አንድ እግረኛ ያወራውን፣ ሺህ ፈረሰኛ አይመልሰውም (ከኢትዮጵያ ኢኮኖሚክስ ማህበር)

0

ኢት-ኢኮኖሚ           /ET- ECONOMY

ከአለፈው የቀጠለ

{1} የቻይና የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት

ፖሊ ጂሲኤል የተባለ የቻይና ኩባንያ፣ የካሉብና ሂላላ የተፈጥሮ ጋዝ ክምችት በአራት ቢሊዩን ዶላር ወጪ የግንባታ ሥራ  በኢትዩጵያ ሶማሌ ብሄራዊ ክልል በኦጋዴን ቤዚን ውስጥ የተፈጥሮ ጋዝ ለማልማትና ነዳጅ ለመፈለግ በእንቅስቃሴ ላይ የሚገኘው ፖሊ ጂሲኤል የተባለ የቻይና ኩባንያ ከማእድን ሚኒስቴር ጋር በ2013 እኤአ የፔትሮሊየም ፍለጋና ልማት ስምምነት መፈራረሙ ይታወቃል፡፡ኩባንያው በካሉብና በሒላላ አካባቢዎች በቆፈረው ጉድጎዶች መልካም ውጤት ማግኘቱ ን አስታውቆል፡፡

  • የካሉብ የጋዝ ክምችት ከአዲስ አበባ ደቡብ ምሥራቅ 1200 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ ሲሆን በ1972 እኤአ ቴኔካ የተሰኘ የአሜሪካን ኩባንያ ካሉብ አንድ ጉድጎድ በመቆፈር ፣የተፈጥሮ ጋዝ ክምችቱን ማግኘቱ እንዲሁም ቴኔካ ኩባንያ በሂላላ አነስተኛ መጠን ያለው ድፍድፍ ነዳጅ ማግኘታቸውን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
  • እኤአ በ1980ዎቹ የቀድሞው የሶብት ኅብረት ኩባንያ የሆነው ስፒ የነዳጅ ፍለጋ ጉድጎዶች በመቆፈር የተፈጥሮ ጋዝ ክምችቱን መጠን ያረጋገተ ሲሆን በሂላላ ተጨማሪ የተፈጥሮ ጋዝ ክምችት አግኝቶ ነበር፡፡ በጥናቶቹ መሠረት በካሉብና በሂላላ ያለው የተፈጥሮ ጋዝ ክምችት መጠን 118 ቢሊዩን ሜትር ኪዩብ እንደሆነ በተለያዩ ኩባንያዎች የተካሄዱ ጥናቶች ይጠቁማሉ፡፡
  • በ2013 እኤአ ፖሊ ጂሲኤል የተባለ የቻይና ኩባንያ ከማእድን ሚኒስቴር ጋር የፔትሮሊየም ፍለጋና ልማት በመስማማት በኦጋዴን 117151 ካሬ ኪሎ ሜትር የነዳጅ ፍለጋ ይዞታ ባለቤት ሆኖል፡፡ ኩባንያው የተፈጥሮ ጋዝ ክምችቶን ለማልማት ጂቡቲ ወደብ ድረስ 830 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው የጋዝ ኤክስፖርት ተርሚናል ለመገንባት በእንቅስቃሴ ላይ ይገኛል፡፡ የፕሮጀክቱ አጠቃላይ ወጪ አራት ቢሊዩን ዶላር ይገመታል፡፡ የጋዝ ኤክስፖርት ተርሚናል ግንባታ የመሠረት ድንጋይ በመጋቢት ወር 2008 ዓ/ም ተቀምጦል፡፡የጋዝ ማስተላለፍያ ባንባ ዝርጋታ ሥራ በነሐሴ 2008 ተጀምሮል፡፡ ፖሊ ጂሲኤል ኩባንያው በዓመት አራት ቢሊዩን ሜትር ኪብ ጋዝ በማምረት አብዛኛውን ምርት ወደ ቻይና ለመላክ አቅዶል፡፡ በተጨማሪም ኩባንያው የፔትሮ ኬሚካል ምርቶች ማምረቻ ሊያቆቁም በጥናት ላይ ነው፡፡ ኩባንያው የተፈጥሮ ጋዝ ምርቱን በ2019 እኤአ ይጀምራል፡፡ በሪፖርተር ጋዜጣ መረጃ መሠረት የተጠናቀረ ነው፡፡

ሃገራችን ኢትዩጵያ ከዚህ የተፈጥሮ ጋዝ ክምችትና የፔትሮ ኬሚካል ምርቶች ማምረቻ የምታገኘው ጥቅም፣ የፕሮጀክቱ ጥናት  በድብቅ እንደ ማፍያ ሥራ መረጃው ይፋ ባለመሆኑና ሊጠይቁ የሚችሉ ህዝብና ጋዜጠኞችን በማፈን በሚስጢር የሚከናወን ሴራ እንዳለ እሙን ነው፡፡ የኦጋዴን መሬት ለቻይና ኩባንያ ካልተሸጠ በቀር የሃገሪቱ ኃብት ድርሻ ከፕሮጀክቱ ምን ያህል እንደሆነና ለህዝብ በመገናኛ ብዙሃን በግልፅ ማሳወቅ የአንድ መንግስት ሥራና ኃላፊነት ነው፡፡  የኢትዩጵያ መንግስት ከቻይና መንግስት 17.5 ቢሊዩን ዶላር ብድር እንዳለበት የዓለም ባንክ በቅርቡ አስታውቆል፡፡ የኢትዩጵያ መንግስት ከውጭ ሃገራት የተበደረውን ብድር ለህዝብና ለምጣኔ ኃብት ጠበብት፣ ለአጥኝዎች፣ ለፓርላማና ለህዝብ ማሳወቅ ይጠበቅበታል፡፡ በመረጃው አሰጣጥ የተዛቡና የመዘበራረቀ የአሀዞች ማቅረብ ለምን ይሆን፡፡ ቀጥሎ አስተውሉት፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ ዶክተር ቴዎድሮስ አዳኖም በኢትጵያ ሄራልድ ጋዜጣ፣ ኢትዩጵያ፣ ጅቡቲና ቻይና በህብረት የአራት ቢሊዩን ዶላር የተፈጥሮ ጋዝ ክምችት ፕሮጀክት፣የድፍድፍ ማጣሪያ ፕልንትና፣  700 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው የጋዝ ኤክስፖርት ተርሚናል እስከ 12 ሚሊዩን ኪዩቢክ ሜትር የተፈጥሮ ጋዝ ምርት በአመት፡፡ ከዚህ ውስጥ ኢትዩጵያ፣ 10 ሚሊዩን ኪዩቢክ ሜትር የተፈጥሮ ጋዝ ምርት ለቻይና በአመት ኤክስፖርት እንደምታደርግ ተገልፆል፡፡  ፖሊ-ጂሲኤል ተባለ የቻይና ኩባንያ የፕሮጀክቱን ግንባታ ውጪ እንደሚሸፍንና በሦስት አመታት ውስጥ ግንባታው እንደሚያልቅ አናዶሉ ኤጀንሲ አስታውቆል፡፡ የኢትዩጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ  አቶ ተክለወልድ አጥናፉ፤ የኢብባ ምክትል ገዥ አቶ ዮሐንስ አያሌው፣  አቶ በቃሉ ዘለቀ የኢትዩጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዜዳንት፣ የልማት ባንክ ፕሬዜዳንት በህወሃት/ኢፈርት እየታዘዙ ሀገሪቱን በማትወጣው ብድርና የእዳ ጫና ውስጥ ከተቶች ደላሎቹ  እነ ዘመዴነህ ንጋቱ፣ ዳዊት ገ/እግዚአብሄር፣ እነ ጀነራል ፃድቃንና አበበ ስለ ሃገራችን እድገት ቱልቱላ ሲነፉ ነበር፡፡

‘‘Ethiopia, Djibouti, China to launch 4 Bln. USD natural gas project’’

Addis Ababa- Ethiopia says physical work on a massive four billion USD joint natural gas project between Ethiopia, Diouti and China will soon be launched. The announcement was made Thursday by Foreign Minister Dr. Tedros Adhanom at the opening of the 4th Ethiopia- Djibouti Joint Ministerial Commttee Meeting in Addis. …The project is made up of a natural gas pipeline, a liquefaction plant, and an export terminal at Damerjog, Djibouti.  The project, which includes a 700 kilometere pipeline capable of transporting up to 12 billion cubic meteres of natural gas per year, would enable Ethiopia to export 10 million cubic meters of liquefied natural gas (LNG) to China annually. Chines firm POLY-GCL Petroleum Group Holding Ltd. Will finnce the project, which is scheduled to take three years to complete, according to Anadolu Agency. (Source:- The Ethiopian Herald, Saturday 23 July 2016)

የቻይና መንግስት በኢትዬጵያ ኤሌትሪክ ኃይል ማመንጫ ዘርፍ ተሳትፎን በተመለከተ Chinese engagement in the Ethiopian Power Sector

የቻይና መንግስት በኢትዬጵያ ኤሌትሪክ ኃይል በማመንጨት፣ኃይል በማከፋፈልና  ዓለም ዓቀፍዊ የኃይል አቅርቦት የማመቻቸት ፕሮግራም ዘርፍ ተሳትፎው ከአለፈው አስር አመታት ጀምሮ እያደገ መጥቶል፡፡ ከሠንጠረዡ ለመረዳት እንደሚቻለው የቻይና ካንፓኒዎች በሁሉም የኤሌትሪክ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች ላይ በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ፡፡ ጣሊያንያዊ  ከሆነው ሳሊኒ ካንፓኒ ከሚሰራው የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት  በስተቀር ማለት ይቻላል፡፡ የቻይና ካንፓኒዎች በሁሉም የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች (Power Generation Total) ያገኙት አጠቃላይ የኮንትራት ዋጋ 1.692.65 ቢሊዬን ዩኤስ ዶለር(21.1 ቢሊዮን ብር ) ይገመታል፡፡ የቻይና ካንፓኒዎች ከኃይል ማመንጫ ማከፋፈያ ፕሮጀክቶች( Power Transmission Total) 354 ሚሊዬን ዩኤስ ዶለር (4.4ቢሊዮን ብር) እና ከመንግስታቶች ዓለም ዓቀፍዊ የኃይል አቅርቦት የማመቻቸት ፕሮግራም (Universal Access Program) 23 ሚሊዬን ዩኤስ ዶለር(288 ሚሊዮን ብር ) አግኝተዋል፡፡ (Source: Ethiopian Electric Power Corporation, September, 2009)

Ethiopia to Get Chinese Funds for $1 Billion Hydropower Line, April 26, 2013 | By William Davison
“April 26 (Bloomberg) — Ethiopia will receive funds from China for a transmission line valued at $1 billion that will bring electricity from a hydropower plant to the capital, Addis Ababa according to a government official. The 619-kilometer (385-mile) link from the 6,000-megawatt Grand Ethiopian Renaissance Dam on the Blue Nile River will be constructed over the next three years by China Electric Power Equipment and Technology, Deputy Prime Minister of Economy and Finance Debretsion Gebremichael told reporters in Addis Ababa today.
“The construction of this big transmission line will help benefit our economy and to ensure our industrial development,” he said. Funding for the two 500-kilovolt cables will come primarily from the Export-Import Bank of China, Debretsion said. Ethiopia, which according to the World Bank has the second-highest hydropower potential in Africa after the Democratic Republic of Congo, hopes to finish the self-funded $5-billion Nile dam in 2018. The project will be the continent’s biggest power plant.”

የኢትዩጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን ኮርፖሬሽን ይባል የነበረው አሁን ኢትዩ ቴሌኮም በመባል ይታወቃል፡፡ በኢትዩጵያ አጠቃላይ የቴሌኮሙንኬሽን አገልግሎት ማለትም የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎቶችና ከላይ የተጠቀሱትን ተግባራት በመስጠት ይታወቃል፡፡ በኢትዩጵያ መንግስት ሞኖፐሊ ፣በብቸኝነት ተጠቃሎ በንብረትነት ከተያዙ የህዝብ ሃብቶች መኃከል  በገቢው ትልቅነት በአንደኛ ደረጃ የኢትዩጵያ አየር መንገድ ሲሆን በመቀጠልም ኢትዩ ቴሌኮም በሁለተኛ ደረጃነት፣ ኢትዩጵያ ንግድ ባንክ፣ኢትዩጵያ መብራት ኃይል ኮርፖሬሽን ድርጅትና፣ ኢትዩጵያ መርከብ አገልግሎት የመንግስት ንብረቶች በመሆን ይታወቃሉ፡፡  ኢትዩ ቴሌኮም የአመት አጠቃላይ ገቢ 300 ሚሊዩን ዩኤስ ዶለር (6, 000, 000 ,000 ቢሊዩን ብር) ፣ተንቀሳቃሽ ገቢ (Operating income) 3,308,636,000 ቢሊዩን ብር እንዲሁም  አጠቃላይ ገቢ (Net income) 1,527,255,000 ቢሊዩን ብር ሲሆን፤ ‹ገንዘብ የምትታለብ ላም› በመባል በጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊና ኃይለማርያም ደሳለኝ በማለት ያሞካሾሉ፡፡በእርግጥ ኢትዩ ቴሌኮምን የኢትዩጵያ መንግስት ያልባታል፣ የቻይና መንግስት የታለበውን ይጠጣል፡፡በአጠቃላይ የኢትዩ ቴሌኮም  22, 288 ሠራተኞች ያሉት ትልቅ ድርጅት ነው፡፡ በ2006 እኤአ የኢትዩጵያ ቴሌኮሙንኬሽን ኮርፖሬሽን ከቻይና መንግስት ንብረት ከሆኑ ሦስት ካንፓኒዎች ጋር ማለትም ዜድቲኢ ኮርፖሬሽን፣ ሃዊ ቴክኖሎጂና የቻይና ዓለም ዓቀፍ ቴሌኮሙንኬሽን ግንባታ ኮርፖሬሽን ጋር 1.5 ቢሊዩን ዩኤስ ዶላር (12,585,000,000 ቢሊዩን ብር) ብድር ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

“By 2005, China’s embassy in Addis Ababa hosted more high-level visits than any Western mission and Chinese companies had become a dominant force building highways and bridges, dams and power stations, cell phone networks, schools, and pharmaceutical factories. Ethiopia’s trade minister said that “China has become our most reliable partner.” China became involved in nearly every aspect of Ethiopia’s economy. One agreement in 2006 with three Chinese companies is valued at $1.5 billion in commercial suppliers’ credit at Libor (interbank lending rate) plus 1.5 percent to develop cellular and 3G services across Ethiopia.”Source:-Ethiopia and China: How Two Former Empires Connected in the 20th Century-by David H. Shinn June 11, 2014

በአጠቃላይ ከላይ ከሠንጠረዡ እንደሚስተዋለው፣ከ2006 እኤአ እስከ 2013እኤአ የቻይና መንግስት ከቻይና የቴሌኮም ካንፓኒ፤ዜድቲኢ ZTE Corporationና ሀዊ Huawei Technologies Co. Ltd. የቻይና ኮምኒስት ፓርቲ ንብረት የሆኑት ድርጅቶች ጋር የኢትዬጵያ ቴሌኮምኒኬሽን ኮርፖሬሽን (አሁን ኢትዬቴሌኮም) የ4.8 ቢሊዬን ዩኤስ ዶለር (72,142,100,000 ቢሊዬን ብር) ብድር በመፈራረም የእዳው ክፍያም ከኢትዩጵያ የሠሊጥ ምርት ወደ ቻይና በመላክ እንደሚወራረድ ይታወቃል፡፡ በሌላ ዜና የቻይናኢትዬ ቴሌኮም ድርጅት ዜድቲኢ ኮርፖሬሽን ከብሄረ-አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዲን) የንግድ ድርጁት ጥረት ጋር በመሆን በባህርዳር ከተማ፤ በዓመት 3 ሚሊዩን የሚያመርት ጣና የሞባይል ስልክ መገጣጠሚያ ፋብሪካ በመክፈት ህብረተሰቡ የውጭ የኢንተርኔት ድረ-ገፆችን እንዳይጠቀም የሚያደርግ የሞባይል ምርት በ370 ብር ዋጋ በማስራጨት ላይ ይገኛሉ፡፡፡

ከ2008እኤአ እስከ 2014እኤአ የኢትዬጵያ አየር መንገድ ድርጅት 5,608,000,000 ቢሊዩን ዩኤስ ዶላር ወይም (104,599,294,400 ቢሊዩን ብር) አይሮፕላኖች ለመግዛት የውጭ ብድር ተበድሮል፡፡ የቻይናው ኤክፖርት ኢንፖርት ባንክ አይሮፕላኖቹን 1,730,000,000 ቢሊዩን ዩኤስ ዶላር ወይም (32,267,614,000 ቢሊዩን ብር) በማበደር የኢትዬጵያ አየር መንገድ አይሮፕላኖች በወለድ አግድ collatoral እንደተያዘ አጥኝዋች ይናገራሉ፡፡

በ1975 እኤአ የኢትዬጵያ የውጭ ብድር 343.7 ሚሊዩን ዩኤስ ዶለር የነበረ ሲሆን ይህውም አመታዊ አጠቃላይ የአገር ውስጥ ምርት (GDP) 14% እጅ ይይዝ ነበር፡፡ በ1991 እኤአ የኢትዬጵያ የውጭ ብድር 9.1 ቢሊዬን ዩኤስ ዶለር የነበረ ሲሆን ይህውም አመታዊ አጠቃላይ የአገር ውስጥ ምርት (GDP) 214% እጅ ይይዝ ነበር፡፡ በጁን 30 1999 ይሄ አሃዝ 10.2 ቢሊዬን ዩኤስ ዶለር ከፍ ብሎል፡፡ በ2013 እኤአ የኢትዬጵያ የውጭ ብድር 16.11ቢሊዬን ዩኤስ ዶለር  የነበረ ሲሆን ይህውም ከአጠቃላይ የአገር ውስጥ ምርት (GDP) 285.5% እጅ ይይዝ ነበር፡፡ የውጭ ብድር ከፍተኛ እዳ ከተቆለለባቸው ደሃ አገራቶች መኃል የኢትዬጵያ አጠቃላይ የውጭ ብድር ከ20 እስከ 30 ቢሊዬን ዩኤስ ዶለር (373,036,000,000 ቢሊዩን ብር እስከ 559,554,000,000 ቢሊዩን ብር) እንደሚደርስ ይገመታል፡፡ የኢትዬጵያ አየር መንገድ፣ኢትዬ ቴሌኮምና የኢትዬጵያ መብራት ኃይል ባለሥልጣን የመሳሰሉ ድርጅቶች በራሳቸው የሚያደርጉት የውጭ ብድር 10  ቢሊዬን ዩኤስ ዶለር ይገመታል፡፡ለዚህም ዋና ማስረጃ የህወሃት/ኢህአዲግ መንግስት ለኢትዬጵያ አየር መንገድ ድርጅትና ለኢትዬቴሌኮም እዳ የኢትዬጵያ መንግስት እዳ እንዳልሆነና  በብድሩም መንግስት ተጠያቂም እንዳአይደለ ለዓለምአቀፍ የገንዘብ ተቆም ማረጋገጡን በማስረጃ ቀጥሎ ይቀርባል፡፡

የቻይና መንግስትና የኢትዬጵያ የቴሌኮሚኒኬሽን ዘርፍ

የቻይና ካንፓኒዎች በኢትዬጵያ የቴሌኮሚኒኬሽን ዘርፍ ትልልቅ ፕሮጀክቶችን በማሸነፍ ኃያልነታቸውን አስመስክረዋል፡፡ የቻይና የቴሌኮም ካንፓኒ፤ዜድቲኢ የቻይና መንግስት ንብረት የሆነው ድርጅት ለኢትዬጵያ ቴሌኮም 1.5 ቢሊዬን ዩኤስ ዶለር የብድር አቅርቦት በማመቻቸትና በማበደር የቴሌኮሚኒኬሽን አገልግሎት ዘርፍን መቆጣጠር ችለዋል፡፡ የብድሩ ስምምነት መሠረት ዜድቲኢ ያለአንዳች ጫረታ ሥራውን እንዲሰራ ተሰጥቶታል፡፡ ይሄ የብድር ስምምነት ምናልባት በአሁኑ ግዜ የገበያ ዋጋ ስሌት መንግስታዊው ኢትዬጵያ የቴሌኮሚኒኬሽን የሽያጭ ዋጋ ያክላል፡፡ የኢትዬጵያ የቴሌኮሚኒኬሽን አገልግሎት ዘርፍ ከአውሮፓና አሜሪካ በተተከሉ መሳሪያዎች  በጥራትና ብዛት የቴሌኮሚኒኬሽን ዘርፉ እድገቱ ሲገነባ ቆይቶ አሁን በዚህ አስር አመታት ውስጥ በቻይና ቴሌኮም ቴክኖሎጅ መተካት ግድ ብሎታል፡፡ በዚህም ምክንያት አሁን ያለው የቴሌኮሚኒኬሽን መሳሪያዎች በቻይና  አዲስ የቴሌኮሚኒኬሽን መሳሪያዎች መተካት ይኖርባቸዋል፡፡ መሳሪያዎች በርካሽ ዋጋና መቀያየሪያዎቹም ለሚቀጥሉት ዘመናት በቻይና ሰራሽ ቴክኖሎጅ ቁጥጥር ስር ለማደር ይገደዳል፡፡ ለዚህም ዋናው ምክንያት የቻይና የቴሌኮም ቴክኖሎጅ ከአውሮፓና አሜሪካ ቴክኖሎጅ ጋር በቀላሉ የማይገጥም በመሆኑ፤ የኃላኃላ የኢትዬጵያ የቴሌኮሚኒኬሽን ዘርፍ ሂሳብ እንደሚያወራርድ ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ የቻይና መንግስት የቴሌኮሚኒኬሽን ዘርፍ በመቆጣጠር የሃገሪቱን ደህንነትና መረጃ  አጠቃላይ ብሄረዊ ሚስጢር ሁሉ በእነሱ ቁጥጥር ስር መሆኑንአደጋ እንዳለው አንድ ቀን ገሃድ ይወጣል፡፡ የቻይና መንግስት ዛሬም በሃገሪቱ ውስጥ የተነሳውን ህዝባዊ እንቢተኝነትና ተጋድሎ ለማጨናገፍ የኢንተርኔት አገልግሎቶችን ማለትም ፋስቡክ፣ ቲውተር፣ዋት ኢዛ አፕ፣ኢሞ፣ቨይበር፣ ቲውብ፣ ኢትዩጵያዊያን ድረ-ገፆችን (ኢትዩሚዲያ፣ ኢትዩፕን ሪቪው፣ ዘ ሃበሻ፣ ወዘተ) ከውጭ የሚተላለፉ የሬዲና የቴሌቪዝን ስርጭቶችንና የሃገር ውስጥ ሚዲያዎችን በማፈን ታላቅ ሥራ አከናውነዋል፡፡ በዚህ አመፅም አንዱም የቻይና ፋብሪካዎች አለመነካታቸው አስፈላጊው መረጃ በእጃቸው እንደሆነ ይመሰክራል፡፡ የቻይና መንግስት የህወሓት የጦር አበጋዞች መንግስት መከታና ጋሻ ነው፣ የቻይና ኢንቨስተሮች ከኢትዩጶያ እስካልወጡ ድረስ ህወሓት መንግስት አይወድቅም፡፡ ቻይና መንግስታዊ ኢንቨስትመንት በሃገሪቱ ሰፍኖል የግል ዘርፉ የተሰማራበትን ሥራ በሙሉ ነጥቀው ይዘዋል፡፡ 

የኢትዬጵያ የቴሌኮሚኒኬሽን አገልግሎት ዘርፍ በ2006 እኤአ ኢትዬጵያ በዘርፉ ካረገችው የመዋዕለ ንዋይ ፍሰት 34,520,000 ሚሊዬን ዶለር የቻይና 12,113,000 ሚሊዬን ዶለር ከመቶ 35 እጅ በመቶ ቻይና ድርሻ ነበራት፡፡ በ2007 እኤአ ኢትዬጵያ በዘርፉ  1,048,600,000 ቢሊዬን ዶለር ድርሻ ሲኖራት ቻይና  1,027,600,000 ቢሊዬን ዶለር ከመቶ 97.99 እጅ ዘርፉን በመቆጣጠር የአንበሳውን ድርሻ ለመያዝ በቅታለች፡፡

ከ2006 እኤአ እስከ 2013እኤአ  ህወሃት/ኢህአዲግ መንግስትና የቻይና መንግስት ከቻይና የቴሌኮም ካንፓኒ፤ዜድቲኢ ZTE Corporationና ሀዊ Huawei Technologies Co. Ltd. ድርጅቶች ጋር የኢትዬቴሌኮም የ4.8 ቢሊዬን ዩኤስ ዶለር ወይም (72,142,100,000 ቢሊዬን ብር) ብድር በመፈራረም በእዳው ጫና ወደፊት የኢትዩጵያ ቴሌኮምኒኬሽን ዘርፍ ወደ ግል ዘርፍ በሚዘዋወርበት አስገዳጂ ሁኔታ ለቻይና መንግስት ለቻይና ቴሌኮም ካንፓኒዎች እንደሚሸጥ ምንም ጥርጥር የለውም፡፡

በማዕድንና ሚንራል በኩልም ከጠቅላላው የኢትዬጵያ 10,608,458 ቢሊዬን ዶለር የመዋዕለ ንዋይ ፍሰት የቻይና ድርሻ 6,957,130 ቢሊዬን ዶለር ሲሆን ይህውም ከመቶ 65.58 እጅ እንደሆነ ያሳያል፡፡ በትራንስፖርት ዘርፍም  ከጠቅላላው የኢትዬጵያ 356,220,000 ሚሊዬን ዶለር የመዋዕለ ንዋይ ፍሰት የቻይና ድርሻ 352,570,000 ሚሊዬን ዶለር ሲሆን ይህውም ከመቶ 99.02 እጅ እንደሆነ ያሳያል፡፡ በአጠቃላይ የኢኮኖሚ ዘርፎች ማለትም በግብርና፤በኢንድስትሪና በአገልግሎት ዘርፎች ከጠቅላላው የኢትዬጵያ 13,535,999,000 ቢሊዬን ዶለር የመዋዕለ ንዋይ ፍሰት የቻይና ድርሻ 1,852,532,958 ቢሊዬን ዶለር ሲሆን ይህውም ከመቶ 13.68 እጅ እንደሆነ ያሳያል፡፡

የኢትዩጵያ ቴሌኮሙንኬሽን ኮርፖሬሽን ጋር የተደረገው ስምምነት የሞባይል አገልግሎትን ከ 1.5 ሚሊዩን ወደ 7 ሚሊዩን ለማሳደግ፣የመስመር ስልክ አገልግሎት ዘርፍን 1ሚሊዩን ወደ 4 ሚሊዩን ከፍ ለምድረግና የፋይበር ኦፕቲክ መረብ አገልግሎት ከ4000 ወደ 10 000 ኪሎ ሜትር በ2010 እኤአ ለመስራት ተስማሙ፡፡ በኢትዩጵያ መንግስት እቅድ መሠረት፤ የሃገሪቱን ቴሌኮሙንኬሽን መሠረተ ልማት ግንባታ ለማሻሻል በ2.4 ቢሊዩን ዩኤስ ዶለር የኢትዩጵያ መንግስትና የቻይና መንግስት በጋራ ስለላ ተግባር በኢትዩ ቴሌኮም  በኩል፣ ኢንተርኔት ጽሁፍና ኅትመት ሳንሱር በማድረግና በመመርመር የኢንተርኔት የማጥለል ሥራ (internet filtering)ና መልእክቶችን በኢትዩ ቴሌኮም  የኢንተርኔት  ክትትልና ሳንሱር በወንጀል ድርጊት ሆኖ በ2012 እኤአ ህግ በማውጣት እስከ 15 አመት እስራት እንደሚስፈርድ ተደንግጎል፡፡ ኢትዩ ቴሌኮም  በተለያዩ ኢትዩጵያዊያኖች ንብረት የሆኑ የባህር ማዶ ድረ-ገፆችን የመንግስት የፖለቲካ ተቃዋሚዎች ሃሳብ፣ በሃገር ውስጥ እንዳይታዩ በማገትና የተለያዩ የውጭ  ድረ-ገፆችን በመዝጋት የስራ ልምድ አካብተዋል፡፡ በ2005 እኤአ ህዝባዊ ምርጫ ግዜ የኢትዩጵያ ቴሌኮሙንኬሽን ኮርፖሬሽን የሞባይል አጭር መልእክቶች እንዳይተላለፍ በማድረግ ለሁለት ዓመታት ያህል እግዱ ቀጥሎ ነበር፡፡ በ2008 እኤአ የጋዜጠኞች መብት ተሞጋች ኮሚቴ(Committee to Protect Journalists) ድረ-ገፆ መስኮት ለብዙ ወራቶች ተዘግቶ ነበር፡፡

የኢትዬጵያ አየር መንገድ፣አይሮፕላኖቹን እያስያዙ ከተለያዩ ባንኮች የሚያደርጎቸውን የውጭ ብድሮች ቀጥለን እንመልከት፡፡ በ2008 እኤአ ስምንት ቦንባርዲየር ኪው 400 አይሮፕላኖች 242 ሚሊዩን ዩኤስ ዶላር፣በ2010እኤአ አስር ቦይንግ 737-800 አይሮፕላኖች  767 ሚሊዩን ዩኤስ ዶላር ዋጋ ለመግዛት ተስማምተዋል፣ የቻይናው ኤክፖርት ኢንፖርት ባንክ የ1.6 ቢሊዩን ዩኤስ ዶላር ለአስር ቦይንግ ድሪም ላይነርስ አበድሮል፡፡ በ2011 እኤአ አራት ቦይንግ 777ኤፍ አይሮፕላኖች በ1.1 ቢሊዩን ዩኤስ ዶላር ለመግዛት ስምምነት ተፈፅሞል፡፡ በ2012 እኤአ አምስት ኪው 400 አይሮፕላኖች   160 ሚሊዩን ዩኤስ ዶለርና ተጨማሪ አንድ ቦይንግ 777-200ኤልአር አይሮፕላን  276 ሚሊዩን ዩኤስ ዶለር  ለመግዛት ስምምነት ተደርጎል፡፡ በተለያየ ግዜትም የተገዙት አይሮፕላኖች ወደ አገር ውስጥ ገብተዋል፡፡በ2013 እኤአ ኤር ሊዝ ኮርፖሬሽንና የኢትዬጵያ አየር መንገድ ሁለት ቦይንግ 777-300 ኢአር አይሮፕላኖች ለመከራየት  ተስማምተው፣ የቻይናው ኤክፖርት ኢንፖርት ባንክ የ130 ሚሊዩን ዩኤስ ዶላር ለኢትዬጵያ አየር መንገድ  ብድር አበደረ፡፡ በ2014 እኤአ የኢትዬጵያ አየር መንገድ 20 ቦይንግ 737 ማክስ 8 አይሮፕላኖች  የ2.1 ቢሊዩን ዩኤስ ዶላር ከዩኤስ አቪየሽን ጋር ስምምነት አደርገዋል፡፡ በተጨማሪም አስራአምስት 737 ማክስ 8 ነዳጅ ቆጣቢ አይሮፕላኖች ለመግዛት ስምምነት ፈፅመዋል፡፡በአጠቃላይ ከ 2008እኤአ እስከ 2014እኤአ የኢህአዲግ መንግስትና የኢትዬጵያ አየር መንገድ ድርጅት 5,608,000, 000 ቢሊዩን ዩኤስ ዶላር ወይም (104,599,294,400 ቢሊዩን ብር) አይሮፕላኖች ለመግዛት የውጭ ብድር ተበድሮል፡፡ የቻይናው ኤክፖርት ኢንፖርት ባንክ አይሮፕላኖቹን 1,730,000,000 ቢሊዩን ዩኤስ ዶላር ወይም (32,267,614,000 ቢሊዩን ብር) በማበደር የአንበሳውን ድርሻ በመያዝ የኢትዬጵያ አየር መንገድ አይሮፕላኖች በወለድ አግድ collatoral በመያዝ እንደሚያበድር ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ የኢትዬጵያ አየር መንገድ Total assets (አጠቃላይ ንብረት) 26.368 ቢሊዩን ብር(1,413,697,338 ቢሊዩን ዩኤስ ዶላር)በ 2012እኤአ ነበር፡፡ በእዳ ብዛትም የኢትዬቻይና አየር መንገድ እንዳይባል ያሰጋዋል፡፡የኢህአዲግ መንግስትና የኢትዬጵያ አየር መንገድ ድርጅት የውጭ ብድር በተመለከተ ብቻ የቀረበ ሲሆን፣ የአገር ውስጥ ብድር ከተለያዩ ባንኮች የተበደሩትን እንደማይጨምር አንባቢ ሊገነዘብ ይገባል፡፡ 2012እኤአ የኢትዩጰያ  የአገር ውስጥ ብድር 45.5 ፐርሰንት ከዓመታዊ አጠቃላይን ብሔራዊ ምርት የነበረ ሲሆን የውጭ ብድር 10 ፐርሰንት ከዓመታዊ አጠቃላይን ብሔራዊ ምርት የያዘ ነበር፡፡

የኢትዬጵያ ንግድ ባንክ ዲሴንበር 6/2011እኤአ  የቻይና አስመጭና ላኪ ባንክ( Chinese Export and Import Bank)ለኢትዬጵያ ዩኤስ 400 ሚሊዩን ዶለር (6.9 ቢሊዬን ብር) ሁለት  የብድር ስምምነቶች አድርገዋል፡፡ከጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ጋር የባንኩ ምክትል ፕሬዜዳንት ዘሁ ሆንጃይ( Zhu Hongjie) እንደገለጹት ባንኩ 1.81ቢሊዬን ዩኤስ ዶለር(31ቢሊዩን ብር) እንዳበደሩ ገልጸዋል፡፡አንዱ ስምምነት ባንኩ 100 ሚሊዩን ዶለር ለአዲስ አበባ የውሃ ሥራዎች አቅርቦት ፕሮጀክቶች ግንባታ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ከኢትዬጵያ ንግድ ባንክ ጋር 300 ሚሊዩን ዶለር የባንኩን የብድር አቅርቦት ከፍ ለማድረግ እንደሆነ ተዘግቦል፡፡ ዘሁ ሆንጃይ እንደገለፁት ከሆነ ባንኩ እስካሁን 11.4 ቢሊዬን ዩኤስ ዶለር(272.2 ቢሊዩን ብር)እንዳበደሩ ገልጸዋል፡፡

ኢትዬቴሌኮምበአጠቃላይ፣ከ2006 እኤአ እስከ 2013እኤአ የቻይና መንግስት ከቻይና የቴሌኮም ካንፓኒ፤ዜድቲኢ ZTE Corporationና ሀዊ Huawei Technologies Co. Ltd. የቻይና ኮምኒስት ፓርቲ ንብረት የሆኑት ድርጅቶች ጋር የኢትዬጵያ ቴሌኮምኒኬሽን ኮርፖሬሽን (አሁን ኢትዬቴሌኮም) የ4.8 ቢሊዬን ዩኤስ ዶለር (72,142,100,000 ቢሊዬን ብር) ብድር በመፈራረም የእዳው ክፍያም ከኢትዩጵያ የሠሊጥ ምርት ወደ ቻይና በመላክ እንደሚወራረድ ይታወቃል፡፡

በአጠቃላይ በ1975 እኤአ የኢትዬጵያ የውጭ ብድር 343.7 ሚሊዩን ዩኤስ ዶለር የነበረ ሲሆን ይህውም አመታዊ አጠቃላይ የአገር ውስጥ ምርት (GDP) 14% እጅ ይይዝ ነበር፡፡ በ1991 እኤአ የኢትዬጵያ የውጭ ብድር 9.1 ቢሊዬን ዩኤስ ዶለር የነበረ ሲሆን ይህውም አመታዊ አጠቃላይ የአገር ውስጥ ምርት (GDP) 214% እጅ ይይዝ ነበር፡፡ በጁን 30 1999 ይሄ አሃዝ 10.2 ቢሊዬን ዩኤስ ዶለር ከፍ ብሎል፡፡ በ2013 እኤአ የኢትዬጵያ የውጭ ብድር 16.11ቢሊዬን ዩኤስ ዶለር  የነበረ ሲሆን ይህውም ከአጠቃላይ የአገር ውስጥ ምርት (GDP) 285.5% እጅ ይይዝ ነበር፡፡ የውጭ ብድር ከፍተኛ እዳ ከተቆለለባቸው ደሃ አገራቶች መኃል የኢትዬጵያ አጠቃላይ የውጭ ብድር ከ20 እስከ 30 ቢሊዬን ዩኤስ ዶለር (373,036,000,000 ቢሊዩን ብር እስከ 559,554,000,000 ቢሊዩን ብር) እንደሚደርስ ይገመታል፡፡ የኢትዬጵያ አየር መንገድ፣ኢትዬ ቴሌኮምና የኢትዬጵያ መብራት ኃይል ባለሥልጣን የመሳሰሉ ድርጅቶች በራሳቸው የሚያደርጉት የውጭ ብድር 11.5  ቢሊዬን ዩኤስ ዶለር ይገመታል፡፡

የኢትዬጵያ ኤሌትሪክ ኃይል 5 ቢሊዩን 490 ሚሊዬን ዩኤስ ዶላር ብድር እንዳለበት ጥናቱ በዝርዝር ያሳያል፡፡ (ሀ) የኢትዬጵያ ኤሌትሪክ ኃይል1.2 ቢሊዩን ዩኤስ ዶላር ከኢትዬጵያ መንግስት የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር IFIs/Government to Sector Institutions on-lending የኢትዬጵያ ኤሌትሪክ ኃይል ሹማምንት ጋር ከተለያዩ ዓለም ዓቀፍ የገንዘብ ተቆማቶች መኃል (የዓለም ባንክ ዓለም ዓቀፍ ልማት ትብብር( International Development Association (IDA)፣ የአፍሪካ የልማት ባንክ African Development Bank(AfDB)፣ የአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ  European Investment Bank (EIB) etc.) ኮንሴሽናል ብድር (Concessionary loans) ለኤሌትሪክ አገልግሎት ዘርፉ አበድረዋል፡፡ኮንሴሽናል ብድር ዋንኛ ገፅታዎች አንደኛ ብድሩ የመካከለኛና የረጅም ግዜ ብድሮችን ሲያካትት፣ የብድሩ ግዜ ለሃያ ዓመታት መሆኑ፡፡ ሁለተኛ የብድሩ የእፎይታ ግዜ (grace period)  አምስት ዓመታት መሆኑና፡፡ በእፎይታ ግዜት ተበዳሪው መንግስት ወለዱን ብቻ እንጂ ዋናውን ገንዘብ (principal) መክፈል አይችልም፡፡ ሦስተኛ ተበዳሪዉ መንግስት የተበደረውን ገንዘብ በአነስተኛ ወለድ ከ3 እስከ 6 በመቶ ጨምሮ የመክፈል ግዴታ ይጠበቅበታል፡፡ (The Sector’s Current Estimated Loan Portfolio  የኢትዬጵያ ኤሌትሪክ ኃይል፣ኤሌትሪክ ኃይል ዘርፍ የውጭ ብድር

(ለ) የኢትዬጵያ ኤሌትሪክ ኃይል 1.0 ቢሊዩን ዩኤስ ዶላር ከተለያዩ የንግድ ባንኮች ብድር ተበድሮል፡፡ ከነዚህም ውስጥ የቻይናና የህንድ የንግድ ባንኮች ለትላልቅ ፕሮጀክቶች የሀይድሮ ኤሌትሪክ ፓወር መሠረተ ልማት ዝርጋታና ግንባታ  የሚውል ብድር ተበድረዋል፡፡ የንግድ ባንክ ብድር (Commercial Banks loans) ዋንኛ ገፅታዎች አንደኛ የብድሩ ግዜ ለአስር ዓመታት መሆኑ፡፡ ሁለተኛ የብድሩ የእፎይታ ግዜ ሦስት  ዓመታት ነው፡፡ በእፎይታ ግዜት ተበዳሪው መንግስት ወለዱን ብቻ እንጂ ዋናውን ገንዘብ መክፈል አይችልም፡፡ ሦስተኛ ተበዳሪዉ መንግስት የተበደረውን ገንዘብ በአነስተኛ ወለድ 6 በመቶ ጨምሮ የመክፈል ግዴታ ይጠበቅበታል፡፡

(ሐ) የኢትዬጵያ ኤሌትሪክ ኃይል 3 ቢሊዩን ዩኤስ ዶላር የቦንድ ብድር Bonds ከሃገር ውስጥና ከባህር ማዶ ዲያስፖራ፣ከመንግስታዊና የግል ዘርፎች ቦንድ በመሸጥ ላይ ይገኛሉ፡፡ የቦንድ ብድር (Bonds loans) ዋንኛ ገፅታዎች አንደኛ የብድሩ ግዜ ለሰባት ዓመታት መሆኑ፡፡ ሁለተኛ ተበዳሪዉ የኢትዬጵያ ኤሌትሪክ ኃይል  የተበደረውን ገንዘብ በአነስተኛ ወለድ 5 በመቶ ጨምሮ የመክፈል ግዴታ ይጠበቅበታል፡፡ በኢትዬጵያ ባንኮች ከሚያበድሩት 27 በመቶ ለቦንድ ግዥ እንዲገዙ ግዳጁ እንደተጣለባቸው ልብ ሊሉ ይገባል፡፡

(መ) የኢትዬጵያ ኤሌትሪክ ኃይል 240 ሚሊዩን ዩኤስ ዶላር በዱቤ አቅራቢ ድርጅቶች Supplier’s  credits በብድር እቃዎች ተበድሮ ገዥቶል፡፡ የዱቤ አቅራቢ ድርጅቶች ብድር (Supplier’s  credits) ዋንኛ ገፅታዎች አንደኛ የብድሩ ግዜ ከ2 እስከ 4 ዓመታት መሆኑ፡፡ ሁለተኛ የብድሩ የእፎይታ ግዜ አንድ  ዓመት ነው፡፡ ሦስተኛ ተበዳሪዉ መንግስት የተበደረውን ገንዘብ በአነስተኛ ወለድ ከ 4 እስከ 6 በመቶ ጨምሮ የመክፈል ግዴታ ይጠበቅበታል፡፡

የብድር አገልግሎት Debt Servicing: የኢትዬጵያ ኤሌትሪክ ኃይል  የተበደረውን ገንዘብ ይሄ ሁሉ እዳ በአለፉት ጥቂት አመታት ውስጥ በመሆኑ የእዳ ክፍያው ከላይ በተጠቀሰው የእፎይታ ግዜ ምክንያት ተበዳሪው ድርጅት  ላይ ተፅዕኖ አያደርግም፡፡ ከዚህ በኃላ የብዙዎቹ እዳዎች የእፎይታ ግዜ ያልቅና የእዳው ክፍያ ከ 2012/13 እኤአ በኃላ ጀመ[ል፡፡ የኢትዬጵያ ኤሌትሪክ ኃይልና የመንግስት የብድር ጫና  በተለይም የመንግስት የእዳ አገልግሎት ጫና 67 በመቶ በ2010 እኤአ እንደደረሰ ይታወቃል፡፡ በቀጣዬቹም አመታት ከ2013 እስከ 2018 እኤአ መከፈል ያለበት የእዳ አገልግሎት የክፍያ መጠን በአማካኝ 250 ሚሊዩን ዩኤስ ዶላር ወይም (5 ቢሊዩን ብር)ና ከዛም በላይ ይሆናል፡፡ ይሄንንም ከሠንጠረዡ ላይ መመልከት ይቻላል፡፡

ለዚህም ዋና ማስረጃ የህወሃት/ኢህአዲግ መንግስት የመንግስት የልማት ድርጅቶች ለኢትዬጵያ አየር መንገድ ድርጅት፣ ለኢትዬቴሌኮምና የኢትዬጵያ ኤሌትሪክ ኃይል እዳ የኢትዬጵያ መንግስት እዳ እንዳልሆነና  በብድሩም መንግስት ተጠያቂም እንዳአይደለ ለዓለምአቀፍ የገንዘብ ተቆም ማረጋገጡን በማስረጃ ቀርባል፡፡ ዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቆም (ኤይኤምኤፍ)ና የኢትዩጵያ መንግስት በጥቅምት 2014እኤአ የአንቀፅ አራት የምክክር አቅጣጫ (IMF Country Report No. 14/303, THE FEDERAL DEMOCRATIC REPUBLIC OF ETHIOPIA 2014 ARTICLE IV CONSULTATION) ያወጣውን ሪፖርት ከድረ-ገፁ መመልከት አስፈላጊ ነው፡፡

በቻይና በ3.4 ቢሊዩን ዶላር ብድር የተገነባው የኤሌትሪክ ባቡር

በቻይና የሬል ዌይ ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽንና ቻይና ሲቨል ኢንጅነሪንግኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን በአራት ቢሊዩን ዶላር ብድር እየተገነባ ያለው 758 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው፣ የሰውና ዕቃ ማጎጎዣ የኤሌትሪክ ባቡር አዲስአበባ ከተማን ከጅቡቲ ጋር ያገናኛል፡፡ በአንድ ግዜ 2760 ሰዎችን ጭኖ በሰዓት 120 ኪሎ ሜትር እንዲሁም 3500 ቶን ሸቀጥ በመጫን በሰዓት 80 ኪሎ ሜትር የመጎዝ አቅም እንዳለው መስከረም 26 ቀን 2009ዓ/ም አዲስ ዘመን ጋዜጣ ዘግቦል፡፡ 

የኢንዱስትሪ ዞን ለማስፋፋት ተመራጭ የሆነችው የደቡብ ክልል መቀመጫ ሐዋሳ ከፍጥነት መንገድ በተጨማሪ የባቡር መስመር እንዲኖራት ተፈልጓል፡፡ ለዚህ ፕሮጀክት የቻይና መንግሥት ፋይናንስ ለማቅረብ መስማማቱ ተገልጿል፡፡ በአጠቃላይ የቻይና መንግሥት ፍላጎት ያሳየባቸውን ፕሮጀክቶች በቀጣይ ጊዜያት በዝርዝር ጉዳዮች ላይ ድርድር እየተካሄደ ተግባራዊ እንደሚደረግ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

የኢትዩጵያ አየር መንገድ ባለ አራት ኮኮብ ሆቴል ግንባታ በ65 ሚሊዩን ዶላር ወጭ በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት በሚገኝ 40,000 ካሬ ሜትር ላይ አራት የተለያዩ ምግብ ቤቶች፣ሁለት መጠጥ ቤቶች፣370 የመኝታ ክፍሎች፣ሁለት መዋኛ ገንዳዎች፣ጂምናዚም፣ስጦታ መሸጫ ሱቆች፣2,000 ሰዎች የሚያስተናግድ የመሰብሰቢያ አዳራሰሾች፣3 አነስተኛ አዳራሾች ያሉት ሆቴል በማስገንባት ላይ ይገኛል፡፡ ግንባታውን የሚያካሂደው አቪክ የተሰኘ የቻይና ኩባንያ ነው፡፡

ምሥራቃዊ ኢንደስትሪያል ዞን/Eastern Industrial Zone (EIZ)) የተለዩ የኢኮኖሚ ዞኖች/ (Special Economic Zones) የተለዩ የኢኮኖሚ ዞኖች( Special Economic Zones) ምሥራቃዊ ኢንደስትሪያል ዞን (Eastern Industrial Zone (EIZ)) ወይም ኢንደስትሪያል ፓርክ በኢትዬጵያ ከአዲስአበባ ስሜን ምስራቅ 37 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው በዱከም ከተማ ተገንብቶ ይገኛል፡፡ በዱከም በ200 ሄክታር ላይ የተገነባው ምሥራቃዊ ኢንደስትሪያል ዞን በአይነቱ የተለየ የቻይና ኢንቨስትመንት ከፍተኛውን የመሬት ቅርምት ከህወሓት የጦር አበጋዞች ጋር በመሆን የሚፈፅሙ የንግድ ካንፓኒዎች ናቸው፡፡

በ2007 እኤአ የንጋንግ ግሩፕና( Yonggang Group) ኪያኦን ግጉፕ( Qiyuan Group) የሆኑት በዛንግጃአጋንግ ከተማ የሚገኑት ሁለቱ የብረት ፋብሪካዎች በቻይና የንግድ ሚኒስትር የወጣውን ጫረታ በማሸነፍ ሥራ ጀመሩ፡፡ በኢትዬጵያ ይህ የተለየ የኢኮኖሚ ዞኖች ምስረታ የመጀመሪያውና ትልቁ ኢንደስትሪያል ፓርክ በሃገሪቱ ለመሆን በቅቶል፡፡ የኢትዬጵያ መንግስት ይህን ፕሮጀክት ከዘለቄታ የኢኮኖሚ እድገትና ከድህነት ቅነሳ ጋር በማዛመድ የኢንደስትሪያል ዘርፍን ለማሳደግ አቅዶል፡፡ ኢትዬጵያ መንግስት ኢንደስትሪ ሚኒስትር የኢኮኖሚ ዞኑ ውስጥ የጨርቃ ጨርቅና የልብስ፣የህንፃ መሣሪያዎች ዕቃ ማምረቻ፣የማኒፋክቸሪንግና የግብርና ምርት ማቀነባበሪያ አገልግሎት እንዲስፋፉ ይፈልጋሉ፡፡ በአሁኑ ግዜ 11 የቻይና ካንፓኒዎች በኢንደስትሪያል ፓርክ ለመስራት ፊርማቸውን አኑረዋል፡፡

ሁጃአን( Huajian) የቻይና የጫማ ፋብሪካ የባህር ማዶ ገበያ ኢንቨስተር በኢትዬጵያ ውስጥ 20 ሚሊዩን ጥንድ ጫማዎች በአመት ወይም ሁለት ሽህ ጥንድ ጫማዎች በቀን በማምረት ላይ ይገኛል፡፡ የጫማ ፋብሪካው በስመ ጥሩ ንግድ ምልክት ብራንድ ስም በማምረት በዓለም ዓቀፍ ንግድ በመሰማራት ለአሜሪካና አውሮፓ በማቅረብ ላይ ይገኛል፡፡ በአሁኑ ግዜ 1600 ሠራተኞች ያሉት ሲሆን አብዛኛዎቹ ኢትዬጵያዊ እንደሆኑ ይታወቃል፡፡ የሁጃአን ማኒፋክቸሪንግ በኢትዬጵያ ውስጥ ርካሽ የሠራተኛ ጉልበት ዋጋ፣ በርካሽ ዋጋ ሰፊ የቆዳ አቅርቦት አግኝቶል፡፡ ፋብሪካው ሰፊ የግንባታ ቦታ፣የተሞላ የኤሌትሪክና ውኃ አቅርቦት፣ የመንገድ መሰረተልማትና የታክስ እፎይታና ከውጭ ለሚገቡ እቃዎች/ማሽነሪዎች ወዘተ ከቀረጥ ነፃ ፖሊሲ በማግኘት ምርቶቹን ወደ አሜሪካና አውሮፓ ገበያ በማቅረብ ከፍተኛ ትርፍ አግኝተዋል፡፡ የሁጃአን የቻይና የጫማ ፋብሪካ ሁሉንም ምርቶች ለባህር ማዶ ገበያ በማቅረብ በ2011 እኤአ 250 ሚሊዬን ብር (12 ሚሊዩን ዶላር በአመት)ገቢ አግኝቶል፡፡

አዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ፣ የቻይና ኤግዚም ባንክ ለአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ አንድ ቢዩን ዶላር ብድር ለማቅረብ ተስማምቶል፡፡ባንኩ በኢትዩጵያና በቻይናዋ ሁናን ግዛት መንግስት አማካይነት ለሚገነባው የኢትዩ-ሁናን ኢንዱስትሪ ፓርክ የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች ማምረቻ ኢንዱስትሪ ፓርክ አው፡፡ ስምምነቱ ከቲቢያን ኤሌትሪክ አፓራተስ ስቶክ(ቲቢኢኤ ትራንስፎርመር ግሩፕ) እንዲሁም ሳኒ ግሩፕ ከተባሉ ሁለት ትልልቅ የቻይና ኩባንያዎች ጋር ዶ/ር አርከበ እቁባይ ተስማምተዋል፡፡ ለአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ ግንባታ ቦታ ከ300 ሄክታር መሬት በላይ መዘጋጀቱን ከዚሁ ውስጥ  የተለያዩ የቻይና ኩባንያዎች መሀከል፣ ስንሻይን ግሩፕ ኩባንያ 80 ሄክታር፣ ኪንግደም ኩባንያ 30 ሄክታር፣የደቡብ ኮርያው ግዙፍ የጨርቃ ጨርቅ አምራች ያንግዋን ኮርፖሬሽን 200 ሄክታር መሬት ላይ የሚንጣለል የማምረቻ ግንባታ እንደሚኖራቸው ዶ/ር አርከበ እቁባይና የኢትጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽነር አቶ ፍፁም አረጋ  ለጋዜጠኞች አረጋግጠዋል፡፡ ለፓርኮቹ ግንባታ ከመንግስት ካዝና፣ ከዓለም ባንክ ብድር፣ እንዲሁም ከዩሮ ቦንድ ሽያጭ በተገኘ ከ1.5 ቢሊዩን ዶላር በላይ ገንዘብ የመገንቢያ ወጪ ጠይቆል፡፡ መንግስት በአንድ ኢንደስትሪ ፓርክ ግንባታ በአማካይ ከ100 እስከ 150 ሚሊዩን ዶላር እንደሚያወጣና አንድ ፓርክ 75 ሄክታር እስከ 2000 ሄክታር    በድሬዳዋ የሚገነባው የኢንዱስትሪ ፓርክ የመሬት ስፍት ሊኖረው ይችላል፡፡  በመላ ሃገሪቱ የሚገነቡ ከ10 በላይ የኢንዱስትሪ ፓርኮች የገበሬውን መሬት የተቀራመቱ በመሆናቸውና ገበሬውን የጥቅሙ ተካፋይ ያላደረጉ በመሆናቸው እንዲሁም በጉልበት ህብረተሰቡን ያላማከረ የመሬት ዘረፋና ነጠቃ በመሆኑ በህዝቡ ድጋፍ አላገኘም፡፡

ኃጀዬን ኢንዱስትሪ ፓርክ፣ የቻይናው ግዙፍ ኩባንያ ኃጀዬን ግሮፕ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ጀሞ አካባቢ በ164 ሁክትር መሬት ላይ ዘመናዊ የሌዘር ኢንዱስትሪ ፓርክ በመገንባት ላይ ይገኛል፡፡ በዚህ ፓርክ ውስጥ ከጫማ ፋብሪካዎች በተጨማሪ የቴክኒክና ሙያ ዩኒቨርሲቲ፣የሠራተኞች መኖሪያ፣የንግድ አገልግሎት መስጫ ተቆማት፣ አረነረጎዴ ሥፍራዎች ግንባታ ያካተተ መሆኑን በሚያዝያ 2007 ዓ/ም የመሠረት ድንጋይ በተቀመጠበት ወቅት ተገላፆል፡፡የፓርኩ ግንባታ ሲጠናቀቅ 30 ሽህ ሰዎች የስራ እድል እንደሚፈጥርና ሁለት ቢሊዩን ዶላር የውጭ ምንዛሪ እንደሚያስገኝ በወቅቱ ተገልጾል፡፡ ፓርኩ ይህን ያህል የስራ እድልና የውጭ ምንዛሪ ማስገኘቱን ኢንቨስትመንት ጥናቱ ለምሁራን ይፋ አልተደረገም፡፡ ብዙ ግዜ ያለ በቂ ጥናቶች የመሬት ቅርምት ለማድረግ ተጋነነ ምናባዊ አሃዞች በማስቀመጥ ህብረተሰቡን የሚያፈንቅል የመሬት ነጠቃ በመካሄዱ የተነሳ በህዝቡ ተቀባይነት አላገኘም፡፡  በዚህም የተነሳ ሰው ሰው ያልሸተተው ልማት፣ መሬታቸውን በግፍ የተነጠቁ አርሶ አደሮች ሊሰጣቸው የታቀደው ተለዋጭ ቦታ ለኑሮ ምቹ ባለመሆኑ እንደማረከቡ አስታውቀዋል፡፡  

ቦሌ ለሚ ኢንደስትሪያል ዞን በአዲስ አበባ ከተማ በቦሌ ለሚ ለደቡብ ኮሪያ ኢንቨስተሮች የሚገነባው ኢንደስትሪያል ዞን 633 ሚሊዩን ብር የግንባታ ወጪ እንዳለው የኢንደስትሪ ሚኒስቴር ለ13 የአገር ውስጥ ኮንትራክተሮች ስራውን ሰጥተዋል፡፡ ፋብሪካዎቹ የሚገነቡት በ156 ሄክታር መሬት ላይ  እንደሆነ ይታወቃል፡፡ የደቡብ ኮሪያ ኢንቨስተሮች ስምንት ካንፓኒዎች በጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ኢንደስትሪያል ዘርፍ እንደሚሳተፉ ተገልፆል፡፡

የቻይና መንግስት፣የቻይና መንግስት የልማት ድርጅቶች በሃገር ውስጥና በባህር ሞዶ አገራቶች የኢንቨስትመንት ፍስት 55 በመቶ መሆኑ ጥናቶች ያረጋግጣሉ፡፡ ከዚህ ውስጥ በአፍሪካ በተለይ በደቡብ ሱዳን በ29 ቢሊዩን ዶላር ኢንቨስትመንት ብድር ቤንዚን በማውጣት ወደ ቻይና የቤንዚን ምርቱን በመጫን ላይ ይገኛሉ፡፡ በደቡብ ሱዳን መንግስት በሁለቱ ተቀናቃኞች በተነሳ ጦርነት የቻይና መንግስት የቤንዚን ኃብት ዝርፍያ እንዳይስተጎጎልበት 10000 የቻይና ወታደሮቾን በደቡብ ሱዳን በማስፈር እስካሁን የነዳጁን ኃብት በመዛቅ ላይ ይገኛሉ፡፡ ከዚህ በመነሳት የቻይና መንግስት በኢትጵያ የሚያከናውነው የኢንቨስትመንት ፍስትና ለኢትጵያ መንግስት እስካሁን 17.5 ቢሊዩን ብድር ማበደርና ጥቅማቸውን ለማስከበር ለህወሓት የጦር አበጋዞች መንግስት ከስልጣን መንበሩ እንዳይወድቅ ለማድረግ የኢንተርኔት ግንኙነቶችን በመፈን፣ መረጃ በመሥጠት በህዝባዊው ትግል ላይ እንቅፋት በመፍጠር ላይ እንደሚገኙ ሁሉም ተቃዋሚ ኃይሎች መገንዘብ ይኖርባቸዋል፡፡ የቻይና ባለኃብቶች በአጭር ግዜ  ውስጥ የኢትዩጵያን ኢኮኖሚ ከህወሓት የፓርቲ ንብረት ከሆኑት ኢፈርትና ሜቴክ ጋር በሽርክና በመስራት የሃገሪቱን ሃብት በመቆጣጠርና መሬት በመቀራመት ሥራ ላይ ይገኛሉ፡፡ የህወሓት የሜድሮክና የቻይና ባለሃብቶች በሽርክና የሃገሪቱን ሃብት በመቆጣጠር ላይ ይገኛሉ፡፡ በአገር ቤት ህዝባዊ እንቢተኝነት በነዚህ የቻይና ኢንቨስትመንቶች ላይ አንዳችም ጉዳት አልደረሰም፡፡  በውጭ  ሃገራት የሚገኙ ኢትዩጵያዊያን በቻይና ኢንባሲዎች ሁሉ ተቃውሞቸውን በቻይና መንግስት ላይ ማድረግና ለዓለም ህብረተሰብ ማሳወቅ ወቅታዊና አንገብጋቢ ጉዳይ ነው፡፡

(የቻይና የመንገድና ድልድይ ኮንስትራክሽን) አዲስ ኢንጂነሪንግ ኃ/የ/ካንፓኒ፣የቻይና መንግስት የኮንስትራክሽን ካንፓኒ ሲሆን በ1998እኤአ ኢትዩጵያ የአዲስአበባ ቀለበት መንገድ ለመስራት ገብቶ ውሎ ሲያድር በ20005 እኤአ ደረጃ አንድ የመንገድ ኮንስትራክሽን ተቆራጭ ፍቃድ በማውጣትና በመጫርት 160 ሚሊዩን ዶላር የመንገድ ሥራ እስከ 2004 እኤአ ያገኘ የቻይና መንግስታዊ ድርጅት ነው፡፡ 

CRBC (China Road and Bridge Construction) Addis Engineering PLC is a Chinese Government construction firm  which came to Ethiopia in 1998 to construct the Addis Ababa ring road. It was previously engaged in Ethiopia as a Chinese foreign contractor, but re-established as a Grade 1 GC local company in 2005 in order to compete in road tenders, which is possible for local contractors only. CRBC has been very successful in winning and implementing government road contracts on time and has undertaken more than $160 million worth of road projects in Ethiopia since 2004.

  • የቻይና የሕንፃ ኮንስትራክሽን ተቆራጮች በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በሰንጋ ተራ አካባቢ ወጋገን ባንክ ህንፃን በግምት በአንድ ቢሊዩን ብር በመገንባት ላይ ይገኛሉ፡፡
  • የቻይና የሕንፃ ኮንስትራክሽን ተቆራጮች በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በሰንጋ ተራ አካባቢ የሕብረት ባንክ ሠላሳ ሁለት ወለል ያለውን ህንፃ በግምት በአንድ ቢሊዩን ብር በመገንባት ላይ ይገኛሉ፡፡
  • የቻይና የሕንፃ ኮንስትራክሽን ተቆራጮች በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በሰንጋ ተራ አካባቢ ለኢትዩጵያ ንግድ ባንክ ህንፃን በግምት በአንድ ቢሊዩን ብር በላይ በመገንባት ላይ ይገኛሉ፡፡
  • የጣሊያኑ ቫርኔሮ የሕንፃ ኮንስትራክሽን ተቆራጮች በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በሰንጋ ተራ አካባቢ የአዋሽ ባንክ ህንፃን በግምት በአንድ ቢሊዩን ብር በመገንባት ላይ ይገኛሉ፡፡

የሙስናና የሌቦች ሃብትና ፎቆች ተወርሰው እዳችን ይከፈል፣ ከሳውዲ አረቢያ የሙስኛዎችን ኃብት ማምከን ተማሩ!!! 

ሙስናና ሌብነትን ለመዋጋት፣ የፕሬስ ነፃነት!!!

ዘራፊዎቹ የወያኔ ኢፈርትና ሜቴክ ድርጅቶች ንብረቶች መጀመሪያ በአክሲዮን ለህዝብ ይሸጡ!!!