በአዲስ አበባ የህግ መስረት በሌለው ሁኔታ መንግስት ንፁሀን ወጣቶችን እያሰረ መሆኑ ታወቀ

0

አባይ ሚዲያ ዜና
ራሄል ሰሎሞን

ከአራት ቀን በፊት ያለፍርድ ቤት ትእዛዝ የአዲስ አበባ ወጣቶችን ማስር የጀመረው የኢትዮጵያ መንግስት አሁንም ወጣቶችን የማሰሩን ተግባር አጠናክሮ መቀጠሉን አንዳንድ የከተማዋ ነዋሪወች ተናገሩ። ከጥቂት ቀናቶች በፊት በቡራዮና አካባቢዋ ዘር ተኮር የሆነ አሰቃቂ ግድያና ዘረፋ መደረጉ ይታወቃል። የኦሮሚያ ፖሊስ እንደገለፀው በዚህ የተነሳ ከወንጀሉ ጋር ግንኙነት አላቸው ተብለው የተጠረጠሩ ግለሰቦቻና ቡድኖች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑ ታውቆል።

ይህ በእንዲ እንዳለ ያለምንም ማብራሪያና ከፍርድ ቤት እውቅና ውጭ እየተደረገ ያለው በጅምላ የአዲስ አበባ ወጣቶችን ማሰር ከግዜ ወደ ግዜ የኢትዮጵያን ህዝብ እያስቆጣ መምጣቱ ተገለፀ። ለዚህ ለጅምላ እስራት ምክንያት የጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ አስተዳድር እስከአሁን የሰጠው ማብራሪያ አለመኖሩ ብዙውን የከተማ ነዋሪወችን እያስደመመ ይገኛል። በዚህም የተነሳ በጠ/ሚሩ ላይ የሚቀርበው ትችት ከግዜ ወደ ግዜ እየጨመረ መምጣቱ ታውቋል።