ልጅ አለሺ አገሬ ( ቴድ አበጋዝ )

0

ሃያ ሰባት ዓመት በጣሊያን ቅጥረኛ
ወያኔ በሚባል ባንዳ ወንጀለኛ
ባንድራ ጨርቅ ነው የሚል ከዳተኛ
ሀገሩን የማይወድ መሰሪ ዘረኛ
 ሀገር ሲመዘብር አንድነትን ሲንድ
ህዝብን ሲከፋፍል በጎሳ በነገድ
ኢትዮጵያን ያለ ሰው ሲታሰር ሲዋረድ
 ንብረቱን ሲዘርፍ ከቃየው ሲሰደድ
 ጀግና እየታሰረ ሌባ እየነገሰ
አባት ያቆየውን ታሪክ እየጣሰ
ደምተው ያቆዩዋትን እያፈራረሰ
ኧረ ስንቱን በደል ባገሬ አደረሰ
ግና
ደም የቀሰቀሰው ያባቶቹ አደራ
ሀገሩን ወገኑን ሁሉንም ሊያኮራ
አድስ ትውልድ መጣ ስምሺን የሚያስጠራ
ቢከፋፍሉትም በዘር በሃይማኖት
ላይሳካላቸው አንገቱን ቢያስደፉት
እምቢ አለ ከማዶ ወገኑን ተጣራ
ጣና ኬኛ ብሎ ቄሮ ታሪክ ሰራ
አንድ! ነን አላቸው ከፋኖወቹ ጋራ
ኦሮሞና አማራን የሚለየው ማነው
እንደ ሰርገኛ ጤፍ የተወሐደ ነው
ጣሊያንን የቀጡት ድል የተቀዳጁት
በመተባበር ነው ሃገር የጠበቁት
ጅምራቸው ሰምሯል ደምህ ደሜ ያሉት
የዘረኝነትን ወጥመዱን ሊሰብሩት
መሪም ደገፋቸው መንገዱን ሲያሳዩት
ገዱም ታሪክ ሰርተህ ላገርህ ገድ ሆንክ
እነለማን ጋብዘህ መልካም መንገድ ጀመርክ
እውነትም ለማ አገርክን አለማህ
 ኢትዮጵያዊነትን ከፍ ከፍ አድርገህ
ከስልጣኔ በላይ አገር ይቅደም ብለህ
አብይ እንዲመራ ብዙ ዋጋ ከፍለህ
ለሀገር አንድነት ለሕዝብም ተስፋ ሆንህ
በርግጥ ደረሳችሁ አገርን ለማዳን
ጩኸቱን ሰማችሁ የፋኖን የቄሮን
 እስረኛም ፈታችሁ ሀገሬን ያለውን
ይቅር እንባባል ብላችሁ አንድ ነን
አይዟቹሁ በርቱ መልካም ጅማሮ ነው
ህዝብም ከጎናችሁ አለን እያለ ነው
 እግዜዓብሔርም ሀይሉ በናንተ ውስጥ ነው
ኢትዮጵያ ልጅ አላት ምንጊዜም አርግጥ ነው::