ምስል ከፋይል

አባይ ሚዲያ ዜና

በመስከርም 5 ቀን 2011 ዓ.ም በጉጉት ይካሄዳል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረው የድምጻዊ የቴዲ አፍሮ ኮንሰርት በተባለበት ቀን እንደማይካሄድ ተገለጸ።

በሚሊኒየም አዳራሽ መስከርም 5 ቀን 2011 ዓ.ም ለኢትዮጵያውያን የሙዚቃ ኮንሰርት ለማድረግ ፕሮግራም የያዘው ተወዳጁ ቴዲ አፍሮ ፕሮግራሙን ለሌላ ቀን እንዲያስተላልፍ ተጠይቋል።

በመስቀል አደባባይ የኦንግ አመራሮችን ለመቀበል በተመሳሳይ ቀን (መስከረም 5 ቀን 2011 ዓ.ም) ፕሮግራም መያዙን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በመግለጽ በዚሁ ቀን ከተማ ውስጥ ጭንቅንቅ ሊኖር እንደሚችል በማስረዳት የድምጻዊ ቴዲ አፍሮ ኮንሰርት ወደ ሌላ ቀን እንዲተላለፍ የከተማው አስተዳደር ያቀረበው ጥያቄ ተቀባይነት ማግኘት እንደቻለ ለመረዳት ተችሏል።

በኢትዮጵያውያን ተወዳጅ የሆነው ድምጻዊ ቴዲ አፍሮ ከአዲስ አበባ መስተዳድር የቀረበውን ጥያቄ በመቀበል የኮንሰርት ዝግጅቱን ቅዳሜ መስከረም 12 ቀን 2011 ዓ.ም እንደሚያደርግ ተገልጿል።

“ኢትዮጵያ ወደ ፍቅር” በሚል መርህ ቅዳሜ መስከርም 12 ቀን 2011 ዓ.ም ተወዳጁ ድምጻዊ ቴዲ አፍሮ ለኢትዮጵያውያን በሚሊኒየም አዳራሽ ኮንሰርቱን እንደሚያቀርብ ማናጀሩ ተናግረዋል።