አባይ ሚዲያ ዜና

ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሮሽን (Ethiopian Broadcasting Corporation) የቦርድ አባል ሆነው አገራቸውን እንዲያገለግሉ መመረጣቸው ተዘገበ።

በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ቆይታቸው  እውቀታቸውን በማካፈል በርካታ ኢትዮጵያውያንን ሲያገለግሉ የቆዩት ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና አሁን ደግሞ በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሮሽን  ኢትዮጵያውያንን ለማገልገል በአባልነት ተመርጠዋል።

ፕሮፌሰር መረራ ጉዲናን ጨምሮ አቶ ፍሰሀ ይታገሱ እና ወይዘሮ ሃሊማ ባድገባ የመንግስት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አህመድ ሽዴ  በሰብሳቢነት በሚመሩት በዚህ ቦርድ ውስጥ በአባልነት  እንደተካተቱ  ተጠቅሷል።

ከወደ ጅማ ከተገኘ ዜና ደግሞ በኢትዮጵያ ውስጥ እየታየ ላለው አበረታታች ለውጥ የማይረሳና ደማቅ አሻራቸውን በታሪክ  ያሰፈሩት ክቡር ኦቶ ለማ መገርሳ የክብር ዶክትሬት ተሸላሚ ሆነዋል።

ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው በሚል ንግግራቸው በእሳት ወቅት ወርቅ ሆነው የተገኙት የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልል ርዕሰ መስተዳዳር ክቡር አቶ ለማ  መገርሳ በሰላምና ደህንነት ከጅማ ዩኒቨርስቲ የክብር ዶክትሬት ተሸልመዋል።

ጅማ ዩኒቨርስቲ በተለያዩ የትምህርት ዘርፍ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች በደመቀ ስነስርአት አስመርቋል። ለተመራቂ ተማሪዎች እንዲሁም የክብር ዶክትሬት ተሸላሚ ለሆኑት ክቡር አቶ ለማ መገርሳ እንኳን ደስ አላችሁ እንላለን።