አማራ ማን ነው የቱስ ነው መመዘኛውስ ምንድን ነው (አሰፉ ከወገል ጤና)

0

ህወሃት የትግራይ ብሎ ዋናዎቹ ፈላጭ ቆራጮች የአድዋ ተወላጆች እንደሆኑ ከድርጅቱ የለቀቁትና ታሪኩን የተከታተሉት የወያኔን ዘረኝነት መሰረቱ ሲወርድ እጅግ የከፋ ጠባብነትና ቤተሰባዊነት የተንሰራፉበት ስለመሆኑ ሲያወግዙ ሰምተናል አይተናል:: እንደምሳሌም የሚቀርበው የወያኔ ቁንጮዎቹ መለስ ዜናዊ ስብሃት ነጋ እና ቤተሰቡ የደህንነት ሚንስትሩ ወታደራዊ አመራሩን የያዙት አብዛኞቹ ጀነራሎች በተለያዩ ወሳኝ መንግስታዊ ስልጣኖችና የኤፈርት ኩባንያዎች የበላይነቱን ተቆጣጥረው የፈለጉትን በትግራይ ህዝብ ስም ሲፈጽሙ ኖረዋል:: ዛሬም ይህንኑ አደረጃጀታቸውን እንዳስጠበቁ ነው:: 

 ይህንን የትግሬ ጋንግስተሮች ተግባር በተገፋውና ህልውናው አደጋ ላይ ለወደቀው የአማራ ሕዝብ ሃይልና ጉልበቱን እውቀትና አብሮነቱ አጠናክሮ እንዳይታገል ጎጠኛ አመለካከት ባላቸው ጥቂት ደካሞች ሌላው የአማራ ወገን ከትግሉ ግንባር በስድብና አሉባልታ እየተገፋ የትግሉ ባለቤት ሆነው መድረኩን የተቆጣጠሩትና የአድዋ ትግሬዎች አቅጣጫ የተከተሉት የጎንደር ጎጠኛ አንጃዎች በዚህ ያህል ድፍረትና አፍረት ማጣት በተለይ የወሎና የሸዋ አማራን በፍጹም አግልለው የአማራው ተወካይ ሆነው መቅረባቸው የሚያመጣው አደጋ በቀላሉ መታየት የለበትም::

ይህን ሃሳብ በዚህ ወቅት ለምን አስፈለገ ለሚሉ ተገቢ ጥያቄ ላላቸው ወገኖች እውነታው አማራው ያለውን አቅም አስተባብሮ ለመታገል የወሰነበት ወቅትና ግዜ ላይ በመድረሱ አብሮነቱ እንዳይላላ ከወዲሁ እርምት እንዲወሰድበት ነው:: በሃገር ቤት አማራው ድርጅት መስርቷል:: ይህ ድርጅት ሕልውናው አደጋላይ ለወደቀው የአማራ ወገን ወሳኝ ተቋም ነው:: ይህን መሰል ህዝብ አድን ተቋም ንፋስ እንዳይገባበትና ከመንገድ እንዳይሰናከል መጠንቀቅ መጨነቅና ማሰብ ከእያንዳንዱ የአማራ ተወላጅ የሚጠበቅ ጉዳይ ነው:: 

 ይህ በመሆኑም አማራ ማለት ጎጃም ጎንደር ሸዋና ወሎን የሚያካትት ከፍና ዝቅ የሌለው ውህድ ማንነትን ያማከለ በመሆኑ በተቋማት ውስጥ የአካባቢ ውክልና ይሰጥ ባይባልም ሁሉንም ግን ሊያሳትፍ የሚገባ ስለመሆኑ የሚያከራክር አይደለም:: ይህን ሃቅ የሚቀበል ትግሉን በሁሉም የአማራ አካባቢዎች እንዲስፋፋ የሚፈልግ የወገንና የሃገር ጉዳይ ከምንም በላይ የሚያሳስበው አማራ ይህን አይነት አካሄድ ሊያወግዝና እንዲስተካከል የማድረግ ግዴታ ይኖርበታል:: 

 እነዚሁ የአንድ አካባቢ ቡድኖች ያቋቋሙት አድማስ የተባለው የድርጅቶችና የግለሰቦች ስብስብ የአማራውን ማህበረሰብ ተደራሽ ያላደረገ ለመሆኑ ከአብዛኞቹ አባሎቹ የትውልድ አካባቢና ትኩረት ሰጥተው የሚያደርጉትን ለተከታተለ የሚባለው አይጠፋውም::  በተለይ  በሃገር ቤት የተቋቋመው አዲሱ የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ ይህንን አይነት የጎጥ ስብስብ የሞላበት ቡድን በጥንቃቄ እንዲመለከተው አደራ ለማለት አወዳለሁ:: 

አድማስ የሚባለው የአማራ ድርጅቶች ሕብረት ዳግማዊ ጎንደር ሕብረት:

1, ተክሌ የሻው   የአማራ ህልውና ለኢትዮጵያ አንድነት ሊቀመንበር 

2, ተክሌ የሻው የሞረሽ ሊቀመንበር ጎንደሬ

3, የአማራ ሬድዮ ተክሌ የሻው ዋና ሃላፊ በስውር   ጎንደሬ

4, የቤተ አማራ መሳፍንት ታምራት   ጎንደሬ

5, ብራና ሬድዮ ሙሉቀን ተስፋው ጎንደር

6,አዴሃን ኮሎኔል አለበል ጎንደር (ተለጣፊው አዴሃን ታዘበው ጎጃም)

7,አለም አቀፍ የአማራ ምክር ቤት ዶ/ር አቤል ጎንደር

8, መአህድ የውጭው አንዱአለም ተፈራ ጎንደር

9, ልሳነ አማራ ባዬ ተሻገር ጎንድር 

10, የዳግማዊ አማራ አርበኞች  ያረጋል ይማም ጎጃም

11, የወልቃይት ጠለምት ቡድን ጎንደር

12 በሲያትል የአማራ ህብረት የጎንደር አካባቢ ስብስብ

13, አህመን የጎጃም ተወላጆች ብቻ ያሉበት ስብስብ

14, አምባ  (የአማራ ፕሮፌሽናል ስብስብ )ዶ/ር ወሰን ያለው ጎንደር

15, የዲሲ አማራ  ማህበር ጎንደር

16, የአማራ ማህበር በአሜሪካ ቴድሮስ ትርፌ ጎንደር 

17, የግዮን ድምጽ ምስጋናው አንዷለም ጎንደር

18, ጎጃምሕብረት (ጎዣም)