ጋዜጣዊ መግለጫ (ከአንድ አማራ ንቅናቄ)

0

June 8, 2018

[email protected]    www.oneamhara.org

ግልጽ  ደብዳቤ  ለጠቅላይ ሚንስትር  ዶ/ር  አብይ አህመድ   ግልባጭ:-  ለአማራ  ህዝብና   የፖለቲካ እንዲሁ ሲቪክ  ተቋማት  ለብአዴን (እውነተኛ አማራ) ወጣትና  አመራር አባላት  ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ!

እንደሚታወቀው የጠቅላይ ሚንስትር  ዶ/ር አብይ  አህመድ አስተዳደር የሚመራዉ የወያኔ ኢህአዴግ መንግስት ከሰሞኑ መሰረታዊ የሆኑ ሃገራዊ ጉዳዮችን በተመለከት በቃላት ደረጃም ቢሆን መልካም ጅማርዎችን እያሳየን መሆኑ  ይታወቃል። ምንም  እንኳን የሃገራችን ችግር የዘር  የበላይነት፥ መሰረታዊ  የህግ እጦትና የሰው ልጆች  የዴሞክራሲ መጓደል ቢሆንም መሰል ተመሳሳይ የሆኑ ችግሮች  ላይ የሚደረገውን  የማሻሻልና የማረም  እርምጃ  በጎነው  ባዮች ነን።  የዶክተር አብይ አስተዳደር ካለፉት የጽንፈኛ  ዘረኛ የህወሃት አመራር  አካላት ጋር ሲነጻጸሩ መልካም የሆነ ጅማሮን  እያሳዩን መሆኑም እውን ነው። ያ ማለት ዓለም እንደሚያዉቀዉ ግን የመሪነት ቦታውን  ሁሉንኢትዮጵያዊ ባሳተፈ መልኩ በነጻና  ፍትሀዊ  ምርጫ ስላሊያዙት ሙሉ  ተቀባይነታችውን ጎደሎ ያደርገዋል።

ከሰሞኑ ባስተላለፉትም የባድመን ኣሳልፎ  የመስጠት ጉዳይ ምንም ህጉ ፍትሃዊ ባይሆንምና አልፎም ውሳኔው በሟቹ ጠቅላይ  ሚንስትር መለስ ዜናዊ እኩይ ተግባር ለሻቢያ መንግስት በዓለም  አቀፍ ፍርድ ቤት ተላልፎ  የተሰጠ ቢሆንም ደፍረው ውሳኔውን ተግባራዊ ማድረግ አለብን ማለትዎ ለለውጥና ለህግ የበላይነት ያሎትን   ቀናዒነት አስረጅ ነው። በመሆኑም ለህግ የበላይነት መከበር የተከተሉት አቅጣጫና ያሳዩት ፅኑ አመለካከት በመረዳት ከአንድ አማራ ንቅናቄ  የሚከተሉትን የፍትህ ጥያቄወች ለዶክተር አብይ አስተዳደርና፥ ለእውነተኛ አማራ የብአዴን አመራር አባላት ጥሪ ያቀርባል።

፩/  ከኦሮሚያና መሰል አጎራባች ክልሎች በግፍ ማንነታቸዉን መሰረት ባደረገ ጥላቻ ብቻ የሚፈናቀሉና በሃገራቸው ላይ ባይተዋር የሆኑ የአማራ ወገኖቻችን ላይ የሚደርሰው በደል በእርስዎ የስልጣን ዘመን እየከፋ በመምጣቱ አስተዳደርዎ ማፈናቀሉን ባስቸኳይ እንዲያቆም ብሎም የተፈናቀሉትን መልሶ በማቋቋም ከአስፈላጊው መሰረታዊ የህግ ከለላና ዋስትና ጋር ችግሩን እንዲፈታ አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጡ እናስገነዝባለ። አማራውን ነጥሎ የማጥቃቱ ኢፍትሃዊ እርምጃ አንድ ቦታ ላይ እልባት ካላገኘ ሃገሪቷ ልትወጣው ከማትችለው አደጋ ላይ እንዳይከታት እንሰጋለን::

፪/  በጽንፈኛው የትግራይ እብሪተኛ ቡድን  በግፍ ከአማራ ምድር ላይ የተወሰዱብንን መሬቶቻችንን ማለትም ፤ የወልቃይት  ጸገዴ፥ ኮረም፥  መሆኒ፥ራያ፥ አላማጣና ሌሎችም የአማራ መሬቶች አልፎም በግፍማንነታችውን ተገፈው አማራነታቸውን በጠመንጃ ሃይል በመጫን ትግሬ እንዲሆኑና ማንነታቸው እንዲጨፈለቅ የተፈረደባቸው  ወገኖቻንን ነጻ እንዲወጡና ሰላም እንዲፈጠር የዶ/ር አብይ አስተዳደር ውሳኔ እንዲያስተላልፍ አጥብቀን እናሳውቃለን። ይህ የማይሆን ከሆነ ግን ዶክተር አብይ በቃላት ደረጃ የተመኙትን ያህል ሰላም እንደማይመጣና    በመቶ ሺዎች ሳይሆን በሚሊዮኖች የሚያጫርስ የማንነት ተጋድሎ ጉዳይ መሆኑን እንዲያዉቁና ከህግ፥ከሞራልና ከታሪክ አንጻር አፋጣኝ  መልስ  ለጥያቄዎቻችን በሰላማዊ መንገድ የሚያልቅበትን ውሳኔ እንዲሰጡበት እናሳስባለን።

፫  /የነጻው የገበያ ስርዓት እውን ይሆን ዘንድ አስተዳደሮ፤ ህወሃት ለረጅም አመታት ሲቆጣጠረውና ሲዘርፋቸው የኖሩትን  የሃገራችንን ንብረቶች ለግል የንግዱ ማህበረሰብ የኢንቨስትመንት ተሳትፎ ዝግጁ መሆኑ በጎ ጅምር መሆኑ ሳለ ነገር ግን ከሃገርና  ከህዝባችን አልፎም  በማን አለብኝነት እብሪት ሃገርና መጭዉ ትዉልድን አሲይዘው ሲበደሩ የኖሩት የዘረፋ ተቋማት  ማለትም ኤፈርት፥ ጥረት፥ ወንዶና የመሳሰሉት ግዙፍ የዘረፋ ተቋማትና የፓርቲ ድርጅቶች በመንግስት ቁጥጥር ስር እንዲሆኑ አስፈላጊው አስተዳደራዊ እርምጃ እንዲወስዱ። ከዚሁ ጋር ከፍተኛው የባለቤትነት ድርሻ በኢትዮጵያ መንግስት ስር ሆኖ የኢትዮጵያ አየር መንገድና ቴሌኮሙኒኬሽን ለነጻውገበያ በቅድሚያ ለኢትዮጵያ ባለሃብቶች ይቀርቡ ዘንድ  እናሳስባለን።

፬  /የመከላከያ ሹመት አሁንም አንድን ብሄር ያማከለ በመሆኑ ያደረጉት የኤታማዦር ለውጥ በምንም  መመዘኛ  ተቀባይነት የለውም። ዶ/ር አብይ አህመድ አጥብቀው እንደተናገሩት መከላከያው የሃገር ዋስትና እንጅ የአንድ ድርጅትና ቡድን መጠቀሚያ ባለመሆኑ የሹመቱን ቦታ በጥሩ ውጤት በተማሩ፥ በወታደራዊ  ትምህርት ሰፊ እውቀትና ልምድ ባካበቱ፥ ሃገራችንንና ሰራዊታችንን  ወደ ተሻለ  ደረጃ ከፈ ሊያደርጉ የሚችሉ ኢትዮጵያዊያን ማካተት አለበት እንላለን። ለሹመትና መዓረግ አሰጣጥ ዋናው መመዘኛ ልምድ ችሎታና  እውቀት  እንዲሆን አጥብቀን እናሳስባለን። የሃገራችን ከፈተኛው የወታደራዊ ቦታ እውቀት በሌላቸው የህወሃት አባላት ብቻ መያዙ አስተዳደርዎን ደካማ ከማድረጉም ባሻገር ሃገራችንን መከፋፈሉ አይቀሬ ነው ብለን እናምናለን። ይህንንና መሰል ተዛማጅ  ጉዳዮችን ከግምት በማስገባት አስቸኳይ ለውጥ እንዲያመጡ አጥብቀን እናሳስባለን።

በመጨረሻም ሕዝባችን የሚካሄዱትን ሃገራዊ ሁኔታዎች በመከታተል መብቶቹ እስከመጨረሻው እስኪረጋገጡ ድረስ ከትግሉ ግንባር ሳያፈገፍግ ነቅቶ እንዲከታተል ጥሪያችንን እናሰማለን። እንዲሁም በአማራው ሕዝብ ድርጅቶችና የዲሞክራሲና የለውጥ ሃይሎች ከጎንዮሽ  ትግልና ከተነጣጠለ አሰላለፍ ወጥታችሁ ሕዝባችንን የሃገሩና  የመብቱ  ባለቤት  ለማድረግ የምታደርጉትን ጥረት እንድታጠናክሩ በዚህ አጋጣሚ እየገለጽንከማናቸውም ታጋይ ሃይሎች ጋር በመተጋገዝ ለመስራት አንድ አማራ ዝግጁ መሆኑን  ልናሳውቃችሁ እንወዳለን።

እዉነተኛ አማራ  እንኳንስ ተነጋግሮ ተያይቶ መግባባት  አለበት!!

አማራዉ አያቶቹ  በገነቧት ኢትዮጵያ ሃገሩ ላይ በክብር  ይኖራል!!

         አንድ  አማራ  ንቅናቄ    !!