ጋዜጠኛ እስክንድ ነጋ በናሽናል ፕሬስ ክለብ ዋሽንግቶን ዲሲ

ጋሻው ገብሬ
አባይ ሚዲያ ዜና

ጋዜጠኛና የነጻነት ታጋዩ አቶ እስክንድንር ነጋ በጁን 20 ቀን 2018 ማምሻው ላይ በናሽናል ፕሬስ ክለብ ተገኝቶ ለቀረቡለት ጥያቄዎች መልስ ሰጥቷል።

ግብዣውን ያቀረቡለት በናሽናል ፕሬስ ክለብ የነጻ ፕሬስ ኮሚቴ እና የጋዜጠኝነት ሙያ ተቋሞች ናቸው።

ለአቶ እስክንድ ነጋ ናሽናል ፕሬስ ክለብ የነጻ ፕሬስ ኮሚቴ ግብዣ ሲያቀርብለት አቶ እስክንድር ህወሃት መሩ መንግስት ኢዴሞክራሲያዊነትና እና ፍጹም ጭቋኝነትን በመተቸት በድፍረት በመጻፉ እንደሆነ አቅርቧል።ከመታሰሩ በፊትም ሆነ በእስር ላይ አቶ እስክንድር የዴሞክራሲ አክቲቪስቶችን እና የዓለም አቀፍ የፕሬስ ነጻነት ታጋዮች እውቅና ማግኘቱንም አውስቷል። እሱን ማስፈታት የፕሬስ ነጻነት ተሟጋቾች፤ ፕሬስ ክለብንም ጨምሮ  ዋና ዓላማ ነበር ብለዋል የውይይቱ መሪ።

ለአቶ እስክንድ ነጋ በእስር እያለ የፕሬስ ክለብን ሽልማት፡የፔን አሜሪካ ከፍተኛውን የባርባራ ጎልድ እስሚዝ ሽልማት በ2012 አግኝቷል።ባለቤቱ ጋዜጠኛ ወ/ሮ ሰርካዓለም ፋሲል አብራው ታስርራ በእስር እያለች 2006 እዚያው እስር ቤት እንድትወልድ መደረጉን የፕሬስ ክለቡ ግብዣ አውስቷል።

ናሽናል ፕሬስ ክለብ ዋሽንግቶን ዲሲ ከሚታወቁት መንግስታዊ ያልሆኑ እውቅ ተቋማት አንዱና ዝነኛው ነው።ለታሰሩ ጋዜጠኞች ለእስክንድ ነጋም ጨምሮ ከእስር እንዲፈቱ የሚሞግት ስለጋዜጠኝነት ነጻነት በዓለም አቀፍ ደረጃ ተሰሚነት ያለው ነው።

አቶ እስክንድ ነጋ ጋር የነበረው ውይይት ስለ እስር ዘመኑ፤ለምን ህወሃት መሩ መንግስት ደጋግሞ እንዳሰረው በመጠይቅ ይነሳና አሁን እየተከሄደ ያለው ለውጥ ምን አቅጣጫን ይዟል የሚል ጥያቄን ያከለ ነበር።

አቶ እስክንድ ነጋ ዘጠኝ ጊዜያት እንደታሰረ፤ሰቆቃ እንደተፈጸመበት፤ለብቻው ጨለማ ቤት ተወውሮ እንደነበር መንግስት የፈጸመበትን በደል እየጠቀሰ ከተናገረ በኋላ “በዳዮቼን ይቅር ብያቸዋለሁ” በማለት ተናግሯል።

በእስር እያለህ እንጮህልህ ነበር።ያደረግነው ረዳህ ? ተስፋ ሰጥቶህ ነበር ለሚለው ጥያቈ አቶ እስክንድ ነጋ “በሚገባ ረድቶኝ ነበር።ኢትዮጵያው ውስጥ በእስር ያለው ቁጥሩ እንጅግ ብዙ ነው።ስሙ የተጠራ እስረኛ የተሻለ እድል” አለው በማለት ተናግሯል።

ዩ ኤ ስ አሜሪካ 2011 የሽብርተኛ ጥቃት ከደረሰባት ወዲህ “ሽብርተኛነት መዋጋት” አዋጅ አስነግራ በአፍሪካ ቀንድ እና ከሎሎችም አገራት ጋር አጋርነት መስርታ ነበር። “ሽብርተኛነት መዋጋት” የሚለውን መከታ አድርገው የራሳቸውን ዜጎች ካጠቁት መንግስታት መካከል ህወሃት መሩ መንግስት እንደነበር በውይይቱ ተነስቷል። አሜሪካ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ምን ተጽኖ አለው? ቀድሞ ለብዙ ጌዜ አምባገነኖችን ሲደግፍ በመቆየቱ ተአማኒነቱ ጎድሏል ቢባል አንተ ምን አስተያየት አለህ ለሚለው ጥያቄ  እስክንድር አሜሪካ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት አንስቶ የዴሞክራሲን ማንሰራራት አግዛለች።ዛሬም መልካሙ በማድረግ ብትቀጥልበት መልካም ውጤት ያፈራል ብሎ አስረድቷል።

ለጋዜጠኛ እስክንድር የቀረቡለት ሌሎች ጥያቄዎች ኢትዮጵያ ውስጥ ስለሚካሄደው ለውጥና ስለ ኤርትራና ኢትዮጵያ ግንኙነት ነበር።የህዝብ ንብረት የሆኑትን የኢኮኖሚ ተቋማት ወደ ግል ይዞታ ማዛወሩ ጉዳይ ጥንቃቄን የሚሻ እንደሆነ የኤርትራና ኢትዮጵያ የሰላም መንገድ ጅማሮው ማልካም እንደሆነም ገልጿል። መሰረታዊ ለውጥ ስለመጣቱ አሁን ልናገር አይቻለኝም ብሏል።አወያይዋ የኢትዮጵያ መንግስት ቻይናን የእድገት ምሳሌ(ሞዴል) አድርጎ የሚያይ ነው።ልማታዊ መንግስት የሚለውን መንገድ ተከታይ ነው።ስለዚህ ምን ትላለህ ለሚለው ጥያቄዋም መልስ ሰጥቷል። ኢትዮጵያ የልማታዊ መንግስትን የእድገት ፈለግ ተከትላ\ተግብራም ፈጣን እድገት ያለው ኢኮኖሚ ገነባች ቢባልም በህዝቡ የኑሮ ደረጃ የፈየደው ነገር የለም።”እድገት ይምጣና ዴሞክራሲ ይከተላል” የሚለው ዘይቤ አይሰራም።ስለማይሰራም ነው መንግስት ችግር የገባው በማለት ጋዜጠኛ እስክንድር አስረድቷል።መንሆን ያለበት የኢኮኖሚ እድገትም ዴሞክራሲም ጎን ለጎን የሚበለጽጉበት መንገድ ነው ብሏል።

ጋዜጠኝነት በቅንጅት ወቅት ወደ ነበረበት ድምቀት ይመለሳል ብለህ ታምናለህ? ወደ እዚያ እንዲያመራስ ምን መደረግ አለበት ትላለህ የሚልም ጥያቄ ቀርቦለት ጋዜጠኛ እስክንድር ሲመልስ እኔ የምጠብቀው የጋዜጠኝነትን ብቻ ነጻነት ሳይሆን የህዝቡን አጠቃላይ ነጻነት ነው።ለጋዜጠኝነትማ ትንሽ ቀዳዳ ብትከፈትልን እንኳ ያችን ይዘን እንታገላለን በማለት በቁርጥኝነት ሀሳቡን ገልጿል። የመጨረሻዎቹ ጥያቄዎች በጋዜጠኛነት ገለልተኛነትን መከተል ይቻላል ወይ የሚልና የኤስ አር 168 ጉዳይ ነበር።በሌላው ዓለም “በጋዜጠኛነት ገለልተኛነት” የሚለውን ማራመድ ይቀላል።በሙያውም የተደነገጉትን የዝገባ ስራቶች መከተል ተገቢ ነው።በኛ አገር ግን ጋዜጠኛ ስንሆን ከሙያችን አክለን የነጻነት ታጋዮችም እንሆናለን።እንዲያው ትንሽ መስራት የሚቻልበት እድል ማግኘታችንን እጠብቃለሁ በቀርቡም አገሬ እመለሳለሁ በማለት ተናግሯል።የኤስ አር 168 ትግሉን እንደሚያግዝም ገልጿል።ዝግጅቱን የአሜሪካ ድምጽ ትከታትሎት ነበር።