ሐረር:- ታሪክ መስረቅ እንጂ፣ ታሪክ መስራት የማያውቀው የ ሐረሪ ብሄራዊ ሊግ (ሐብሊ) የነገሰባት ከተማ (በኤድመን ተስፋዬ)

0

ሐረር:-  ታሪክ መስረቅ እንጂ፣ ታሪክ መስራት የማያውቀው ሐረሪ  ብሄራዊ   ሊግ (ሐብሊ)  የነገሰባት ከተማ።

ክፍል አንድ

ኤድመን ተስፋዬ

ሀረር በምስራቁ የሀገራችን ክፍል ከሚገኙ ጥንታዊ ከተሞች መሀል ላቅ ያለ እድሜ ያላት ከተማ ነች፡፡ .. 2007 በተካሄደው ሀገር አቀፍ የህዝብ ቆጠራ መሰረት የሀረር ህዝብ ብዛት 183,415 ነው፡፡ ህወሀትኢህአዴግ በምን መሰረት እንዳዋቀራቸው  በከማይታወቁት ክልሎች በተለየ መልኩ የሀረር ከተማ ብዙሀኑ ህዝብ በከተማ የሚኖርባት ከተማ ነች፡፡ .. 2007 በተካሄደው አጠቃላይ የህዝብ ቆጠራ መሰረት ከአጠቃላዩ የሀረር ህዘዝብ ውስጥ 56.41 ፐርሰንቱ ኦሮሞ  ፣ እንዲሁም 22.77 ፐርሰንቱ አማራ፣8.65 ፐርሰንቱ ሀረሪ (በቀድሞ አጠራሩ አደሬ) 4.34 ፐርሰንት ጉራጌ፣3.87 ፐርሰንት ሱማሌ፣1.53 ፐርሰንቱ ትግሬ እንዲሁም 1.26 ፐርሰንቱ የአርጎባ ብሄር ተወላጅ ነው፡፡  በሀረር ከተማ ህዝቦች የሚነገርን ቋንቋ በተመለከተ፣ .. 2007 የተካሄደው የህዝብ ቆጠራ እንደ ሚያሳየን ከሆነ  56.84 ፐርሰንት የሚሆነው የሀረር ህዝብ ኦሮምኛ ተናጋሪ ሲሆን፣ 27.53 ደግሞ አማርኛ ተናጋሪ ነው፡፡ የሀረሪ ቋንቋ ተናጋሪው ደሞ ከአጠቃላይ የሃረር ህዝብ 7.33 ፐርሰንቱን ይይዛል።  ከሀረር የአጠቃላይ ህዝብ ውስጥ 68.99 የእስልምና እምነት ተከታይ ሲሆን፣27.1 ፐርሰንቱ የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታይ ነው፣ በተጨማሪም 3.4 ፐርሰንት የሚሆነው የሀረር ህዝብ ፕሮቴስታንቴ 0.3 ፐርሰንቱ የካቶሊክ፣ እንዲሁም የተቀረው 0.2 ፐርሰንቱ ደግሞ የባህላዊ እምነት ተከታዮች ናቸው፡፡

መስፈርቱ ምን እንደሆነ ለብዙሀኑ ግልፅ ባልሆነ ምክንያት ህወሀትኢህአዴግ ሀረርን እንዲያስተደዳር ለሀረሪ ህዝብ ሀላፊነቱን ከሰጠ ጀምሮ ሀረርን በማስተዳደር ላይ የሚገኘው ሀብሊ ነው፡፡ የሲዳማ ብሄርን የመሳሰሉ ብሄሮች ለብቻችን ክልል የሰጠን ሲሉ ከህወሀት ኢህአዴግ የሚሰጠውን መምላሽ ላስተዋለ የሀረር ህዝብ በሀብሊ የበላየረነት መተዳደሩ ላይ ጥያቄ ቢያነሳ አይገርምም፡፡ የሀረሪ ብሄራዊ ሊግ (ሀብሊ) ጥንታዊታን ሀረር ከተማን ማስተዳደደር ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ከተማዋ ከማደግ ይልቅ ባለችበት እንደቆመች፣ ነዋሪዎቿ ሀብሊ በፈጠረው የዘረኝነት ጦስ እየተለበለቡ ይገኛሉ፡፡

ላለፉት ሃያ ሰባት አመታት ሃረርን ሀሪሪ ብሄራዊ ሊግ (ሀብሊ) በዋነኛነት እንዲሁም የ ኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) በስልጣን ተጋሪነት ሲያስተዳድሩ ቆይተዋል። በህወሃት – ኢህአዴግ የፌደራል መዋቅር  ስር ሃረርን የሚያስተዳድረው ሀብሊ የልዩ ጥቅም ባለቤት ነው። በየአምስት አመቱ በሚካሄደው የብሄራዊ ምርጫ ከአጠቃላይ አስራ ዘጠኙ የሃረር ቀበሌዎች መሃል ሰባቱ ቀበሌዎች በሚገኙበት እና የተለያዩ (እንደ ኦሮም፣አማራ፣ጉራጌ ወዘተ)ብሄር ብሄረሰቦች በሚኖሩበት ጀጎል  አካባቢ የሀሪሪ ብሄራዊ ሊግ (ሀብሊ) በብቸኝነት የሚወዳደር መሆኑ፣ ከክልሉ ውጪ የሚኖሩ የሃረሪ ብሄር ነዋሪዎች ባሉበት ቦታ ሆነው የሀሪሪ ብሄራዊ ሊግ (ሀብሊ)ን መምረጥ የሚያስችላቸው ስርአት መዘርጋቱ (በየ አምስት አመቱ በሚካሄደው ምርጫ በአዲስ አበባ የሚኖሩ የሃረሪ ብሄር ተወላጆች ከ አዲስ አበባ አምስት መቶ ሃያ ስድስት ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ለሚወዳደረው ሀሪሪ ብሄራዊ ሊግ (ሀብሊ) ድምጣቸውን የሚሰጡበት አሰራር መኖሩ ጸሃይ የሞቀው እውነት ነው)፣ ከክልሉ ምክር ቤተ አጠቃላይ ሰላሳ ስድስት ወንበር ውስጥ አስራ ስድስቱ ለሃረሪ ብሄር ብቻ የሚሰጥ መሆኑ ወዘተ የብዙ ብሄር ብሄረሰቦች መኖሪያ የሆነችውን ሃረርን እንዲያስተዳድር በ ህወሃት- ኢህአዴግ አረንጋዴ መብራት የበራለት የሀሪሪ ብሄራዊ ሊግ (ሀብሊ)  የተጎናጸፈው ልዩ ጥቅም ነው።

እንግዲህ ከላይ የተጠቀሱትን ልዩ ጥቅሞች በመያዝ ነው  የሃረሪ ብሄራዊ ሊግ (ሃብሊ) የብዙ ዘውግ፣ በተለይም የቅይጥ ዘውጎች መኖሪያ የሆነችውን ሃረርን እያስተዳደረ የሚገኘው። እኔም ሃረር፦ ታሪክ መስረቅ እንጂ፣ ታሪክ መስራት የማያውቀው ሐረሪ ብሄራዊ   ሊግ (ሐብሊ) ላለፉት ሃያ ሰባት አመታት የነገሰባት ከተማ የሚል ርእስ በሰጠውት ተከታታይ ጽሁፌ በዘመነ ሃብሊ በሃረር ህዝብ ላይ በተለይም በወጣቱ ላይ የደረሰውን ማህበራዊ፣ፓለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች በማሳየት፣ የክልሉን ችግር ለመቅረፍ መፍትሄ የምላቸውን የመፍትሄ ሃሳቦችን ለማመላከት እሞክራለው

የእስልምና ትምህርት አስተምህሮቶች  በቃልም ሆን በጽሁፍ እሳን ማአከል አድርገው ወደ ሌሎች የሃገራችን ከተሞች የተስፋፉባት ፣ በእምዬ ምንይልክ ዘመነ መንግስት በሃገራችን ታሪክ የመጀመሪያ በሆነው የስልክ መስመር ከአዲስ አበባ ጋር የተገናኘችው፣ ወጣቱ ተፈሪ መኮንን ዘመናዊ ትምህርትንም ሆን ህዝብን ማስተዳደር ሀ ብሎ የጀመረባት፣ በሃገራችን ታሪክ የመጀመሪያው ዘመናዊ በጦር አካዳሚ ትምህርት ቤት በቀዳማዊ ሃየለ ሰላሴ ዘመነ መንግስት  የተከፈተባት፣ ንጉሰ ነገስቱን ከስልጣን አውርዶ በሃላም እራሱን ደርግ ብሎ ሰይሞ ሃገራችንን ለ አስራ ሰባት አመታት በወታደራዊ አገዛዘ ጠርንፎ የገዛው ደርግ ስብስቡን የፈጠረበትም ሆነ የመጀመሪያውን ስብሰባ ያደረገባት ሃረር፣ ዛሬ በዘረኛው ሀብሊ አገዛዝ የተነሳ፣ ሰዎች በማንነታቸው ብቻ ከፓለቲካዊም ሆነ ከኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ተገፍተው የሚኖሩባት ከተማ ሆናለች።

ሃረርን በበላይነተ ላለፉት ሃያ ሰባት አመታት ያስተዳደረው የ ሃረሪ ብሄራዊ ሊግ (ሀብሊ)  የሃሪሪ ብሄር ተወላጅ በሆኑ ግለሰቦች የተመሰረተ ድርጅት ነው። ከሃገራቸው ታሪክ ይልቅ ለባእዳን ሃገር ታሪክ ልባቸው ቅርብ በሆኑ እና አንድን የህብረተሰብ ክፍል በተለየ በሚጠሉ  ግለሰቦች በዋነኛነት የሚመራው ሃብሊ በዋነኝነት የድጋፍ ማእከሉ የብሄሩ ተወላጆች (በክልሉ የተንሰራፋው የሃረሪ ብሄር ብቻ ተጠቃሚነት ለ ሃረሪ ብሄር አደጋ ስለመሆኑ እና የሀብሊን አካሄድ የሚነቅፉ ጥቂት የሃረሪ ብሄር ተወላጆች እንዳሉ ሆነው)  እና ህወሃት እንደሆኑ ይታመናል።

 

ከሃረር አጠቃላይ ህዝብ ብዛት ውስጥ  8.65 ፐርሰንት የሚወክለውን የህብረተሰብ ክፍል የሚወክለው የ ሃረሪ ብሄራዊ ሊግ (ሀብሊ) ላለፉት ሃያ ሰባት አመታት በአንጻራዊነት የሀረሪን ብሄር ተጠቃሚነት ብቻ መሰረት ያደረጉ አስተዳደራዊ መዋቅሮችን ዘርግቶ ብዙሃኑን በተለይም አማርኛ ተናጋሪውንና ቅይጥ (ከሁለት ብሄር የሚወለደውን ) የሆነውን የህብረተሰብ ክፍል ያገለለ የዘረኝነት አገዛዝ በጥንታዊ ሃረር ከተማ ላይ አስፍኖ ይገኛል። በሃረር ከተማ ከሚገኙ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች መሃል በአንጻራዊነት የሃረሪን ብሄር  ተጠቃሚ የሚያደርጉት አስተዳደራዊ መዋቅሮች ደሞ በዋነኛነት ከማህበራዊ ዋስትና፣ ከመሬት ጉዳዮች ፣ክፍትህ እና ጸጥታ፣ከመንግስት ንብረቶች ፣ ከ መንግስታዊ ገቢ እና ወጪ፣ እንዲሁም ከአመታዊው የክልሉ መንግስት እቅድ ጋር የተሰላሰሉ ናቸው።

 

በእኔ እምነት አንድ ግለሰብም ሆነ የግለሰቦች ስብስብ የሆነው ስርአትም ሆነ ቡድን እራሱ እንደ ግለሰብም ሆን እንደ ቡድን በጊዜው ለሰራው በጎም ሆነ መጥፎ ታሪክ ሙገሳውም ሆነ ወቀሳው የታሪክ ሰሪው ነው። ባለፉት ሃያ ሰባት አመታት በሃረር ከታዩት የሀብሊ ነውረኛ  የዘረኘነት አገዛዝ መሃል አንዱ ታሪክ ከመስራት ይልቅ ታሪክን ከመስረቅ ጋር የተያያዘ ነው።

 

በሃረር ከተማ በሀብሊ ከተፈጸሙት የታሪክ ስርቆቶች መሃል፣ ለከተማዋ እና ለአካባቢው ነዋሪዎች መሰብሰቢያ ይሆናል ተብሎ በቀዳማዊ ሃይለስላሴ ዘመነ መንግስት የተሰራውን የህዝብ መሰብሰቢያ አዳራሽ፣ አዳራሹን ሰርቶ ለህዝብ አገልግሎት ያዋለውን የጊዚው አስተዳደር ለአዳራሹ ያወጣለትን ራስ መኮንን አዳራሽ የሚለውን መጠሪያውን ወደ አሚር አብዱላሂ አዳራሽነት መቀየሩ (ንጉሱን ከስልጣን ያወረደው ደርግ እንካን የአዳራሹን ታሪካዊ ስም ጠብቆ ቆይታል)፣ በቀዳማዊ ሃይለስላሴ ዘመነ መንግስት የተሰራውን እና ቀሃስ የሚል መጠሪያ የተሰጠውን ት/ም ቤት አቦከር መሰናዶ ት/ቤት በሚል ስም መቀየሩ፣ በ ዘመነ ደርግ ከህዝብ በተሰበሰብ ብር ተሰርቶ ሃረር አዲሱ እስታዲየም በሚል መጠሪያ ይታወቅ የነበረውን እስታዲየም አሚር ሃቦባ በሚል ስም መቀየሩ  ይጠቀሳሉ።

 

የብዙሃኑ ህብረተሰብ አስተዳደር፣ የአናሳውን መብት ባስጠበቀ መልኩ የሚለው ህልዮት ዋነኛው የዲሞክራሲያዊ ስርአት ማቀንቀኛ ነው። ይህ የዲሞክራሲያዊ ስርአት በዋነኛነት የአናሳዎችን (አንጻራዊ በሆነ የ ቁጥር ልዩነት ስሌት) መብት ባስጠበቀ መልኩ የብዙሃኑን ፍላጎት ወድ አስተዳደር የሚያመጣ ነው። ይህ አይነቱ ስርአት ትልቁ ጥቅሙ በአንድ ሉአላዊ ሃገር የሚኖሩ የተለያዩ አንጻራዊ የቁጥር ልዩነት ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ከጋራ ሃገራቸው ሃብት ፍትሃዊ ተጠቃሚነት እንዲኖራቸው ማድረጉ ነው። በተቃራኒው  ውስን በሆነ ሃገራዊ ሃብት በሚገኝበት ሉአላዊ ሃገር ላይ በዋነኛነት የአናሳ ህብረተሰብ ክፍሎችን (አንጻራዊ በሆነ የ ቁጥር ልዩነት) መብት እና ጥቅም ብቻ ለማስጠበቅ ሲባል ብቻ የብዙሃኑን ፍላጎት የሚገፋ ስርአት ውጤቱ የብዙሃኑን ህብረተስብ የገፋውን አካል እንደ ማህበረሰብ የወደፊት ህልውና አደጋ ላይ እስከመጣል እንደሚደርስ የሃገራት ታሪክ ይነግረናል።

 

በእኔ እምነት ከሃያ ሰባት የ ሀብሊ የዘረኝነት አገዛዝ በኋላ አሁን ላይ በሀረር ያለውን ማህበረሰብ ያየን እንደሆነ አንጻራዊ በሆነ የ ቁጥር ልዩነት ስሌት አናሳ የሆነውን የሃረሪ ብሄር የበላይነት  ጥቅም ለማስጠበቅ ሲባል ለሚዘረጋ አስተዳደር አደጋ ተብሎ በማንነቱ ብቻ የተገፋ እና አስተዳደራዊ ብልግና የተፈጠመበት ብዙሃኑን የህብረተሰብ ክፍል እና አንጻራዊ በሆነ የ ቁጥር ልዩነት ስሌት አናሳ የሆነውን የሃረሪ ብሄር የበላይነትን ጥቅም ለማስጠበቅ  ሲባል በተዘረጋ አስተዳደር ተወልዶ ያደገን ወጣት የህብረተሰብ ክፍል እናገኛለን። ይህ ወቅታዊው የ ሃረር አካባቢ ህብረተሰባዊ ሁነት ደሞ ፣በተለያዩ የሃገራችን ክፍል፣ በሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች ላይ፣ በተለይም በወጣቱ ትውልድ ላይ፣ ለደረሰው ማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊ እና ፓለቲካዊ ቀወሶች፣ በዋነኛነት መንስኤው የ ህወሃት-ኢህአዴግ ስርአት መሆኑን ባገናዘብ መልኩ፣ በሃረር የሚታየውን የሃረሪ ብሄር የበላይነት ለማስወገድ በወጣቱ ትውልድ ላይ  ማተኮርን የውዴታ ግዴታ ያደርገዋል። በተጨማሪም ትኩረታችንን በዋነኛነት በሀብሊ የዘረኝነት አገዛዝ የተነሳ የሀረር ወጣት ትውልድ የደረሰበትን ማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊ እና ፓለቲካዊ መድሎ በመዳሰስ እና ከሃገራዊው የወጣቱ ትውልድ ጥያቄዎች ጋር መግመድን እና ኢትዮጲያዊ መፍትሄን መፈለግን ማእከል ያደረገ እንዲሆን ይረዳዋል።

ይቀጥላል