ቅዳሜ June 30,2018

በሚዙሪ ሴንትሉዊስ ከተማ ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያኖች በሃገራችን እየተካሄደ ያለውን ለውጥና በተለይ ባለፋት 3 ወራቶች ዶ/ር አብይ አህመድ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስቴር ሆነው ከተመረጡ በሃላ እያሳዩ ላለው ፈጣን መልስ በተለይም ለ27 ዓመታት ኢትዮጵያዊነት ደብዝዞ የነበረውን ከፍ አድርገው በማሳየታቸውና ለፍቅር ለይቅርታና የመደመርም ተምሳሌት በመሆናቸው ይህንኑ ጅምራቸውን ለመደገፍ የሴንትሊውስ ነዋሪዎች መንፈሳዊ እባቶችና የከተማው ታላላቅ ሰዎች በተገኙበት በቅርቡ በተከፈተው የኢትዮጵያ ሆቴል አዳራሽ በደማቅ መልኩ ድጋፋችንን በመግለፅ ተከብሮ ውሏል በዚሁ በአል ላይም የሃይማኖይ አባቶች ተዋቂ የከተማው ሰዎችና የከተማው የኢሳት ቤተሰብ ሊቀመንበር የተለያዩ መልእክቶች አስተላልፈው በቀጣይም

ከጠቅላይ ሚኒስተራችን ጎን በመሆን እንደምንሰራና ሰኔ 16 ላይም በደረሰው ለሞቱትና ለተጎዱት የተሰማንን ሃዘን በመግለፅ በማንኛውም መንገድ የእርዳታ እጃችንንም ለመለገስ ቃል በመግባትና ኢትዮጵያ ሃገራችን በዚህ ወሳኝ የለውጥ ግዜ የሚፈለግብንን ነገሮች ሁሉ ለማከናወን ዳግም ለዚህ ለውጥ መሰዋትነትን በከፈሉ ወገኖቻችን ስም ቃል በመግባት በአሉ ተጠናቅቋል::