የብአዴን 12ኛ ጉባኤ ድርጅታዊ ረቂቅ ፀደቀ (ከምናላቸው ስማቸው)

0

አባይ ሜድያ ዜና
በ12ኛው የብአዴን ጉባኤ ላይ የቀረበው ድርጅታዊ ረቂቅ ሪፖርት ከብዙ ወዝግብ በኋላ በአብላጫ ድምጽ ጸድቋል።

የለውጥ ሀይሉ ከፊቱ የተጋረጡብትን እንቅፋቶች በጉባኤው አባላት ከፍተኛ የድምጽ ድጋፍ አማካኝነት ወደፊት እየተሻገረ ይገኛል።በአማራ ጠልነት የሚታወቁት በርከት ሰምኦን እና ታደሰ ካሳ ያደራጁት የዋግህምራ ዞን ተወካዮች በልማት ሰበብ ያነሱት አደናቃፊ ጥያቄ በጉባኤው ተቀባይነት አላገኘም።

በታደሰ ካሳ ሚስት የተመራው 34 አባላት ያሉት የዋግህምራ ቡድን ሪፖርቱ ሲጸድቅ የተቃውሞ ድምጽ ቢሰጥም ሂደቱን አላበላሸውም።በፖለቲካዊ መድረክ ላይ ተገቢ ባልሆነ መንገድ የልማት ጥያቄ ያነሳው የዋግ ህምራ ቡድን በነ አቶ በረከት ስምኦን እና ታደሰ ካሳ የተረጨለትን ገንዘብ በመጠቀም የአገውን፥የራያን እና ሌሎች በአማራ ክልል የሚገኙ ማህበረሰቦችን በማነሳሳት የአማራ ህዝብን ዋነኛ የለውጥ ጥያቄዎች ለማድበስበስ ቢሞክርም አልተሳካም።

በለውጥ ሀዋርያው ገዱ አንዳርጋቸው ላይ ያነጣጠረው አሉታዊ ዘመቻም ከሽፎባቸዋል።የብአዴን 12ኛ ጉባኤ በኦዲትና ቁጥጥር ሪፖርት ላይ እየተዋያየ ይገኛል። ነገ እሁድ ከሰአት በኋላም የማእከላዊ ኮሚቴ ምርጫ ይካሂዳል ተብሎ ይጠበቃል።አዳዲስና ወጣት ስራአስፈጻሚዎችም ይመረጣሉ ተብሏል።

የአማራን ህዝብ ይቅርታ ይጠይቃል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረው አለምነው መኮንን እድሉን ባለመጠቀሙ ለምርጫ እንኳ የመቅረቡ ነገር አጠራጥሯል።ብአዴን ከህውሀት እራሱን አጥርቶ ከወጣ ከፍተኛ የህዝብ ድጋፍ ሊያገኝ ይቻላል ነው የተባለው።ካልሆነ ግን ከፊቱ የቀረበለትን ታሪካዊ እድል በማበላሸት ክልሉን የብጥብጥና የአመጽ ቀጣና ከማድረግ አልፎ የኢትዮጵያንም እድል ሊያበላሽ ይችላል።