በምእራብ አውስትራሊያ፣ የፐርዝ ኗሪ ኢትዮጵያውያን የነፃነት ታጋዩ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌና ሌሎችም ከእስር በመፈታታቸው የተሰማቸውን ደስታ በዝግጅታቸው ላይ ገለጹ

0

%e1%8a%a0%e1%8a%95%e1%8b%b2-700

ብዙ ሚሊዮን ዶላር ለየመን የጸጥታ ሃይሎች ከስክሶና የዓለም አቀፍ ሕግጋትን ጥሶ ከየመን መንግሥት ጋር በማበር አቶ አንድአርጋቸው ጽጌን አግቶ፣ ሌሎች የነጻነት ታጋዮችን ደግሞ በፈጠራ ወንጄል በእየእስር ቤቱ ይህ ነው በማይባል ስቃይ ውስጥ አቆይቶ፣ በኢትዮጵያ ሕዝብ ያላሰለሰና እልክ አስጨራሽ ትግል በርካታዎቹ በቅርብ መፈታታቸው ይታወሳል።

የነዚህ የነጻነት ቀንዲሎች ቀዳሚውና የታገሉለት ዓላማ ለኢትዮጵያና ለሕዝቧ ነጻነት፣ ፍትህና ብልጽግና የማምጣት ትግል ብቻ ነበር። ይሁንእና፣ በትእቢትና በድንቁርና የተተበተበው የአናሳው የኢትዮጵያ መንግሥት ኢህአዴግ በጥቅም በመታወሩ የንጹሃን ታጋዮች ድምጽ እንዳይሰማ በሰበብ አስባቡ በእስር አቆይቷቸዋል።  አሁንም በርካቶች በእየእስር ቤቶቹ እየማቀቁ ነው።

የኢትዮጵያ ሕዝብ ለጊዜው በአዲሱ አመራር ትንሽም ቢሆን የተስፋ ጭላንጭል ማየቱ የሚያበረታታ ቢሆንም፣ ትግሉ እዳር እስኪደርስ ድረስ ባለመዘናጋት ዓላማው ግቡን እስኪመታ ነቅቶ መጠባበቅና  ሃዲዱን እንዳይስት ማድረግ ይጠበቅበታል/ይጠበቅብናል።

እኛም በዚህ ታሪካዊ  ሊሆን  በሚችል ቀን ተሰባስበን የጀግኖቻችንን መፈታት አቶ አንድአርጋቸው ፅጌና ባለቤቱ በስካይፕ በታደሙበት በደስታ በምናከብርበት እለት፣ ትግሉ መስመር የያዘ ቢመስልም  የታቀደለት ውጤት ዘንድ ለመድረስ አሁንም ገና የቀረ ካባድ ትግል ስለአለ፣ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር በመሆን የበኩላችንን ማድረግ መቀጠል ይኖርብናል።

አቶ እንዳርጋቸው “እኔ ዓላማ አስፈጻሚ እንጂ ዓላማ አይደለሁም” እንደአሉት አስፈጻሚ መሆን ወይም አስፈጻሚዎችን ለመርዳት እንዲያበረታታን የአምላክ ፈቃድ እንዲሆን እንለምናለን።

በድጋሚ እንኳን ደስ ያለን።

ኢትዮጵያ ሳትፈርስ ለዘለዓለም ትኖራለች

ከአዘጋጅ ኮሚቴው