ሕወሀት የባድመን ጉዳይ አስመልክቶ በኢህአዴግ የተወሰነውን ውሳኔ ሙሉ በሙሉ እደግፋለሁ አለ

0

አባይ ሚዲያ
ሱራፌል አስራት

ባለፈው የባድመን ጉዳይና በኢትዮ ኤርትራ ያለውን ውዝግብ አስመልክቶ የኢህአዴግ ፅህፈት ቤት መግለጫ ማውጣቱ ይታወቃል። በድርጅቱም መግለጫ መሰረት የኢትዮጵያ መንግስት በአልጀርሱ ስምምነት መሰረት ለአመታት አወዛጋቢ ሆኖ የቆየውን የባድመን ግዛት ለኤርትራ እንደሚአስረክብና በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን እሰጣ ገባ በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ጥሪ ማስተላለፉ ይታወቃል።

ይሀንን ውሳኔ ተከትሎ አንዳንድ  ኢትዮጵያዊያኖች በተለይ ደግሞ የትግራይ ተወላጆች ቅሬታቸውን በማሰማት ላይ ይገኛሉ። የኢሀዴግን ውሳኔም በመቃወም ዛሬ በትግራይ ክልል በኢሮብ ከተማ በብዙ መቶወች የሚቆጠሩ የከተማው ነዋሪወች የተለያዩ መፈክሮችን በመያዝ የኢሀዴግን ውሳኔ ተቃውመዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ሕዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ሕወሀት) ዛሬ በፅህፈት ቤቱ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው  በኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ የተወሰነውን ውሳኔ ሙሉ በሙሉ አነደተቀበለውና ውሳኔውም እንዲፈፀም የበኩሉን ድርጅታዊ አስተዋፅዋ እንድሚአደርግ አስታውቋል።  ሕወሀት በመግለጫው እንዳሳወቀው ይህንን ጉዳይ ድርጅቱ ሀላፊነት በተሞላው መንገድ ሲሰራበት እነደቆየና ለዚህም ውሳኔ ቀዳማዊ ሚና እንደተጫወት በመግለጫው አትቷል።