ይህችን ጽሁፍ ለመጻፍ ያነሳሳኝ ከሶስት ወራት በፊት አዲሱ የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ሆነዉ በኢሕአዲግ የተመረጡት ዶ/ር ዓብይ አህመድ ኢትዮጵያዊያንን እና ትዉልደ ኢትዮጵያዊያንን ለመጎብኘትና ለማነጋገር ወደ ሰሜን አሜሪካ ተጉዘዉ ዋሺንግተን ዲሲ የፊታችን ቅዳሜ ሐምሌ 21 ቀን 2010 ዓም (July 28, 2018) እንደሚገኙ በመስማቴ ነዉ፡፡ ይህ ታላቅ እና አስደሳች ዜና የፈጠረብኝን ደስታ ለመግለጽ ቃላት ቢያጥሩኝም በዉስጤ የተሰማኝን ፍጹም ደሰታ እና አግርሞት ለመግለጽ ዛሬ ያለንበትን ዘመን መዋጀት ጥሩ መንገድ ነዉ ብዬ አስብኩኝ፡፡ ለዚህም እንዲረዳ በተለይም የኢትዮጵያን ጠ/ሚ ዶ/ር ዓብይን እና የአሜሪካኑን ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕን በንጽጽር መልክ ማየቱ የእኔን ብቻ ሳይሆን የብዙ ቅን እና አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያኖችን ስሜት ይገልጻል ብዬ እገምታለሁ፡፡ Read In PDF

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here