ባገር-ወገን ክብር  ቅን ልብህ የፈካ፣ የፍቅር፣ የሰላም፣ 

የአንድነት.. ዋርካ፤ ወገን አለኝ ብለህ  ባሕር-ማዶ ዘልቀህ፣

ልታየን የጓጓህ – እንኳን ደህና መጣህ!

ግንቡን አስፈርሰህ – ድልድይ ልትዘረጋ፣ ለመሸጋገሪያ –

ወደላቀ ጸጋ፣ ለኢትዮጵያችን ክብር – አርቀህ በማሰብ፣

የጠፉትን በጎች – ከዓለም ልትሰበስብ፣በክንፍህ ጥላ ስር –

ሁሉን ልትደምር፣ ህብረ-ብሔራዊ – ዜማን ልታዘምር፤

እንኳን ደህና መጣህ! – በድሉ ጎዳና፣ የጀግና አቀባበል – ይገባሃልና!
ያርባ ዓመት ታሪክ..

በሦስት ወር የቀየርክ፣

አንተ የልብ ሐኪም – ያገር ሕይወት ቤዛ፣ ግብርህም ይባረክ! – በረከተህ ይብዛ!

ክፋት፣ ምቀኝነት..፣ ጥላቻን.. ሰርዞ፣

መከባበር፣ ኅብረት..፣ ዕድገት፣ ጥበብ.. ይዞ፤ የተሳካ ይሁን! – የጀመርከው ጉዞ።

የድንቅ የውብ አገር – የታላቅ ሕዝብ መሪ፣ አዲስ ባለራዕይ –

ደማቅ ታሪክ ሰሪ፣ የዜጎችህ ኩራት – የወገን አለኝታ፣

ሁሉ ይስመርልህ – በሄድክበት ቦታ፤

ይጎዝጎዝ ቄጠማ – ይበተን አበባ፣

የደስታ ቀን ይሁን – አንተ ስትገባ፤

ወርቀ-ዘቦ ምንጣፍ – ይዘርጋ ለክብርህ፣

ዐቢይ ኢትዮጵያዊ – እንኳን ደህና መጣህ!

ሐምሌ 2010 ዓ/ም      (ጁላይ 2018)

floweres