አባይ ሚዲያ ዜና
ሱራፌል አስራት

በሀገራችን ኢትዮጵያ እየታየ የመጣው ለውጥ ለዘመናት ታፍኖ ለኖረው የኢትዮጵያ ህዝብ ትልቅ ተስፋ የሚሰጥ መሆኑን ብዙ ኢትዮጵያውያኖች እየተናገሩ ይገኛሉ። ይህንን ተስፋ ሰጭ የለውጥ ግስጋሴ በዘላቂነት ለማስቀጠል አብዛኛው የኢትዮጵያ ህዝብ ከጠቅላይ ሚ/ር አብይ አህመድ ጎን የተሰለፈ መሆኑኑን ብዙዎች ይናገራሉ። እንደብዙዎቹ ግምት ይህንን የለውጥ እንቅስቃሴ ለመግታት ሌት ከቀን የሚሰሩ እንደሚኖሩ ማህበረሰቡ በሰፊው ያምናል። እነዚህ የለውጥ ተቀናቃኞች ያላቸውን መዋቅር በመጠቀም በተለያዩ ክልሎች የእርስ በእርስ ግጭቶችን በመፍጠርና በማቀጣጠል ሀገሪቱን ወደ መጥፎ ሁኔታ ሊከቷት ይችላሉ የሚል ስጋት እንዳላቸው አባይ ሚዲያ ያነጋገራቸው በተለያዩ ክልሎች  የሚኖሩ ግለሰቦች ገለፀዋል።

በተለይ ሰሞኑን በደቡብ ክልል ሲዳማ፣ ወላይታና ጉራጌ ዞኖች ተከስቶ በነበረው የእርስ በርስ ግጭት የሰው ህይወት መጥፋቱ ይታወቃል። ይህንንም ተከትሎ ጠ/ሚ አብይ አህመድ ወደ አካባቢው በመሄድ የማረጋጋት ስራ ማከናወናቸው ይታወቃል።

ይሁን እንጂ በማህበራዊ ሚዲያ ትላንትና እና ዛሬ በተሰራጩት በጣም አስደንጋጭና ዘግናኝ የሆኑ በምስል የተደገፉ ጥቃቶች ህዝቡ ቁጣውን እየገለፀ ይገኛል። የጠ/ሚ አብይ አህመድ መንግስትም ወንጀለኞችን አጣርቶ በአስቸኳይ ለፍርድ እንዲቃርብ በማለት ማህበረሰቡ እየጠየቀ መሆኑ ተረጋግጧል።

ይህ በእንዲ እንዳለ በአሜሪካ የሚኖሩ የወላይታ ተወላጆች በዋሽንግተን ዲሲ ከኢትዮጵያ አምባሳደር ካሳ ተክለብርሀን ጋር ባደረጉት ውይይት ይህንን ሁሉ አሻጥር የሚሰራና ህዝብ ከህዝብ የሚያጫርሰን አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ነው፤ ለፍርድ ይቅረብልን በማላት እያለቀሱ አምባሳደሩን ሲማጸኑ እንደ ነበር በምስል ከወጣው ማስረጃ ማወቅ ተችሏል።