ከ60 በላይ ኢትዮጲያውያን ህይወት ማለፉ ተሰማ

0

አባይ ሚዲያ ዜና
አቢሰሎም ፍሰሃ

ከሶማሌ ቦሳሳ ወደብ በመነሳት ቀይ ባህርን አቋርጠው በጦርነት እየታመሰች ያለችውን የመን ተሻግረው መዳረሻቸውን ሳውዲ አረቢያ አድርገው በማሰብ ስደት የጀመሩ ወጣት ኢትዮጵያውያን የተሳፈሩባት ጀልባ ተገልብጣ ከተሳፋሪዎቹ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት መሞታቸው ተሰማ።

በጀልባዋ ላይ የተጫኑት 100 ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ 83 ወንዶች እና 17 ሴቶች እንደነበሩ የታወቀ ሲሆን ከ50 በላይ ወንዶች እና ከ10 በላይ ሴቶች በአደጋው ህይወታቸው ማለፉ ተነገረ።

ይህ ዜና እስከተዘገበበት ሰዓት ድረስ ከሞቱት ውስጥ 46 አስከሬን ብቻ ሲገኝ የ16ቱ አስከሬናቸው እንዳልተገኘ ታውቋል።

የአለም የስራ እንቅስቃሴና ድንገተኛ አደጋዎች ዳይሬክተር የሆኑት መሐመድ አብዲከር አደጋውን አሳዛኝ እና አሳፋሪ ነው በማለት ይህንን አደገኛ ጉዞ በየወሩ ከ 7000 የሚበልጡ ደሃ ነዋሪዎች ያደርጋሉ፤ እንዲያውም ባለፈው አመት ብቻ 100 000 የሚሆኑት ስደተኞች ይህን ጉዞ በአስጨናቂና አደገኛ ሁኔታ አድርገውታል ብለዋል።