አባይ ሚዲያ
ሱራፌል አስራት
በጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ የሚመራው መንግስት በተለያዩ “ወንጀል” ተጠርጥረውና ፍርድ ተበይኖባቸው  የነበሩትን ከ300 በላይ የሚሆኑ እስረኞች መንግስት የኢድን በአል በማስመልከት ከእስር በምህረት እንዲለቀቁ አድርጓል።  

ከእስር ከተለቀቁትም መካከል ወደ ሶስት መቶ የሚሆኑት ታራሚወች በይቅርታ ሲለቀቁ ከእነዚህም መካከል አስራ ሁለቱ እስከ ሞት ፍርድ የተፈረደባቸው የነበሩ መሆናቸውን ጠቅላይ አቃቢ በመግለጫው አሳውቋል።  

ከእስር ከተፈቱት መካከል ከሰባሰባት በላይ የሚሆኑት በአርበኞች ግንቦት ሰባት ተጠርጥረው የታሰሩ እንደነበሩ ለማወቅ ተችሏል። ይህ በእንዲህ እንዳለ በአርበኞች ግንቦት ሰባት ተጠርጥረው ከእስር ከተፈቱት በአብዛኛው በአሁኑ ሰአት ከእስር ከተለቀቀው በአንተንህ ጌታቸው የእናቱ መኖሪያ ቤት ውስጥ እነደሚገኙ ለማረጋገጥ ተችልዋል።

12