ኢት-ኢኮኖሚ           /ET- ECONOMY

በ1983ዓ/ም  ወያኔ ዓሳራ “ግመሎቹ ይሄዳሉ፣ ውሻዎቹ ይጮሃሉ!”ይል ነበር፡፡ከ2008ዓ/ም ጀምሮ ህዝብ “ግመሎቹ ይጮሃሉ፣ ውሻዎቹ ዝም ብለዋል!”አላቸው!!!

የዴሞክራሲና የፀረ-ዴሞክራሲ ኃይሎች ፍልሚያ !!! 

ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ  በ100 ቀናት ውስጥ የሰሩት አስደናቂ ሥራዎች በተለያዩ የባህር ማዶና የሃገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን መደመጡ ዋቢ ምስክር አያስፈልገውም፡፡ ሌሎቹ የተለያዩ ሚንስትሮች ከተሾሙ ጀምረው ምን ሰሩ ምን ለመስራት አቀዱ፣ በየመሥሪያ ቤቱ ምን የእርምት እንቅስቃሴ አደረጉ፣ ለመገናኛ ብዙኃን በራቸው ክፍት አድርገዋል ወይ፣ ሙስናንና ሌብነትን ለመዋጋት ያላቸው ቁርጠኝነት ምን ድረስ ነው፣ ከሰራተኞቻቸው ጋር ያላቸው ግንኙነት እንዴት ነው፣ መስሪያ ቤቱ ከህብረተሰቡ ጋር ያለው ግንኙነት ምን ይመስላል፣ የመሳሰሉት ለግልፅነትና ለመልካም አስተዳደር የእርምት እንቅስቃሴ በር ይከፍታል እንላለን፡፡ ብዙዎቹ  ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶችና ኤጀንሲዎች በድረ-ገፆቻቸው መረጃ ለህዝብ መስጠትና ለዮኒቨርሲቲ የጥናትና ምርምር ተማሪዎችና መምህራን እንዲሁም የምጣኔ ሃብት፣ የማህበራዊ ጥናት ተመራማሪዎች ለጥናታቸው ግብዓቶች የሚሆኑ ስታስቲካል/ አሀዛዊ መረጃዎች የማግኘት መብት በህገ-መንግስቱ የተረጋገጠ በመሆኑ ተግባራዊ የማድረግ ግዴታ እያንዳንዱ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶችና ኤጀንሲዎች ኃላፊነትና ግዴታ መሆኑን ሊገነዘቡ ይገባል፣ ብሎም ተግባራዊ ካልሆነ ተጠያቂነት እንዳለባችሁ ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶችና ኤጀንሲዎች የፕሬስና የሌሎች መገናኛ ብዙኃን፣ የህዝብን ጥቅም የሚመለከት መረጃ የማግኘት ዕድልን መስጠትና ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎች፣ ሃሳቦችና አመለካከቶች በነጻ መንሸራሸራቸውን ለማረጋገጥ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶችና ኤጀንሲዎች በድረ-ገፆቻቸው ማስተናገድ ይኖርባቸዋል፡፡ ወጣት የዲጅታል ቴክኖሎጂ ሙያተኞች በድረ-ገፆች መረጃ የማቅረብና የማሰራጨት ክህሎታቸውን የመጠቀም መብት አላቸውና፡፡ የዴሞክራሲ ኃይሎች እንደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የ100 ቀናት የሥራ ክንውን ግምገማ ልዩ ልዩ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶችና ኤጀንሲዎች ባለስልጣኖች የሥራ እቅድና አፈፃፀም ለህዝብ ይፋ መሆን አለባቸው እንላለን፡፡

  • ኢትዮ ቴሌኮም፣ የኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን የሃገሪቱን ህዝብ ተልኮውን ሳይወጣ ህዝብ ሲሰልል፣ ሲያሳስር የከረመ ድርጅት ነው፡፡ በኢትዮጵያና በኤርትራ ህዝብ ለአለፉት 20 አመታት የስልክ አገልግሎት በማቆረጥ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቶችን ያቆረጠ ድርጅት ነው፡፡
  • የማዕድን፣ ነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ሚኒስቴር፣ የሜድሮክ የወርቅ ማዕድንና የኢዛና ወርቅ ማዕድኖች ያመረቱትን ወርቅ ወደ ብሄራዊ ባንክ ገቢ ሳያደርጉ ባህር ማዶ እየሸጡ እንደነበር ታጋልጦል፣ ጋዜጠኞች ጉዳዩን መርምሮ ፀሃይ እንዲሞቀው ማድረግ ያሻል፡፡
  • የትራንስፖርት ሚኒስቴር፣ ሙስና ተጋለጠ፣ በአዲስ አበባ አስተዳደር የመንግስት የአንበሳ አውቶቡስ ውስጥ 120 አውቶብሶች ሊብሬ የሌላቸው በሌብነት ገንዘቡ የግለሰቦች መጠቀሚያ እንደሆነ ታውቆል፣ የኢፈርት አውቶብሶችና የጭነት መኪኖችም ይጋለጡ፡፡
  • የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ፣ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል ምርመራ ቡድን ፀረ ዲሞክራቲክ ኃይል በመሆን የሃገረቱን ለውጥ ና ጸጥታ ለማደፍረስ የቀድሞ የኢንፎርሜሽንና መረብ ደህንነት ኤጀንሲ (ኢንሳ) ምክትል ዳይሬክተር ኮ/ል ቢንያም ወልደ ማርያም በቁጥጥር ስር በማድረግ የሰሩት ስራ ያስመሰግናል፡፡ የማረሚያ እስር ቤት ሁኔታን ማሻሻልና የግርፋት (ቶርቸር) ማስቀረት፣ ገራፊዎቹን ለፍርድ ማቅረብ፣ ማረሚያ ቤቱን ታራሚዎች አያያዝ ማስተካከልና በመገናኛ ብዙሃን የቀድሞ እስረኞችና የአሁን አያያዝ ሁኔታን በግልፅ ማሳየት  ወዘተ እርማቶች በማስተካከል ላይ ይገኛሉ፡፡ በሃገሪቱ ያሉ ስውር የወያኔ እስር ቤቶች ይጋለጡ፡፡
  • በኢፈዴሪ የመንግስት ቤቶች ኤጀንሲና የመንግስት ቤቶች ኤጀንሲ፣ ቤት ሰርተው የሚያከራዩ በመንግስት ቤቶችና በቀበሌ ቤቶች የሚኖሩ ሹማምንቶች እንዲሁም መከላከያ በሰራቸው ወታደራዊ ኮንዶሚንየም ቤቶች የሚኖሩ ጀነራል መኮንኖችና ደህንነቶች ብሎም ሁለትና ሦስት ኮንዶሚኒየም የተሰጣቸው ሌቦች ተጋልጠው ለፍርድ መቅረብ አለባቸው፡፡ የመንግሥት ቤት ካርታን በስማቸው ያዞሩ አዲሱ ለገሠ፣ ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሄር፣ አስመላሽ ወልደስላሴ፣ ስብሃት ነጋ፣ አዜብ መስፍን ወዘተ ሌሎችም ተጋልጠው በህግ ፊት ሁሉም ዜጋ እኩል መሆኑንና ለሌባ ፍርድ መስጠት የሃላፊነት ግዴታ ነው፡፡ ሙስናውን የሚያውቁ የመስሪያ ቤቱ ሠራተኞች በተጠያቂነትና በተባባሪነት በህግ ይጠየቃሉ፡፡ በተለያዩ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶችና ኤጀንሲዎች የሚገኙ ሠራተኞች ሙስናና ሌብነትን የማጋለጥ ባህላቸውን በማዳበር ከዴሞክራሲ ኃሎች ጋር መደመር የህልውና ጉዳይ ነው፡፡ የገማው የመንግሥት ቤቶች ኤጀንሲ ይዘጋ፡፡
  • የኤፌዲሪ ሀገር መከላከያ ሚኒስቴር፣ በሙስና የተዘፈቁ የሜቴክ ጀነራል መኮንኖች በተጠያቂነት ለፍርድ ማቅረብና ሌሎች የሌብነት ወንጀሎች ማጋለጥ ሠራዊቱ ውስጥ የሚገኙ አባላቶች ተሳትፎን ይጠይቃል፡፡ በኢትዮጵያና ኤርትራ መንግሥቶች የተፈረመው የሰላም ስምምነት በቀጣኝነትና በዘለቄታው ሠራዊቱን ወደ ቀድሞው ቦታ መመለስ ለሁለቱም ሃገራቶች የኢኮኖሚ ልማት የሚያስገኘው ፋይዳ አመታዊ ወጪ የሆነውን ከ15 እስከ 20 ቢሊዮን ብርና ናቅፋን ስለሚያድን ለልማት ሥራ በማዋል መተግበር አለበት እንላለን፡፡የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ከካንፑና ከምሽጉ ቀበሮ ጉድጎዱ ወጥቶ በአዲሱ አመት በእንቁጣጣሽ ከቤተሰቦቹ ጋር ይቀላቀል እንላለን፡፡
  • የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴርና የሴቶችና ህጸናት ጉዳይ ሚኒስቴር፣ 24 ሽህ ህፃናቶችን በማደጎነት የሸጡና ከነዚህ ውስጥ 7 ሽህ ህፃናቶች ወላጆች ልጆቻቸው የት እንዳሉ እንደማያውቁ መስሪያ ቤቱን ሲጠይቁም መልስ አለማግኘታቸው ቢጋለጥም የሹማምንቶቹ ተጠያቂነትና ለፍርድ አለመቅረብ በኢትዮጵያ ፍትህ የጨለመ፣ ጋዜጠኞች ለህፃናቱ ህይወት አለመታገል፣ ያስቆጫል፡፡
  • የፌዴራል ጠቅላይ አቃቢ ህግ፣ የፍትህ ሚኒስትር በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት እንዲሁም በከፍተኛ ፍርድ ቤት 120 ዳኞች ሹመታቸው በህዝብ ተወካዮች ምክርቤት መፅደቁ ፍትህ ለተጠማ ህዝብ ትልቅ አስተዋፆኦ አለው፣ ለ27 አመታት ፍትህ ያዛቡ ዳኞች በተጠያቂነት ለፍርድ መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ የወያኔ የጅምላ መቃብር ሥፍራዎች በትግራይ፣ በአፋር፣ በጋምቤላ፣ በደቡብ በሎቄ ሲዳማና በአረካ የወላይታ፣ በኦሮሚያ፣ በሃረር፣ ወለጋ፣ በባሌ ዶሎመና፣ በሱማሌ ሁሉ ግዛት፣ በአማራ ጎንደር ወልቃይት፣ ደብረማርቆስ፣ ደብረብርሃን፣ አዲስአበባ በወያኔ የጦር ሠፈሮች ውስጥ ተቆፍሮ ይወጣል!!! የወያኔ የዘር ፍጅት ተዋናዬች ተጠያቂ ለፍርድ ይቅረቡ፡፡ 
  • የፌደራል ዋና ኦዲተር፣ በልዩ ልዩ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶችና ኤጀንሲዎች ያደረገው የኦዲት ሪፖርት ተጠያቂዎች ለፍርድ እንዲቀርቡ፡፡

የህዝብ ተወካዬች ምክር ቤትና የፌደሬሽን ም/ ቤት፣ በኦነግ፣ኦብነግና ግንቦት 7 ላይ ተጥሎ የነበረው የሽብርተኝነት ክስ መሠረዝ፣ የመንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የወጣ ህግና የቦዘኔ በተመለከተ ህግ ማምከን የዴሞክራሲውን ምህዳር ያሰፋዋል፡፡ እንዲሁም የመለስ ዜናዊ ክልሎች የበጀት ቀመር አድሎዊና ፍህታዊ ባለመሆኑ ዶክተር አብይ አህመድ ለሙያተኞች አስጠንተው በዘርና የልሳን ፌዴራሊዝም ላይ ያልተመሠረተ ሁሉንም ዜጋ የሚያካትት የበጀት ቀመር ማድረግ የሚነሳውን የማንነት ጥያቄ በጀትን የሽሮ መብያ ያደረጉ ዘውጌ ብሄርተኞችን የገቢ ምንጭ ያደርቃል እንላለን፡፡ የብሄርና የብሄረሰብ የማንነት ጥያቄ በቀጥታ ከበጀት ድልድል ጋር የተያያዘ መሆኑን በተደረጉ ጥናቶች መረዳትና ወይም ማስጠናት ከዚህ የዘር ፍጅት፣ የሃብት ድርሻ፣ የመሬት፣ የግጦሽ ቦታ፣ ግጭቶችና የማንነት ጥያቄ እድገት መጨመር መንስኤው ወደ ልዮ ዞንና ፣ የክልል መንግስት ለማደግና በጀት ቅርምቱና ድልድል ገንዘብ ከማግኘት ጋር የተያያዘ መሆኑን ለቅጣት አንጠራጠርም፡፡ በሃገራችን የማንነት ጥያቄ የሽሮ መብልያ ጥያቄ ነው፣ ሲዳማ፣ ጉራጌ፣ ወላይታ ወዘተርፈ እያለ 80ዎቹ ሁሉ የመጠየቅ መብት እንዳላቸው መረዳት አልያም የማንነት ጥያቄን በሰውነት ጥያቄ ለውጦ ከጠባብ ብሄርተኝነት ህብረ ብሄራዊ ሃገር መገንባት አማራጭ የሌለው መፍትሄ ነው እንላለን፡፡ የበጀቱ ቀመር በዘውጌና በልሳን ላይ የተመሠረተ አይሁን አልን እንጅ ክልሎች ባህላቸውን መጠበቅ፣ ልሳናቸውን መጠቀም፣ ማዳበር ስብአዊ መብታቸው መሆኑን ማክበር ሊዘነጋ አይገባም፡፡          

የክልል መንግሥታት፣ የኦሮሞ ክልል ፕሬዜዳንት ኦቦ ለማ መገርሳ  ለጨፌ ኦሮሚያ (ለኦሮሚያ ምክር ቤት) የክልሉ ፀጥታ መደፍረስ በንቃት ይከታተላሉ፣ ፀረ ዲሞክራቲክ ኃይሎችን የክልሉን ጸጥታ ለማደፍረስ የሞከሩትን ነቅሶ በማውጣትና  ከኦሮሚያ መንግሥታዊ መዋቅር በመንቀል አስፈላጊውን ቆራጥ ዕርምጃ በመውስድ ያደረጉት የፀረ ዴሞክራሲ ሃይሎችን ማዳከም ቆራጥ አቋም በሌሎች ክልሎች  መቀጠል ይኖርበታል። ዶክተር አብይ አህመድ በኦሮሚያና ሱማሌ ክልል ያለውን ግጭት ለማስቆም የመከላከያ ሠራዊተወና  የፖሊስ ኃይል ማሰማራቱ የሚደገፍ ነው። በሌሎችም ቦታዎች በፍጥነት ማሰማራት በህይወትና ንብረት ውድመትን ያስቆማል፡፡ የሶማሌ ክልል ፕሬዜዳንት አብዲ ኢሌ በሱማሌ ብሮድባንድ ለጋዜጠኞች ያቀረቡትን የጌታቸው አሰፋን ጉድ አዳመጠን፣ የአብዲ ኢሌ በህዝብ ላይ የፈጸሙትን ግፍ አወቅን መረጃ የማወቅ መብት በሃገራችን ሊበረታታ ይገባል፡፡ በተመሳሳይ የአማራ ክልል ፕሬዜዳንት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የብአዴን የእንግዴ ልጆችን ጠርጎ መጣልና ፀረ ዲሞክራቲክ ኃይሎችን የክልሉን ጸጥታ ለማደፍረስ የሚሞክሩትን አረሞች በጊዜው ማረም አስፈላጊ ነው፡፡ ዳተኝነት አያዋጣም፡፡  

የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ቴሌቪዝን የእስረኞች አያያዝ ሁኔታን ለህዝብ ይፋ በማድረግ፣ የተለያዩ መንግሥት ሹማምንቶችን በጥያቄ ማፋጠጥ፣ የሜጋ ፕሮጀክቶችን ሁኔታ በግልፅነት መከታተል፣ ሃቁን ለህዝብ የማቅረብ የጋዜጠኝነት ሥነምግባር በመወጣት፣ የኢትዮጵያ ብሮድካስት የቦርድ አባል አድርጎ ዶክተር መረራ ጉዲናን ሾሟል። የእርምት ንቅናቄው ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል እንላለን፡፡

የኢትዮጵያ ብሮድካስት በግብር ከፋዩ ህዝብና በመንግሥት ገንዘብ የሚካሄድ ወይም በመንግሥት ቁጥጥር ሥር ያለው መገናኛ ብዙኃን ላለፉት 27 አመታት የህወሓት/ኢህአዴግ ፖለቲካን ሲያናፉና በውሽት የተቀቀለ መረጃ ሲያቀርቡ የኖረ፣ ለሙስናና ሌብነት ከለላ ሲሰጥ የኖረ፣ ለዋልጌነትና ለምግባረ ብልሹነት ዋስትና የሰጠ ሲሆን፣ በመልካም አስተዳደር ሥነምግባር ብልሹነት፣ ለፀያፍ አነጋገርና ስነዜጋ ለጎደለው የሚዲያ የጋዜጠኝነት አቀራረብ፣ ተጠያቂነትና የችሎታ ማነስና በዘመድ አዝማድ መቀጠርና ከችሎታ ይልቅ በዘር ተኮር መመዘኛ ያተኮሩ መሆናቸው ይታወቃል፡፡ በእርምቱ እንቅስቃሴ በዩኒቨርሲቲ መምህራኖች ፈተና ወጥቶ ያለአንዳች አድሎ ተፈትነው የሥራ ብቃትና ችሎታ ያላቸው መስፈርቱን የሚያሟሉ ጋዜጠኞችና ሙያተኞች ቦታውን መያዝ ይገባቸዋል፡፡ ዴማክራሲያዊ ጋዜጠኞች የተለያዩ አስተያየቶች የማስተናገድ ችሎታ የተገነዘቡ፣ ወገንተኝነት የሌላቸው፣ ሚዛናዊ ፍርድና የጋዜጠኝነት ሙያ ፍቅር ያላቸው፣ ለፕሬስ ነፃነት ማበብ አስተዋፅኦ ያበረከቱ፣ በባህር ማዶና በሃገር ውስጥ የሚገኙ የተባረሩ ጋዜጠኞች ይቅርታ ተጠይቀው ተመልስው እንዲሰሩ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ በወያኔ የፖለቲካ ፓርቲ አደግዳጊነት የተሰጡ የብሮድካስት የቴሌቪዝን፣ ሬዲዬና ኤፍኤም ሬዲዬኖች ንብረት የግብር ከፋዮ የኢትዮጵያ ህዝብ የተገዙ ንብረቶች በሃቀኛ ሠራተኞች ተጋልጠው ለህዝብ የማሳወቅ ግዴታ አለባችሁ እንላለን፡፡ የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ አመዛኙን ብሮድካስቶች በግሉ ዘርፍ እንዲሸጡ ማድረግ አስፈላጊ ነው እንላለን፡፡ አንድ ሽህ አንድ የኢትዮጵያ ብሮድካስት የውሸት ወሬ በቅፌን፣  አንድ ለናቱ ኢሣት እንደደባለቀውና፣ ኦኤምኤን እንደደቆሳቸው ህዝብ ያውቃል፡፡ 

የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶችና ኤጀንሲዎች የ100  ቀናት የሥራ ክንውናቸውን በጋዜጠኞች መጠየቅና መመለስ የዴሞክራሲ ባህል መለመድ አለበት፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሴቶችና ህጸናት ጉዳይ ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን
የኤፌዲሪ ሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የማዕድን፣ ነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ሚኒስቴር የኢትጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት
የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የፌደራል ሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ
የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የፌዴራል ጠቅላይ አቃቢ ህግ የፌደሬሽን ም/ ቤት
የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ታላቁ የህዳሴ ግድብ
የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ሚኒስቴር ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ የመንግስት ቤቶች ኤጀንሲ
የትምህርት ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የኢትዮጵያ ካርታ ሥራ ኤጀንሲ
የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የፌደራል የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ
የፌደራልና አርብቶአደር ልማት ጉዳዮች ሚኒስቴር የፌደራል ዋና ኦዲተር የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ኢትዮ አይሲቲ ቪሌጅ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የንግድ ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ኢትዮ ቴሌኮም
የፐብሊክ ስርቪስና የሰው ሃብት ልማት ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ሥራ አመራር ኢንስቲትዩት የመንግስት ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ
የእንሰሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ሚኒስቴር የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ የግል ድርጅቶች ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ
የትራንስፖርት ሚኒስቴር የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመፃህፍት ኤጀንሲ
የውሃ፣ መስኖና ኤሌትሪክ ሚኒስቴር የፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን የፌደራል ጥቃቅንና አነስተኛ ማህበራት
የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስቴር የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የመንግስት ግዥና ንብረት ማወገድ አገልግሎት
የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ድርጅት
የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በኢፈዴሪ የመንግስት ቤቶች ኤጀንሲ የፌዴራል ኤች አይቪ ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ  ጽ/ቤት

ሁሉም የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶችና ኤጀንሲዎች፣ ሙስናና ሌብነትን የማጋለጥ ቀጣይ ዘመቻ፣ በድረ-ገፆች የህዝብ ጥያቄንና አስተያየት መቀበል እንዲሁም የዴሞክራሲያዊ ባህልን ማዳበር፣ ተጠያቂነትን ማስፈንና  አስፈላጊ ነው እንላለን፡፡ ከዴሞክራሲ ኃይሎች ጋር በጊዜው ይደመሩ እንላለን!!! በመቐለ የመሸጉ የወያኔ ፀረ-ዴሞክራሲ ኃይል የዓሳራ ግመሎች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ፣ የትግራይ ህዝብ አሳልፎ እንዲሰጣቸው እንጠይቃለን፡፡  

‹‹ድር ቢያብር፣ አንበሳ ያስር!!!››  የመምህራን ማህበር፣የተማሪዎች ማህበራት፣ የሠራተኛ ማህበራት፣ የሴቶች፣ የገበሬዎች፣ የወጣቶች፣ የታክሲ ሹፌሮች  ማህበራት ተጠናክረው የዴሞክራሲ ኃይሉን መቀላቀል ይጠበቅባቸዋል፡፡ 

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ከካንፑና ከምሽጉ ቀበሮ ጉድጎዱ ወጥቶ በእንቁጣጣሽ ከቤተሰቦቹ ጋር ይቀላቀል!!!

አድርባይ ምላሳዊ ጋዜጠኞች ይወገዱ!!! የኢትዮጵያና ኤርትራውያን ህዝቦች ወዳጅነት ይጠንክር!!!

የዴሞክራሲ አብሪ ጥይቶች በሃገራችን ሰማየ ሰማያት ላይ ተተኩሰዋል!!!

 ( ሃምሌ 10 ቀን 2010ዓ/ም ተፃፈ )