ ወዘተ በአዋጅ ቁጥር 20/1974 ወደ መንግስት ሃብትነት አዘዋወረ:: በሶሻሊዝም  ርዕዬተ-ዓለም ፍልስፍና ሃገር ለማዝመን ተወጠነ፡፡ የሃገሪቱ የኢኮኖሚ የግብርና፣ የኢንዱስትሪና ስርቪስ ዘርፎች አንጡራ ኃብቶች በብሄራዊ ሃብትና እድገት ሚኒስትር (Ministry of National Resource Development) ስር የተወረሱትን ንብረቶች እንዲያስተዳድር ስልጣንና ሃላፊነት በአዋጅ ተሰጠው፡፡ የኢትዬጵያ ወታደራዊ መንግስት የፖለቲካና ኢኮኖሚ ፖሊሲዎች በሶሻሊስት የዕቅድ ኢኮኖሚ  በማስፋፋት በአንድ ማዕከላዊ ዕዝ የሚመራ መንግሥታዊ ዘርፍ በአገሪቱ ውስጥ ለ17 ዓመታት አስፈነ፡፡ የህወኃት/ኢህአዴግ የጦር አበጋዞች መንግሥትም፤ የደርግን መንግሥታዊ ካፒታሊዝምን ውርስ ማለትም  ፋብሪካዎች፣ ባንኮችና ኢንሹራንሰ፣ የከተማ ትርፍ ቤቶችን፣ የገጠር መሬትን፣ የመንግሥት እርሻዎችን ወደ ግል ዘርፍ በስመ ፕራይቬታይዜሽን፣ የወያኔ መንግሥት ወደ እራሱ የፖለቲካ ፓርቲዎቹ  ኃብትና ንብረትነት በማዘዋወር  ምጣኔ ኃብቱን ተቆጣጠረ፡፡ የህወኃት/ኢህአዴግ መንግሥት የመሬት ፖሊሲ ከደርግ የቀጠለ ሲሆን የደርግ መንግሥታዊ ዘርፍ ወደ ኢህአዴግ ፖለቲካ ፓርቲዎች፣ በህወኃት፣ ብአዴን፣ ኦህዴድ፣ ደህዴድ ኃብትና ንብረትነት ተዘዋወሩ፡፡  ባንኮችና ኢንሹራንሰ፣ የከተማ ትርፍ ቤቶችን፣ የገጠር መሬትን፣ፋብሪካዎች፣ የመንግሥት እርሻዎች በእነዚህ የፖለቲካ ፓርቲዎችና በቢዝነስ አጋሮች ኢፈርት፣ጥረት፣ዲንሾና ወንዶ እንዲሁም ጥቂት ባለኃብቶች ሚድሮክ ወዘተ በጋራ የህዝብ ኃብትና ንበረት ተቀራምተው የያዙበት አንባገነን ስርዓት መስረቱ፡፡ ከመንግሥታዊ ዘርፍ ወደ ግላዊ ዘርፍ የተደረገው የኢኮኖሚ ነቀላና ተከላ ያልተሳካው ለዚህ ነው፡፡  የደርግ መንግሥታዊ ዘርፍ ነቀላ በወያኔ መንግሥታዊ ዘርፍ ተከላ ተጠናቀቀ፡፡ የህወኃት/ኢህአዴግ የፖለቲካ ፓርቲዎች በ‹‹ልማታዊ መንግሥት›› ስም የኢትዮጵያን ህዝብ አርባና ሃምሳ ዓመታት ለመግዛት እንዲችሉ ኢኮኖሚውን በሙሉ ተቆጣጥረዋል፡፡  በኢትዮጵያ የመለስ ዜናዊ ውርስና ቅርስ የሆነው የሙስና ፋብሪካ ምርት አምራች የመንግስት ልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ ዴሬክተር ጀነራል አሰፋ አብርሃና  ዴሬክተር ጀነራል በየነ ገብረመስቀል  የደርግን መንግሥታዊ ዘርፍ ወደ ህወኃት/ኢህአዲግ የፓርቲዎች መንግስታዊ ዘርፍነት በማዘዋወር ‹‹በልማታዊ መንግሥት ስም›› ህዝብን ያጭበረበሩበት የወያኔ መንግሥታዊ ዘርፍ ነቀላና ተከላ ጥናታዊ ዘገባ ሚስጢር ‹‹አንድ ወናፍ፣ ሁለት አፍ፡፡››

የሙስናና የሌቦች ሃብትና ፎቆች ተወርሰው እዳችን ይከፈል፣ ከሳውዲ አረቢያ የሙስኛዎችን ኃብት ማምከን ተማሩ!!! 

ሙስናና ሌብነትን ለመዋጋት፣ የፕሬስ ነፃነት!!!

ዘራፊዎቹ የወያኔ ኢፈርትና ሜቴክ ድርጅቶች ንብረቶች መጀመሪያ በአክሲዮን ለህዝብ ይሸጡ!!!  

ይቀጥላል…