የአርበኞች ግንቦት 7 አመራሮችና አባላት የስልክ ንግግር በደሕንነት ሰወች እንደሚጠለፋ ታወቀ

0

አባይ ሚዲያ መሪ ዜና
ራሄል ሰሎሞን

በቅርቡ ወደሀገር ቤት የገቡት የአርበኞች ግንቦት 7 አመራርና አባላት የስልክ ልውውጥ በደህንነት  ሰወች እንደሚጠለፍ ተረጋገጠ። በጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ የተደረገውን ጥሪ በቅርቡ ተቀብለው ወደሀገር ቤት ከገቡት አመራሮችና አባላት አንዱ የሆኑት አቶ ሙሉነህ እዮኤል ዛሬ በፌስ ቡክ ገፃቸው እንዳስታወቁት የአግ7 አቀባበል ኮሚቴ ዋና አስተባባሪ የነበረውን ወጣት ብርሀኑ ተክለያሬድን በእስር ቤት ለመጥየቅ በሄዱበት ወቅት ይህንን አስደንጋጭ መረጃ እንዳገኙ ገልፀዋል።

አስደንጋጩ ዜና ይላሉ አቶ ሙሉነህ “እነብርሃኑ የአግ7ን አመራሮች ለመቀበል በሚያስተባብሩበት ወቅትና አመራሮቹ ወደሀገር ከተመለሱ በኋላ ከአስተባባሪዎችና ከውጭ ከተመለሱ ጓዶች ጋራ በስልክ ያደረጓቸውን ንግግሮች ቅጂ መርማሪወች እንዳስደመጧቸው ተናግረዋል።”