አባይ ሚዲያ ዜና

ወደ ሳውዲ ያቀኑት ጠ/ሚ ዶክተር አብይ አህመድ ከፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር በመሆን ከፍተኛ ሽልማት ተበረከተላቸው።

የሳውዲው ንጉስ ሳልማን ለጠ/ሚ ዶክተር አብይ እና ለፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በሳውዲ አረቢያ ከፍተኛ የተባለውን የክብር ሜዳሊያ ሸልመዋቸዋል።

ጠ/ሚ ዶክተር አብይ አህመድ  ለሁለት አስርተ አመታት በባላንጣለንት የኖሩትን ኢትዮጵያን እና ኤርትራን በበጎ ተነሳሽነት ዳግም ወደ ሰላም መንገድ ለመምራት በመብቃታቸው ይህ ከፍተኛ የክብር ሽልማት ሊበረከትላቸው እንደቻለ ተገልጿል።

የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈውርቂም የጠ/ሚ ዶክተር አብይ አህመድን የሰላም ጥሪ ሳያጣጥሉ በመቀበላቸው እና ለሁለቱ አገራት ዳግም ሰላም መስፈን ቁርጠኛ ውሳኔ በማስተላለፋቸው ከሳውዲው ንጉስ የክብር ሽላማት ሊበረከትላቸው ችሏል።

የሳውዲው ንጉስ ይህን ከፍተኛ የክብር ሜዳሊያ ለጠ/ሚ ዶክተር አብይ አህመድ እና ለፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ባበረከቱበት ፕሮግራም ላይ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በቦታው በመገኘት ታዳሚ ሆነዋል።